ፈልግ

በቫቲካን የተለያዩ አገራትን በመወከል የተሾሙ አዳዲስ አምባሳደሮች ጋር በቫቲካን የተለያዩ አገራትን በመወከል የተሾሙ አዳዲስ አምባሳደሮች ጋር  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ መልካም እና ሰላም የሰፈነበት ዓለም ለመገንባት ጥረት ማደረግ ይኖርብናል አሉ።

በቫቲካን የተለያዩ አገራትን በመወከል የተሾሙ አዳዲስ አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤዎቻቸውን በታኅሳስ 09/2012 ዓ.ም ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ማቅረባቸው የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባደረጉት ንግግር እንደ ገለጹት መልካም የሆነ ዓለም ለመገንባት ጥረት ማደረግ ይኖርባችኋል ማለታቸው ተገልጹዋል። እነዚህ በቫቲካን የተለያዩ አገራትን በመወከል የተሾሙት አምባሳደሮች ተወክለው የመጡባቸው አገሮች ሲሼልስ፣ ማሊ፣ አንዶራ፣ ኬኒያ፣ ሌቶኒያ እና ኒጄር እንደ ሆነ የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባደረጉት ንግግር የእነዚህ አምባሳደሮች ሚና እና ዋነኛው ተግባር ሊሆን የሚገባው ቁርጠኝነት በተሞላው መልኩ የጋራ ጥቅምን ማስከበር እና የጋራ መኖሪያ ቤታችን የሆነችውን ምድራችንን በኃላፊነ መንከባከብ እንደ ሆነ ጨምረው ገልጸዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

እኛ ክርስቲያኖች እንደ “የሰላም አለቃ” አድርገን የምንቆጥረው አምላካችን የሚወልደበትን የገና በዓል ለማክበር በመዘጋጀት ላይ እንገኛለን ያሉት ቅዱስነታቸው እርሳቸው በወቅቱ አዲስ ለተሾሙ አምባሳደሮች ያደረጉት ንግግር ሰላም ላይ ትኩረቱን ያደረገ እንደ ነበረ ከደርሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል። ከእነዚህ በቫቲካን የተለያዩ አገራትን በመወከል የተሾሙ አዳዲስ አምባሳደሮች መካከል ሲሼልስን፣ ኬንያን እና ሌቶኒያን በመወከል የተመደቡት አባሳደሮች ሴቶች ሲሆኑ እነርሱም በኢኮኖሚ እና በሳይንስ ዘረፉ የበቃ ልምድ እና እውቀት ያላቸው እንደ ሆነ ተገልጹዋል፣ በተጨማሪም ሶስት ወንዶች የሚገኙበት ሲሆን እነዚህም በቅደም ተከተል ከማሊ ከአንዶራ እና ኒጀር የመጡ ናቸው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር ፍትህ ኣና ሰላም የስፈነበት ዓለም መገንባት ተቀዳሚ ተግባር ሊሆን እንደ ሚገባው በአጽኖት ገልጸው በተጨማሪም በአካባቢያችን ላይ እይደርሰ የሚገኘውን ውድመት ዘላቂነት ተግዳሮት በመሆኑ የተነሳ ኃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ ተግባራችንን በማከናወን ፍትሃዊ እና ሰላማዊ ዓለም መገንባት አስፈላጊ መሆኑን አብከረው ገለጸዋል።

ሕይወት፣ ሰብዓዊ ክብር እና መብቶች ሊከበሩ የገባል

ሰላም አሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ንግግራቸውን በቀጠሉበት ወቅት ሰላም  “የመላው የሰው ዘር ምኞት” ነው፣ የእዚህ ዓይነቱ ሰላም ሊረጋገጥ የሚችለው ደግሞ “ውይይት፣ ዕርቅ እና ሥነ ምህዳራዊ ልውጥ እያስከተለ የሚገኘውን አደጋ ከግምት ባስገባ” መልኩ ሊሆን እንደ ሚገባው ገለጸው በተጨማሪም ሰላም የተስፋ ጉዞ ነው በማለት ገልጸዋል።  ስለሆነም በእዚህ ረገድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አስፈላጊ በሆኑ ሁኔታዎች ተባብራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑዋን የገለጹ ሲሆን በቫቲካን የተለያዩ አጋራትን በመወከል የተሾሙ አምባሳደሮች ጋር በመተባበር ሰላም በዓለም ዙሪያ እንዲረጋገጥ ቤተ ክርስቲያኗ የበኩሉዋን አሰተዋጾ ማበርከት እንደ ምትፈለግ ቅዱነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

በዜጎች እንዲሁም በክልላዊ እና በዓለም አቀፍ ግጭቶች፣ በማህበራዊ ክፍፍል እና እኩልነት በማይታይበት ዓለም ውስጥ፣ በሀቀኝነት እና በእውነት ላይ የተመሠረተ ገንቢ እና አሳታፊ ውይይቶችን ማከናወን ተገቢ እንደ ሆነ በንግግራቸው የገለጹት ቅዱነታቸው በዓለም ማህበረሰብ ውስጥ የእያንዳንዱን ሰው እና የሁሉን ህዝብ መልካም ነገር ለማስፋፋት ከእያንዳንዱ ኃላፊነት የሚሰማው አጋር ከሆኑ ሰዎች ጋር የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በትብብር እንደ ምትሰራ ቅዱነታቸው በንግግራቸው አመላክተዋል።

የእናንተ ተልዕኮ ወክላችሁት ከመጣችሁት አገራት እና በቅድት መንበር መካከል መልካም ግንኙነት እንዲፈጠር ከማሳቻል ባሻገር ሰብዓዊ ሕይወት ፣ ክብር እና መብት የሚከበረበት እና ፍትህ የሰፈነበት ዓለምን ለመገንባት የሚያስችል ጠንካራ ተልዕኮ ጭምር እንደ ተሰጣቸው ቅዱነታቸው ጨምረው ገልጸዋል.

20 December 2019, 12:40