ፈልግ

በኢትዮጲያ የጌታች የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በድምቀት ተከበረ በኢትዮጲያ የጌታች የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በድምቀት ተከበረ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ኢየሱስ ፣ ገር፣ የዋህ እና ሰው አክባሪ እንድንሆን አስተምሮናል” አሉ።

በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ። ዮሐንስ ግን፣ “ይህማ አይሆንም፤ እኔ ባንተ መጠመቅ ሲያስፈልገኝ እንዴት አንተ ወደ እኔ ትመጣለህ?” ብሎ ተከላከለ። ኢየሱስም፣ “ግድ የለም ፍቀድልኝ፤ ይህን በማድረግ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና” አለው፤ ዮሐንስም በነገሩ ተስማማ። ኢየሱስም እንደ ተጠመቀ ከውሃው ወጣ፤ ወዲያውኑም ሰማይ ተከፍቶ የእግዚአብሔር መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድበት አየ። እነሆ፣ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው” የሚል ድምፅ ከሰማይ ተሰማ። (3፡ 13-17)

በዛሬው ቀን ከማቴዎስ ወንጌል ተወስዶ በተነበበው ንባብ ውስጥ ኢየሱስ የተጠመቀበትን ሁኔታ የሚገልጽ ታሪክ እናገኛለን። ወንጌላዊው በኢየሱስ እና በመጥምቁ ዮሐንስ መካከል የነበረውን ኣና ኢየሱስ ለመጠመቅ ያቀረበውን ጥያቄ እና ውይይት በመግለጽ መጥምቁ ዮሐንስ “እኔ በአንተ መጠመቅ ሲገባኝ አንተ ወደ እኔ እንዴት ተመጣለህ?” ብሎ ያቀረበለትን ጥያቄ እናገኛለን። ይህ የኢየሱስ ውሳኔ መጥምቁ ዮሐንስን ያስደንቃል ፣ በእርግጥ መሲሑ መንጻት አያስፈልገውም፣ እርሱ የሚያነጻ አምላክ ነው እንጂ። እግዚአብሔር ግን ቅዱስ ነው ፣ የእርሱ እና የእኛ መንገድ የተለያየ ነው፣ እና ኢየሱስ የእግዚአብሔር መንገድ ነው ፣ ሊታይ የማይቻል መንገድ ነው ፡፡ የሚያስደንቅ አምላክ መሆኑን አስታውሱ።

ዮሐንስ በእርሱና በኢየሱስ መካከል የማይሻር የማይለዋወጥ ርቀት እንዳለ ተናግሯል ፡፡ “እኔ የጫማውን ማሰሪያ ለመፍታት የተገባው አይደለሁም” (ማቴ 3፡ 11)። የእግዚአብሔር ልጅ ግን በሰው እና በእግዚአብሔር መካከል ያለውን ይህንን ክፍተት ለመሙላት በትክክል መጣ። ኢየሱስ ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ጎን ነው፣ እርሱ ደግሞ ከሰው ወገን ነው ፣ በሰው እና በእግዚኣብሔር መካከል የነበረውን ክፍተት ይሞላዋል። ለዚህም ነው ዮሐንስን “ “ግድ የለም ፍቀድልኝ፤ ይህን በማድረግ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና” (ማቴ 3፡15) በማለት የተናግረው። መሲሁ ለመጠመቅ የጠየቀው ፍትህ ይረጋገጥ ዘንድ ነው፣ ይህ ማለት ደግሞ በልጅነት መነፈስ ታዛዢ በመሆን በደለኛ እና ኃጢአተኛ ከሆነው ሰው ጋር በመተባበር የሚፈጸም የአብ የማዳን እቅድ አካል ነው። ይህ የልጁ ትሕትና እና የእግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ እኛን የቅረበበት መንገድ ነው።

