ፈልግ

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለዘላለም የእግዚአብሔር እናት ሆና ትኖራለች!

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የዓለማችን የማኅበረሰብ ክፍሎች ዘንድ 2019 ዓ.ም ተጠናቆ የ2020 ዓ.ም አዲስ አመት በታኅሳስ 22/2012 ዓ.ም መጀመሩ ይታወሳል። በተመሳሳይ መልኩ በዚሁ በጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር የ2020 ዓ.ም የአዲስ አመት መጀመሪያ ቀን ላይ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ከአዲስ አመት በዓል ባሻገር ስለ እመቤታችን እጅግ ቅድስት ድንግል ማርያም ከተደነገጉ አራት የእምነት እውነቶች (ዶግማዎች) መካከል በቀዳሚነት የሚገኘውና እ.አ.አ በ250 ዓ.ም አከባቢ ላይ የተደነገገው “እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ናት” መሆኑዋን በመግለጽ የሚከበረው አመታዊ በዓል በታኅሳ 22/2012 ዓ.ም ተክብሮ ማለፉ የሚታወስ ሲሆን ይህ በዓል በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በርካታ ምዕመናን በተገኙበት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ተከብሮ ማለፉ የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት “ማርያም ለዘለዓለም የእግዚኣብሔር እናት ሆና ትኖራለች” ማለታቸው ተገልጹዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በታኅሳስ 22/2012 ዓ.ም የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የዓለማችን ማኅበረሰቦች ዘንድ ከተከበረው የ2020 ዓ.ም አዲስ አመት ጋር ተያይዞ የተከበረውን “ማርያም የእግዚኣብሔር እናት” መሆኑዋን በሚዘክረው አመታዊ በዓል ላይ ያሰሙትን ስብከት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

“ነገር ግን የተወሰነው ዘመን በደረሰ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን፣ ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ” (ገላቲያ 4፡4)። ከሴት የተወለደው ኢየሱስ በእዚህ መንገድ ነበር ወደ እኛ የመጣው። እሱ ወደ ዓለም የመጣው ጎልማሳ ሆኖ ሳይሆን፣ ነገር ግን ቅዱስ ወንጌል እንደ ሚለው እርሱ “በማህፀን ተጸንሶ ተወልዶ ነበር” (ሉቃ 2፡ 21)። ዕለት ተዕለት ፣ ከወራት እስከ ወራት ድረስ የእኛን ሰብዓዊነታችንን የራሱ አደረገው። በሴት ማህፀን ውስጥ፣ እግዚአብሔር እና የሰው ልጆች ፈጽሞ በማይለያይ መልኩ አንድ ሆነዋል። አሁንም ፣ በመንግሥተ ሰማይ ፣ ከእናቱ ማህፀን በወሰደው ሥጋ ውስጥ ኢየሱስ ይኖራል ፡፡ በእግዚአብሄር ዘንድ ሰብዓዊነታችን ይገኛል።

በሴት ማህፀን ውስጥ በተፈጠረው እግዚአብሔርና በሰው ልጆች መካከል ያለውን ይህን ታላቅ አንድነት በዓመቱ የመጀመሪያ ቀን እናከብራለን ። በእግዚአብሄር ውስጥ ሰብአዊነታችን ለዘላለም ይኖራል፣ ማርያም ለዘለዓለም የእግዚአብሔር እናት ትሆናለች፡፡ እርሷ ሴት እና እናትም ጭምር ናት፣ ይህ በጣም መሰረታዊ የሆነ ነገር ነው። ከእሷ ሴት ከሆነችው ዘንድ መዳን ወጣ፣ ስለሆነም ያለ ሴት ድነት የለም። በእሷ ውስጥ ፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሕብረት ፈጥሩዋል፣ እኛም ራሳችንን ከእርሱ ጋር አንድ ለማድረግ ከፈለግን ፣ ማርያም፣ ሴት እና እናት መሆኑዋን በማመን ተመሳሳይ መንገድ መውሰድ ይኖርብናል።  ስለዚህ ነው እኛ የአምላካችንን ሰብአዊነት የቀሰቀሰውን እመቤታችንን በማክበር አዲስ ዓመት የምንጀምረው። በዚህ ጊዜ ውስጥ የሰውን ዘር መልበስ ከፈለግን ከሴቲቱ እንደገና መጀመር አለብን።

