ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ፍራንቸስኮስ በታይላንድ ከሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዓን ጳጳሳት ጋር በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ፍራንቸስኮስ በታይላንድ ከሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዓን ጳጳሳት ጋር በተገናኙበት ወቅት  

ጳጳሳት አገልጋዮች ናቸው እንጂ ሥራ አስኪያጆች መሆን አይገባቸውም!

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከኅዳር 09-16/2012 ዓ.ም ድረስ በታይላንድ እና በጃፓን በቅደም ተከተል የሚያደርጉትን 32ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በኅዳር 09/2012 ዓ.ም አመሻሹ ላይ መጀመራቸውን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በእዚህም መሰረት ቅዱስነታቸው በኅዳር 11/2012 ዓ.ም በታይላንድ ብሔራዊ ቤተመንግሥት ውስጥ ተገኝተው የአገሪቷን ጠቅላይ ሚንስትርን ጨምሮ በስፍራው ለተገኙ የአገሪቷ ባለስልጣናት እና የተለያዩ አገራት ልዑካን ንግግር ማደረጋቸውን መግለጻችን የሚታወስ ሲሆን ከእዚያም በመቀጠል ቅዱስነታቸው በታይላንድ የቡድሃ እምነት ቤተመቅደስ ውስጥ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በታይላንድ የሚያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት በቀጠሉበት ወቅት በኅዳር 12/2012 ዓ.ም በታይላንድ ከሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዓን ጳጳሳት ጋር ተገኝተው በተወያዩበት ወቅት ጳጳሳቱ የቅዱስ ኒኮላስን አብነት በመከተል ሐዋርያዊ ተግባራችውን እንዲያከናውኑ ጥሪ ማቅረባቸው ተገልጹዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ንግግራቸውን የጀመሩት “ለእስያ አጥቢያ አብያተ-ክርስቲያናት ሁሉ ቅዱስ ወንጌልን ማዳረስ እንችል ዘንድ እንዲያነሳሳን” የብጹዕ ኒኮላስን አብነት መከተል እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

ብፁዕ ኒኮላስ እ.አ.አ በ1930 ዓ.ም በሰሜናዊ ታይላንድ ውስጥ ቅዱስ ወንጌልን በማስፋፋት ላይ የነበረ ሚሲዮናዊ ካህን የነበረ ሲሆን የዘረዐ ክህነት ተማሪዎችን በማዘጋጀት እና ተገቢውን ስልጠና እንዲወስዱ በማደረግ በታይላንድ ብዙ ሰዎች የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አባል እንዲሆኑ ተግቶ የሰራ ብጹዕ ነው።

ብጹዕ ኒኮላስ ፀረ-ክርስትያን ስሜቶች በነበሩበት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት “በሽብር” ድርጊቶች ላይ ተሰማርቷል የሚል ክስ ቀርቦበት የ15 ዓመት እስራት ተፈረዶበት የነበረ ሲሆን አብረውት በማረሚያ ቤት የነበሩትን 68 የሕግ ታራሚዎች በማስተማር እና በማጥመቅ በማረሚያ ቤት ውስጥ ሚስዮናዊ ተግባሩን ያከናውን የነበረ ሲሆን እ.አ.አ በ 1944 ዓ.ም በ49 አመቱ በሳንባ ነቀርሳ በሽታ ከእዚህ ዓለም በሞት ተለይቱዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እ.ኤ.አ. 2020 ዓ.ም የእሲያ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት የተቋቋመበት 50ኛው ዓመት እንደ ሚከበር ያስታወሱ ሲሆን በእሲያ አገራት ውስጥ የክርስትና እምነት መገለጫ የሆኑ ምልክቶች የሆኑ የአምልኮ ስፍራዎች እና የሚሲዮናዊያኑ ልፋት እና መልካም ተግባር ውጤት ለመመልከት እና ለመጎብኘት መልካም እና ተስማሚ አጋጣሚ መሆኑን ገልጸው “በእስያ አህጉር ውስጥ የምትገኘው ቤተክርስቲያን እና ማኅበርሰቡ የቅዱስ ወንጌል አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ጳጳሳቱ በርትተው መሥራ እንደ ሚኖርባቸው ገልጸዋል።

