ፈልግ

የስብከተ ገና ወቅት ከተጠናወተን የግድዬለሽነት መንፈስ ነጻ የምንወጣበት ወቅት ነው!

የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ለማከብር ዝግጅት የሚደረግበት የስብከተ ጋና ወቅት በትላንትናው ዕለት  ማለትም በኅዳር 21/2012 ዓ.ም መጀመሩ ይታወቃል። ስብከተ ገና ኢየሱስ በዓለም ታሪክ ውስጥ በመግባት የዓለምን የቀን አቆጣጠር ወደ ዓመተ ምሕረት እንደቀየረው ሁሉ የእኛንም ሕይወት በምሕረቱ ሊሞላት እንደ ሚመጣ እና በእርሱ በኩል ሁሌም ዝግጁ መሆኑ የሚሰበክበት ወቅትና፣ እኛም ለእዚህ ጌታ ለሚያደርግልን መንፈሳዊ ለውጥ የማምጣት ጥሪ በቃላት እና በትግባር በትደገፈ መልኩ ምላሽ የምንሰጥበት ወቅት ላይ እንገኛለን።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በእዚህም መሰረት የእዚህ የስብከተ ገና 1ኛ ሣምንት በኅዳር 21/2012 ዓ.ም በተጀመረበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የአገር ጎብኚዎች እንደ ተለመደው እና ዘወትር እሁድ ዕለት በእለቱ በተነበቡው ቅዱስ ወንጌል ላይ መሰረቱን ባደርገው ስብከት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት “የስብከተ ገና ወቅት ከተጠናወተን የግድዬለሽነት መንፈስ ነጻ በመውጣት ወንድሞቻችንን የምናገለግልበት ወቅት ነው” ማለታቸው ተገልጹዋል። 

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በኅዳር 21/2012 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በእለቱ የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ የተጀመረውን የመጀመሪያው ሣምንት የስብከተ ገና ወቅት አስመልክተው ያደርጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ዛሬ የመጀመሪያው የስብከተ ገና ሳምንት እና እንዲሁም አዲሱ የዓመቱ የስረዓተ አምልኮ አቆጣጠር ስረዓት ይጀመራል። በስበከተ ገና ሣምንታት ውስጥ የሚደረጉት ሥርዓተ አምልኮዎች በእያንዳንዱ ቀን ኢየሱስ ወደ ሕይወታችን ውስጥ እንደ ሚመጣ እና እርሱም በኋለኛው ዘመን በክብር እንደ ሚመጣ፣ እኛን በማስታወስ በእዚህ በአራት ሳምንታት ውስጥ ኢየሱስ የሚወለድበትን ቀን በአግባቡ እንድናከብር ያደርገናል። ይህ እርግጠኝነት ነቢዩ ኢሳያስ እንደተናገረው ከእርሱ አፍ በሚወጣው ድምጽ በመታገዝ በእዚህ በያዝነው የስብከተ ገና ወቅት ጎዞ ላይ ከእኛ ጋር በመሆን የወደፊቱን ጊዜ በልበ ሙሉነት እንድንጠባበቅ ያደርገናል።

ዛሬ በተነበበው የመጀመሪያው ምንባብ ውስጥ ነቢዩ ኢሳይያስ “በዘመኑም ፍጻሜ፣ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተራራ ከተራሮች ከፍ ብሎ ይመሠረታል፤ ከኰረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ ሕዝቦችም ሁሉ ወደዚያ ይጐርፋሉ” (ኢሳ 2፡2) በማለት ያቀረበውን ትንቢት አዳምጠናል። በኢየሩሳሌም ያለው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሁሉም ህዝቦች መሰባሰቢያ እና የሚገናኙበት መዕከላዊ የሆነ ሥፍራ እንደ ሆነ ሆኖ ቀርቡዋል። የእግዚአብሔር ልጅ ሥጋ ለብሶ ከተወለደ በኋላ ፣ ኢየሱስ ራሱ እንደ እውነተኛው ቤተ መቅደስ ራሱን በእዚያው ስፍራ ይገልጻል። ስለዚህ ነቢዩ ኢሳያስ አስደናቂ ራዕይ መለኮታዊ ተስፋን ለእኛ በመግለጽ እንደ መንፈሳዊ ነጋዲ በመሆን ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚደረገውን ጉዞ በእዚህ መልኩ እንድናከናውን ይመራናል። ፍትህ የተራቡ እና የተጠሙ ሰዎች ስንት ናቸው! እነዚህን ነገሮች ማግኘት የሚቻለው ደግሞ የጌታን መንገድ በመከተል ብቻ ነው፣  ግጭትና ኃጢአት ወደ እዚህ ምድር የሚመጣው ግለሰቦች እና ማህበራዊ ቡድኖች ግጭቶችን እና ጦርነቶችን የሚያስከትሉ በራስ ወዳድነት ፍላጎቶች የተያዙ ዱካዎችን መከተል ስለሚመርጡ ነው። መጪው ጊዜ የእግዚአብሔርን መንገድ ሊያሳየን የሰላም መልእክተኛ ሆኖ የሚመጣውን የኢየሱስን መምጣት ለመቀበል ትክክለኛ ጊዜ ነው።