ከሴት የተወለደ። የሰው ልጅ እንደገና መወለድ የተጀመረው በሴት ነው። ሴቶች የሕይወት ምንጭ ናቸው ፡፡ ሆኖም ያለማቋረጥ ይሰደባሉ ፣ ይደበደባሉ ፣ ይደፈራሉ፣ በአስገዳጅ ሁኔታ ራሳቸውን ለሴተኛ አዳሪነት ያጋልጣሉ፣ በእዚህም ምክንያት በማሕጻናቸው ውስጥ ያለውን ሕይወት ለመግታት ይገደዳሉ። በሴቲቱ ላይ የሚደርሰው ማንኛውም ዓይነት ጥቃት ከሴት በተወለደ በእግዚአብሔር ላይ የሚቃጣ ስድብ ነው። የሰብአዊ ፍጡር መዳን የተገኘው ከሴት አካል በተገኘ አዳኝ አማካይነት ነው፣ የሰብዓዊነትን ደረጃ በትክክል ልንረዳው የምንችለው ለሴት ልጅ አካል ከምንሰጠው ክብር በመነሳት ነው። ይህ ክቡር የሆነው የሴቶች አካል ምን ያህል ጊዜ ነው በማስታወቂያ ሰሌዳዎች ላይ ተገቢ ባልሆነ መልኩ የሚለጠፈው፣ በየቦታው የሚለጠፉ የብልግና ምስሎች የመሳሰሉ ጥቅም ላይ የሚውሉ ነገሮች የሴቶችን ክብር ያጎድፋሉ። ሆኖም የሴቶች አካል ለፍጆታ ማቅረብ መቆም የሚገባው ጉዳይ ነው፣ እነርሱ የተከበሩ እና ክቡር መሆን ይኖርባቸዋል። እጅግ በጣም ድንቅ የሆነ በፍቅር ተፀንሶ ብርሃን ወደ ዓለም መጣ! በእኛም ዘመን የእናትነት ክብር ዝቅ ተደርገዋል፣ ምክንያቱም ከምንም በላይ እኛን የሚስበን ብቸኛ ነገር የኢኮኖሚ ዕድገት ነው። ለወደፊቱ የማሕጸናቸው ፍሬ የተሻለውን ለመስጠት በጣም አስቸጋሪ ጉዞዎችን የሚያደርጉ እና በአደጋ ላይ የወደቁ እናቶች አሉ ፣ ሆኖም ግን እነዚህ እናቶች ሆዳቸው ሙሉ በሆነ ነገር ግን ልባቸው ፍቅር አልባ በሆኑ ሰዎች እጅ ይወድቃሉ።

ከሴት የተወለደ። ሴቶች የፍጥረት ከፍታን ወደ መድረኩ እንደሚያመጡ መፅሐፍ ቅዱስ ይናገራል። የፍጥረትን ዋና ዓላማ በውስጣቸው ይይዛሉ፣ የትውልድን ሕይወት መጠበቅ፣ በሁሉም ነገር ላይ መተባበር፣ ሁሉንም ነገር መንከባከብ ይችላሉ።  በዛሬ ቅዱስ ወንጌል የእግዚአብሔር እናት እንዲሁ እንደ ሆነች መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል “ማርያም ግን ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ ይዛ ታሰላስል ነበር” (ሉቃ 2፡19) በማለት ይናገራል። በኢየሱስ መወለድ ተደስታ ነበር፣ በቤተልሔም የታየው እንግዳ ተቀባይነት ማጣት ሐዘን ውስጥ ከቱዋት ነበር፣ የዮሴፍ ፍቅር እና የእረኞች አድናቆት፣ የተሰጠው ተስፋ እና የወደፊቱ ጊዜ እርግጠኛ አለመሆን ማርያም እነዚህን ሁሉ ነገር በውስጧ ጠብቃ ይዛ ነበር። ሁሉንም ነገር ወደ ልብዋ ወሰደች ፣ እናም በልቧ ውስጥ ፣ ሁሉንም ችግሮች በትክክለኛው ቦታ ላይ አስቀመጠችሁ፣ መከራን እና ችግርን ፣ በልቧ ውስጥ ሁሉንም በፍቅር ቅደም ተከተል አስቀምጣ ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሔር አደራ ሰጠች።