“የእስያ አህጉር ፈጣን የቴክኖሎጂ ዕድገቶች የሚታይበት፣ ሰፊ ዕድሎችን ሊከፍቱ የሚችሉ “ባሕል እና  የሐይምኖት ብዝሃነት” በሰፊው የሚስተዋልበት አህጉር መሆኑን” የገለጹት ቅዱስነታቸው በተመሳሳይ መልኩም “ከልክ በላይ የሆነ የሸማቾች የመሸመት ፍላጎት መጨመር፣ የፍቅረ ነዋይ ስሜቶች ማደግ፣ የአደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚ ሰዎች ቁጥር መጨመር፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ለስደተኞ የሚደረገው እንክብካቤ መቀነስ፣ የሰዎች ጉልበት ብዝበዛ፣ እንዲሁም በሀብታሞች እና በድሃዎች መካከል ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እኩልነት አለመኖር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱ በእስቲያ አሁጉር ውስጥ የሚታዩ ተግዳሮቶች መሆናቸው ቅዱስነታቸው እንደ ሚያሳስባቸው ለብጹዕን ጳጳሳቱ ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጨምረው እንደ ገለጹት የመጀመሪያዎቹ ሚስዮናውያን የነበራቸውን “ብርታት፣ ደስታ እና ታላቅ ጥንካሬ ማስታወስ አሁን ያለንበትን ሁኔታ እና ተልዕኮዎቻችንን ለማስፋት እና የበለጠ ለውጥ ለማምጣት ይረዳናል” ብለዋል። ያ ትውስታ “ያለፈው ጊዜ ቅዱስ ወንጌልን ለማስፋፋት እና ለማወጅ መልካም ጊዜ ነበረ” ከሚለው እምነት እና አስተሳሰብ ነፃ እንደ ሚያደርግ የገለጹት ቅዱስነታቸው እንዲሁም “ማንኛውንም ዓይነት እርምጃ እንዳንወስድ በማደረግ እርሳችንን እስከማዞር የሚደርሱ ፍሬ አልባ ከሆኑ ውይይቶች ራሳችንን እንድናርቅ” ይረዳናል ብለዋል።

የመንፈስ ቅዱስ ኃይል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በታይላንድ ለሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት የሚያደርጉትን ንግግር በቀጠለሉበት ወቅት ጨምረው እንደ ገለጹት ከሚሲዮናዊያኑ በፊት ቀድሞ የመጣው እና ከእነርሱ ጋር አብሮ የነበረው መንፈስ ቅዱስ መሆኑን በማስታወስ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል “ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ሚስዮናውያንን ማንኛውንም አገር፣ ህዝብ ፣ ባህል ወይም ሁኔታን እንዲጋፈጡ ደግፎዋቸዋል” ያሉት ቅዱስነታቸው “ቅዱስ ወንጌል ስጦታ በመሆኑ የተነሳ ለሁሉም መዳረስ ያለበት ቃል መሆኑን በመረዳታቸው የተነሳ ደፋሮች እና በወኔ የተሞሉ ነበሩ” ብለዋል። ተልእኮው ማለት የማሽተት ስሜትን ማዳበር ማለት ነው-“ተልእኮው የአባትነት እና የእናትነት ስሜት እና አሳቢነትን ይጠይቃል፣ በጎቹ የሚጠፉት እረኛው ሲዘናጋ እና የጠፉትን በጎች መፈለግ ሲያቆም ነው” ብለዋል።

የቤተክርስቲያን ተልዕኮ ምስክርነት መስጠት ነው!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በታይላንድ ለሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዓን ጳጳሳት የሚያደርጉትን ንግግር በቀጠሉበት ወቅት ቅዱስ ወንጌል ሕይወታችንን ይቀይር ዘንድ ልንፈቅድለት ይገባል፣ በጌታ ልንጸዳ ይገባል፣ የቤተክርስቲያን ተልዕኮ ምስክርነት መስጠት ነው፣ በየመንገች ላይ በግልጽ ለመራመድ በኃላፊነት ከተሰጡን ሕዝቦች ጋር ፊት ለፊት መገናኘትን ይጨምራል በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በታይላንድ የምትገኘው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በቁጥር አናሳ በመሆናቸው የተነሳ ተስፋ መቁረጥ እና ማዘን እንደ ማይኖርባቸው ገልጸው እውቅና የምናገኘው በቁጥራችን ብዛት ሳይሆን በምንሰጠው የቅዱስ ወንጌል ምስክርነት ነው ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጨምረው እንደ ገለጹት እኛ የተልዕኮው ኃላፊ አይደለንም፣ የተልዕኮዋችን ዋነኛው እና እውነተኛው ተዋናይ መንፈስ ቅዱስ ነው፣ በምንሄድባቸው ስፋራዎች ሁሉ መልካም ነገሮችን እንድንዘራ የሚረዳን በመንፈስ ቅዱስ አመካይነት ከተለወጥን በኋላ ነው፣ ተልእኮው “ለኢየሱስ ክርስቶስ እና ለሕዝቡ ያለንን ፍቅር መግለጽ ማለት ነው” ብለዋል።