ነቢዩ ኢሳያስ ከዓለም መንፈስ ጋር ተጻራሪ በሆነ መልኩ በዓለም ውስጥ ተልእኮውን የሚፈጽም የእግዚአብሔር አገልጋይ ፍትህ በማወጅ “አይጮኽም፣ ቃሉን ከፍ አያደርግም፤ ድምፁን በመንገድ ላይ በኀይል አያሰማም። የተቀጠቀጠ ሸምበቆ አይሰብርም፤ የሚጤስም የጧፍ ክር አያጠፋም፤ ፍትሕን በታማኝነት ያመጣል” (ኢሳ 42፡2-3) በማለት ይናገራል። ይህ የትህትና አካሄድ ዛሬም ቢሆን ከጌታ ደቀመዛሙርት የሚጠበቅ የዋህነትን፣ ትህትና እንዲኖራቸው ኢየሱስ ያስተማረበትን ትህትና የሚገልጽ ነው። የእዚህ ዓይነት ትህንትና ያላቸው የኢየሱስ ደቀመዛሙርት ምን ያህል ናቸው? ትህትና የሌለው ደቀመዛሙርት እውነተኛ ደቀመዛሙርት አይደለም። አንድ ደቀመዝሙር ትህትና ሊኖረው ይገባል። አንድ ጥሩ የሚባል ደቀመዝሙር ትሁት ኣንናገር ሊሆን ይገባዋል። በሚስዮናዊነት ተግባር ፣ የክርስቲያን ማኅበረሰብ በማቅረብ ፣ በማሰባሰብ፣ የሰዎችን ተጨባጭ ሕይወት በመጋራት ሁል ጊዜ ሌሎችን ለመገናኘት እንዲወጣ ተጠርቷል ።

ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ እንደተጠመቀ ሰማያት ተከፈቱ መንፈስ ቅዱስም እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ወረደ ፤ ደግሞም “የምወደው ልጄ ይህ ነው እኔ በእርሱ አኖርሁ”  (ማቴ 3 17) የሚል ድምጽ ከሰማይ መጣ። በኢየሱስ ጥምቀት በዓል ላይ እኛም ጥምቀታችንን እናድሳለን። ልክ ኢየሱስ የተወደደ የአብ ልጅ እንደመሆኑ ፣ እኛ ከውኃ የተወለድን እና በመንፈስ ቅዱስ የምንወደው ልጆች መሆናችንን እናውቃለን - አብ ሁሉንም ይወዳል! ለሌሎች ወንድሞቻችን የእግዚአብሔርን ፍቅር በታላቅ ተልእኮ ላይ ለመመስረት እና ለሁሉም ሰዎች የአብ ወሰን የሌለው ፍቅርን ለመመስከር እና ለማወጅ ተጠርተናል።

ይህ የኢየሱስ ጥምቀት በዓል ጥምቀታችንን ያስታውሰናል። እኛም በጥምቀት ውስጥ ተወልደናል ፡፡ በጥምቀት መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ይኖራል ፡፡ የተጠመቅሁበት ቀን መቼ እንደ ሆነ ማወቁ አስፈላጊ የሆነው በእዚሁ ምክንያት ነው። የተወለድንበት ቀን መቼ እንደ ሆነ እንውቃለን፣ ነገር ግን የተጠመቅንበት ቀን መቼ እንደ ሆነ ግን እንዘነጋለን። መቼ እንደ ተጠመቃችሁ ታስታውሳለችሁ ወይ? ወደ ቤታችሁ ስትመለሱ ይህንን የቤት ሥራ መስራት እንዳትዘነጉ፣ የተጠመቃችሁበትን ቀን ጠያቃችሁ ተረዱ። የተጠመቅኩት መቼ ነበር? ብለን ጥያቄ ለራሳችን ማቅረብ ይጠበቅብናል። የተጠመቃችሁበትን ቀን በልባችሁ በእየአመቱ ማክበር ይኖርባችኋል። የጥምቀትን ጸጋ በሚገባ መረዳት እንችል ዘንድ፣ ይህንን ጸጋ በዕለታዊ ሁኔታዎች ውስጥ በቋሚነት ለመኖር እንድንችል ቅድስት ድንግል ማርያም እንድትረዳን አማላጅነቷን ልንማጸን ይገባል።

ምንጭ፥ የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በጥር 03/2012 ዓ.ም የጥምቀት በዓል በተከበረበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ካደረጉት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ የተወሰደ።

አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ

20 January 2020, 13:13