በቅዱስ በወንጌል ውስጥ ማርያም ይህንን ተመሳሳይ ነገር ለሁለተኛ ጊዜ ትፈጽማለች - በኢየሱስ ስውር ሕይወት መጨረሻ ላይ “እናቱም ይህን ሁሉ በልቧ እንደጠበቀች” ይናገራል። ይህ መደጋገም እመቤታችን “በልቧ ውስጥ ታኖረው ነበር” የሚለው ልምድ ከጊዜ ወደ ጊዜ ያከናወነችው ነገር ሳይሆን የተለመደ ነገር መሆኑን እንድንገነዘብ ያደርገናል። ሴቶች በተለምዶ ህይወትን ወደ ልባቸው ያመጣሉ። የሕይወት ትርጉም የሚገኘው ነገሮችን በማከናወን ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ነገሮችን ወደ ልብ በመሳብ እንደሆነ ሴቶች ያሳዩናል። ልብን በትኩረት የሚመለከቱ ሰዎች ብቻ ናቸው ነገሮችን በክክል ለመረዳት የሚችሉት፣ ነገሮችን በተገቢው ሁኔታ የሚመለከቱ ሰዎች በቅድሚያ ልብን ሊመለከቱ የገባል፣ ምክንያቱም እያንዳንዱን ሰው እንዴት መመልከት እንደ ሚገባቸው ሰለሚገነዘቡ፣ ወንድማቸውን ከስህተቱ ባሻገር ስለሚመለከቱ፣ እንዲትን እህት ከስሕተቶቿ ባሻገር ሂደው መመልከት ሰለሚችሉ፣ ችግሮችን በተስፍ መጋፈጥ ስለሚችሉ።  እግዚአብሔርን በሰው ሁሉ እና በሁሉም ነገሮች ውስጥ መመልከት ይችላሉና።

ይህንን አዲስ ዓመት ስንጀምር “በልቤ መመልከት አውቃለሁኝ ወይ?” በማለት ራሳችንን እንጠይቅ። በልቤ   ሰዎችን መመልከት አውቃለሁኝ ወይ? የምኖርበትን ህዝብ ልብ እላለሁ ወይ? ወይስ በሐሜት እነርሱን ዝቅ አድርጌ እመለከታለሁ? ከሁሉም በላይ ፣ ጌታን በልቤ መሃከል ውስጥ አኖረዋለው ወይስ በሌሎች እሴቶች ፣ በሌሎች ፍላጎቶች ላይ ለምሳሌ እድገት፣ ሀብት ፣ ስልጣን ላይ ነው ልቤን የማኖረው? ሕይወታችንን ወደ ልባችን የምንወስድ ከሆነ በዙሪያችን ያለውን የግድየለሽነት ስሜት እንዴት እንደምናስወግድ እና እንዴት እንደምንሸነፍ እናውቃለን።  ስለዚህ ሌሎችን ወደ ልብ ለመውሰድ እና እነሱን ለመንከባከብ የሚያስችል  ፍላጎት በዚህ ዓመት በውስጣችን እንዲቀሰቀስ ይረዳን ዘንድ ጸጋውን እንጠይቅ። የተሻለ ዓለምን የምንፈልግ ከሆነ ፣ ሰላም የሰፈነባት መኖሪያ እና የጦርነት ስፍራ ያልሆነች ዓለም የምንፈልግ ከሆነ፣ እያንዳንዳችን የሴትን ክብር ከፍ ማድረግ ይኖርብናል። የሰላም ልዑል ከሴት የተወለደ ነው። ሴቶች ሰላም ሰጭዎች እና ሰላም እንዲስፍን መሸምገል ስለሚችሉ በውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ውስጥ ሙሉ በሙሉ መካተት ይኖርባቸዋል። ምክንያቱም ሴቶች ስጦታቸውን ሲያካፍሉ፣ ዓለም ራሷን የበለጠ አንድ በመሆን ሰላሟን ታገኛለች። ስለሆነም ሴቶች ወደ ፊት የሚያደርጉዋቸው እያንዳንዱ እርምጃ የሰው ልጆች ሁሉ እርምጃ ይሆናል።

