ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ከሆኑት ሳልቫ ኪር ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት   ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ከሆኑት ሳልቫ ኪር ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለደቡብ ሱዳን መሪዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት ቀን የሚከበርበት የገና በዓል በታኅሳስ 15/2012 ዓ.ም ተክብሮ ማለፉ ይታወሳል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ይህንን የገና በዓል አስምልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ለደቡብ ሱዳን መሪዎች ማስተላለፋቸው የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው “በግጭት ለተበታተነው የደቡብ ሱዳን ህዝብ ሰላምና ብልፅግናን እንደ ሚመኙ” ገልጸዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት ቀን የሚከበርበት የገና በዓል ብዙን ጊዜ ሰዎች በአካል ማየት ለሚፈልጓቸው ሰዎች የመልካም ምኞት መልእክት የሚያስተላልፉበት እለት እንደ ሆነ የሚታወቅ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእዚህ በጋና በዓል ቀን ለደቡብ ሱዳን ህዝብ እና የፖለቲካ መሪዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን በማስተላለፍ በዚያ በእድሜ ጠገብ ባህል ውስጥ ተሳትፈዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ይህንን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ያስተላለፉት የካትርቡሪ የአንግሊካን ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳ ክቡር ጆን ካልመርስ ጋር በጋራ በመሆን እንደ ሆነ የተገለጸ ሲሆን “በዚህ የገና በዓል ወቅት እና በአዲሱ ዓመት መጀመሪያ ላይ ለእናንተ ለደቡብ ሱዳን መሪዎች እና ለሁሉም የደቡብ ሱዳን ህዝብ ሰላምን እና ብልጽግናን እየተመኘን መልካም ምኞታችንን እንገልጽላችኋለን፣ ከእናተ ጋር መሆናችንን እየገለጽን በቅርቡ የተፈራረማችሁት የሰላም ስምምነት ተፋጻሚ ይሆን ዘንድ በጸሎታችን ከእናንተ ጋር ነን” ማለታቸው ተገልጹዋል። “የሰላም ልዑል የሆነው ጌታ ኢየሱስ የእውቀት ብርሃን እንዲሰጣችሁ እና እርምጃዎቻችሁን በመልካም እና በእውነት መንገድ እንዲመራ፣ ተወዳጅ የሆነችሁን አገራችሁን ለመጎብኝት ያለንን ፍላጎት እውን ያድርግልን” ማለታቸው ተገልጹዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የአገር ጎብኚዎች በጥቅምት 30/2012 ዓ.ም. በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ለእመቤታችን ለቅድስት  ደንግል ማርያም ከሚቀርቡ የመማጸኛ ጸሎቶች ውስጥ አንዱ የሆነውን መልአኩ ገብርኤል ማርያምን ያበሰረበትን  ወቅት በማሰብ፣ የእግዚኣብሔር መልኣከ ማርያምን እንዳበሰራት እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት መጸነሱን በሚዘክረው የገብርኤል ብሥራት ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኃላ ለዓለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት እንደ አወሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በመጪው 2020 ዓ.ም ደቡብ ሱዳንን እንደ ሚጎበኙ መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን በእዚያች አገር ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት ባለድርሻ አካላት አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ማደረጋቸው የሚታወስ ሲሆን በአገሪቷ የወንድማማችነት መንፈስ ይጠናከር ዘንድ ሁላችንም የበኩላችንን ጥረት ማደረግ ይጠበቅብናል ማለታቸው ይታወሳል።

26 December 2019, 11:46