በዛሬው ቅዱስ ወንጌል (ማቴ 24፡33-44) ውስጥ  “ጌታችሁ በየትኛው ቀን እንደሚመጣ አታውቁምና ተዘጋጅታችሁ ኑሩ” (ማቴ 24፡44) በማለት ለመጪው ጊዜ ዝግጁ እንድንሆን ኢየሱስ ያሳስበናል። ነቅቶ መጠበቅ ማለት እንዲያው በግርዱፉ በአካላችን ላይ የሚገኘውን ዓይናችንን ገልጠን ወይም ከፍተን  መጠበቅ ማለት አይደለም፣ ነገር ግን ልባችንን ነፃ ማደረግ እና በትክክለኛው አቅጣጫ ላይ መጓዝ፣ ማለትም ለጋሽ ለመሆን እና ለማገልገል ፈቃደኛ መሆን ማለት ነው። ይህ ነቅቶ መጠበቅ ይባላል! እኛ ልንነቃበት የሚገባው የእንቅልፍ ዓይነት መሆን የሚገባው የግድዬለሽነት፣ ከንቱነት ፣ እውነተኛ በሆነ መልኩ ከሰዎች ጋር ግንኙነቶችን መመሥረት ካለመቻል፣ በብቸኝነት፣ በሽታ የሚሰቃየውን፣ ገለልተኛ  የሆነውን ወንድማችንን እንዳንቀርብ ከሚያደርገን እነዚህን ከመሳሰሉ የእንቅልፍ ዓይነቶች መንቃት ይኖርብናል። ስለዚህ የሚመጣውን ኢየሱስ በተስፋ ንቅቶ መጠበቅ ማለት ቁርጠኛ ወደ ሆነ አግልግሎት መተርጎም አለበት። ከሁሉም በላይ ጥያቄው ለእግዚአብሔር ሥራ፣ ለእርሱ ድንቅ ተግባር ቅድሚያ መስጠት ማለት ነው። ነቅቶ መጠበቅ ማለት ደግሞ፣ በእውነቱ በችግር ውስጥ የሚገኙትን ባለእንጀሮቻችንን በትኩረት መከታተል፣ የእነርሱን ችግር የእኛ በማድረግ ችግሮቻቸውን ለመፍታት መሞከር፣ እነርሱ ማለትም በችግር ውስጥ የሚገኙ እህት ወንድሞቻችን ጥሪ እስኪያደርጉልን ድረስ ሳንጠብቅ፣ እግዚኣብሔር ለእኛ እንደ ሚያደርገው ዓይነት እኛም ችግሮቻቸውን ቀድመን በመተንበይ እና በመረዳት ከጎናቸው ልንሆን ይገባናል።

ንቁ እና የተስፋ እናት የሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የኢየሱስ መገለጫ ወደ ሆነው “የጌታ ተራራ ላይ” ትኩረታችንን ሙሉ በሙሉ ማደረግ እንችል ዘንድ ወደ እዚያው በምናደርገው ጉዞ ትደግፈን ዘንድ እንድትመራን አማላጅነቷን ልንማጸን ይገባል።

01 December 2019, 11:15