 

ከሴት የተወለደ። አዲስ የተወለደው ኢየሱስ በእናቱ ፊት በሴቲቱ ዓይኖች ላይ ያንጸባርቅ ነበር። በቅድሚያ እርሱን የዳሰሰችው እርሷ ናት፣ የመጀመሪያውን ፈገግታ የተለዋወጠው ከእርሷ ጋር ነው። በእሷ አማካኝነት የርህራሄው አብዮት ተጀመረ። ሕፃኑን ኢየሱስን እየተመለከተች ቤተክርስቲያኗ ያንን አብዮት ለመቀጠል ተጠርታለች። እሷም ልክ እንደ ማርያም ሴት እና እናትም ነች። ቤተክርስቲያን ሴት እና እናት ነች፣  በእመቤታችን ውስጥ ልዩ የሆነ ባሕሪዋን ታገኛለች። እርሷ ብጽዕት ማርያምን በመመልከት ለኃጢያት እና ለዓለማዊነት ፈቃደኛ አይደለሁም ብላ ድምጿን ታሰማለች። በቤተክርስቲያን ማርያም ውጤታማ እንደሆንች አድርጋ ስለምትመለከተ ቅዱስ ወንጌልን ለማወጅ እና በሰዎች ልብ ውስጥ ለመወለድ እንደ ተጠራች ሆና ይሰማታል። ማርያምን እንደ እናት ትመለከታለች፣ በእዚህም የተነሳ እያንዳንዱን ወንድና ሴት እንደ ወንድም ወይም እህት አድርጋ ተቀበላለች።

ቤተክርስቲያን ወደ ማርያም ለመቅረብ ስትነሳ ቤተክርስቲያን ራሷን ታገኛለች፣ ማዕከሉዋን አንድነቷን በእርሷ ውስጥ ታገኛለች። የሰው ተፈጥሮአዊ ጠላት የሆነው ዲያብሎስ ልዩነቶችን፣ መከፋፈልን፣ ርዕዮተ ዓለሞችን፣  ግለሰባዊ አስተሳሰብን እና ፓርቲዎችን በማጉላት ለመከፋፈል ይፈልጋል። እኛ ግን መዋቅሮችን ፣ ፕሮግራሞችን እና አዝማሚያዎችን ፣ ርዕዮተ ዓለምን እና ተግባሮችን ከእነዚህ በመጀመር ቤተክርስቲያንን የምንመለከት ከሆንን ስለቤተክርስቲያን አልተረዳንም ማለት ነው። አንድ ነገር ልንረዳ እንችል ይሆናል፣ ነገር ግን የቤተክርስቲያኗን ልብ አንረዳም። ምክንያቱም ቤተክርስቲያን የእናት ልብ አላት። እኛን ወንዶችና ሴቶች ልጆች የእግዚኣብሔር እናት ዛሬ አማኞችን በሙሉ እንድትሰብሰብ ተጠርታለች። እናታችን ሆይ ፣ በውስጣችን ተስፋን ፍጠሪ አንድነትን አምጪ። የአድነት ሴት ሆይ ፣ ይህንን አዲስ አመት ለአንቺ በአደራ እንሰጣለን። በልብሽ ውስጥ ያዢን። የእግዚአብሔር ቅድስት እናት ሆይ እናመሰግንሻለን።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
01 January 2020, 14:41