ፈልግ

አውሽ ቪዚ ቢንኬርናው በመባል በሚታወቀ ስፍራ የተገደሉት አይሁዳዊያን 75ኛ አመት ተዘከረ!

በፖላንድ አገር አውሽ ቪዚ ቢንኬርናው በመባል በሚታወቀው ስፍራ ላይ በጀርመን ናዚ በተገነባው እና ከመላው አውሮፓ የተሰበሰቡ አይሁዳዊያን የታጎሩበት፣ የተጨፈጨፉበት፣ የተወሰኑት ደግሞ ነጻ የወጡበት 75ኛው አመት በጥር 17/2012 ዓ.ም በመላው ዓለም ተዘክሮ ማለፉ ይታወሳል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጥር 17/2012 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ እንደ ተለመደው በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ክብር በመስጠት ከሚደገሙ ጸሎቶች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰውን “የእግዚኣብሔር መልአክ ማርያምን አበሰራት” የሚለውን ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኋላ ለዓለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት  በፖላንድ አገር አውሽ ቪዚ ቢንኬርው በመባል በሚታወቀው ስፍራ ላይ በጀርመን ናዚ በተገነባው እና ከመላው አውሮፓ የተሰበሰቡ አይሁዳዊያን የታጎሩበት፣ የተጨፈጨፉበት፣ የተወሰኑት ደግሞ ነጻ የወጡበት 75ኛው አመት እየተዘከረ እንደ ሚገኝ ቅዱስነታቸው ማናገራቸው የተገለጸ ሲሆን በእዚህ አስከፊ በሆነ ሁኔታ ሕይወታቸውን ላጡ፣ በሁኔታው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጎጂ ለሆኑ ሰዎች ሁሉ ጸሎት እንዲደረግ ጥሪ ማቀረባቸው የተገለጸ ሲሆን በክርስቶስ ቃል እንድንታመን፣ ራሳችንን ለአብ ምሕረት እንድንከፍት እና በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በመታገዝ መንፈሳዊ ለውጥ ማምጣት እንደ ሚገባ ገልጸው በዓለማችን ዙሪያ እንዲህ ያሉ አሰቃቂ የሚባሉ ድርጊቶች ተመልሰው እንዳይፈጠሩ በትጋት መሥራት እና መጸለይ ይገባል ብለዋል።

26 January 2020, 14:26