ፈልግ

በኢርቅ ባግዳድ በመደረግ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ በኢርቅ ባግዳድ በመደረግ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ  

ር.ሊ.ጳ ፍራችስኮስ “በኢራቅ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ በደረሰው ጣቅት ብዙ ሕዝብ በመሞቱ አዝኛለሁ!”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የአገር ጎብኚዎች በኅዳር 21/2012 ዓ.ም. በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ መስረቱን አድርጎ የነበረ አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ለእመቤታችን ለቅድስት  ደንግል ማርያም ከሚቀርቡ የመማጸኛ ጸሎቶች ውስጥ አንዱ የሆነው መልአኩ ገብርኤል ማርያምን ያበሰረበትን  ወቅት በማሰብ፣ የእግዚኣብሔር መልኣከ ማርያምን እንዳበሰራት እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት መጸነሱን በሚዘክረው የገብርኤል ብሥራት ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኋላ ለዓለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት እንደ ገለጹት በአሁኑ ወቅት በኢራቅ እየተካሄደ የሚገኘው ሕዝባዊ አመጽ በቅርበት እየተከታተሉ መሆኑን የገለጹት ቅዱስነታቸው በተለይም ደግሞ ከቅርብ ቀናት ወዲህ የተደረጉት የተቃውሞ ሰልፎች በርካታ ሕዝቦች መሞታቸው እና ገሚሶቹ ደግሞ መጎዳታቸውን መስማታቸው እንዳሳዘናቸው ቅዱስነታቸው ገልጸዋል። “ለሞቱት እና ለቆሰሉት እፀልያለሁ” በእዚህ ጥቃት ሕወታቸውን ላጡ እና ጉዳት ለደርሰባቸው ሰዎች ቤተሰቦች ከእነርሱ ጋር መሆኔን ለመግለጽ እወዳለሁ፣ እግዚአብሔር ሰላምና ስምምነትን ለእራቅ ሕዝብ ይሰጥ ዘንድ ጸሎቴ እና ምኞቴ ነው ካሉ በኋላ እንደ ተለመደው እና ዘወትር  ሳምንታዊ መልእክታቸውን ከማገባደዳቸው በፊት “እባካችሁን ለእኔ መጸለይ እንዳትዘነጉ” ካሉ በኋላ በእዚያው ለሚገኙት ምዕመናን ሰላምታ አቅርበው እና ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ሰጠተው መሰናበታቸው ከሥፍራው የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።

01 December 2019, 11:19