አገልጋዮች አስተዳዳሪዎች አይደሉም

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በታይላንድ ለሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት የሚያደርጉትን ንግግር በቀጠለሉበት ወቅት “እኛ የዚህ ሕዝብ አካል ነን እንጂ ጌቶች ወይም አስተዳዳሪዎች እንድንሆን አልተመረጥንም” በማለት የተናገሩት ቅዱስነታቸው ይህ ማለት ደግሞ የምናገለግላቸውን ሰዎች በታላቅ ትዕግስት ማገዝ እና አብሮ መሆን ማለት ነው ያሉት ቅዱስነታቸው በትዕግስት እና በአክብሮት፣ በማደመጥ፣ ሰብዓዊ መብታቸውን በማክበር እነርሱ ሊያበረክቱ የሚችሉትን ሐዋርያዊ ተግባር ከግምት ማስገባት እና አሳታፊ መሆን እና ዋጋ መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳስታወቁት በእናተ አገር (ታይላድ) ቅዱስ ወንጌል እንዲስፋፋ ያደረጉ የሕዝባቸውን ቋንቋ እና ባህል ጠንቅቀው በሚያውቁ፣ ክርስቶስን ለመመስከር ከፍተኛ ቅንዓት በነበራቸው ምዕመናን እንደ ነበረም ጨምረው ገልጸዋል።

ጳጳሳት እና ካህናት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በታይላንድ ለሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዓን ጳጳሳት የሚያደርጉትን ንግግር በቀጠለሉበት ወቅት እንደ ገለጹት ብጹዕን ጳጳሳት ሁልጊዜ በሮቻቸውን ለካህናቶቻቸው እንዲከፍቱ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን “የአንድ ጳጳስ ቅርብ ጎሬቤት የሆነው ካህን ነው፣ በመሆኑም ለካህናቶቻችው ቅርብ ሁኑ፣ አዳምጡዋቸው፣ በማነኛውም ሁኔታ ውስጥ አግዙዋቸው፣ በተለይም ደግሞ የዲያቢሎስ ፈተና ከሆነው መካከል አንዱ እና ዋነኛው በሆነው ተስፋ በሚቆርጡበት ወቅት ወይም የግዴለሽነት መንፈስ በሚያጠቃቸው ወቅት ከካህናቶቻችሁ ጎን መሆን ይኖርባችኋል፣ ይህንን ስታደርጉ ደግሞ እንደ አንድ ዳኛ ሁናችሁ ሳይሆን ነገር ግን እንደ አንድ አባት በመሆን፣ እንደ አንድ አሰሪ ሁናችሁ ሳይሆን እንደ አንድ ታላቅ ወንድም ሁናችሁ ማከናወን ይኖርባችኋል” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በአካባቢያቸው ውስጥ የሚያጋጥሟቸውን እና ሊያጋጥማቸው የሚችሉትን   በርካታ ጉዳዮች እና ተግዳሮቶች አምነው በመቀበል ወደ ፊት መጓዝ እንደ ሚገባ ገልጸው “ብቻችንን እንደ ማንጓዝ እርግጠኞች በመሆን የወደፊቱን ጊዜ በተስፋ በመጠባበቅ ጌታ እዚያ እኛን እንደ ሚጠባበቀን እና እለት በእለት በምናደርገው መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ በምንሳተፈው በቅዱስ ቁርባን አማካይነት ጌታ ከእኛ ጋር አብሮ እንደ ሚጓዝ በማመን ሐዋርያዊ ተልዕኮዋችንን በእምነት እና በተስፋ ተሞልተን ማከናወናችንን መቀጠል ይኖርብናል ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
22 November 2019, 16:23