ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ  በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ ስድስተኛ የስብሰባ አዳራሻ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ ስድስተኛ የስብሰባ አዳራሻ  

“የድኾችም ተስፋ ለዘላለም መና ሆኖ አይቀርም”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የአገር ጎብኚዎች በኅዳር 07/2012 ዓ.ም. በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ መስረቱን አድርጎ የነበረ አስተንትኖ ካደረጉ በኃላ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ለእመቤታችን ለቅድስት  ደንግል ማርያም ከሚቀርቡ የመማጸኛ ጸሎቶች ውስጥ አንዱ የሆነው መልአኩ ገብርኤል ማርያምን ያበሰረበትን  ወቅት በማሰብ፣ የእግዚኣብሔር መልኣከ ማርያምን እንዳበሰራት እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት መጸነሱን በሚዘክረው የገብርኤል ብሥራት ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኋላ ለዓለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት እንደ ገለጹት በእለቱ “የድኾችም ተስፋ ለዘላለም መና ሆኖ አይቀርም” በሚል መሪ ሐሳብ ሦስተኛው ዓለም አቀፍ የድሆች ቀን መከበሩን የገለጹ ሲሆን እርሳቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲከበር ጥሪ ባደረጉት መሰረት በተለያዩ አገራት ውስጥ በሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቁምስናዎች እና ተቋማት ውስጥ ዓለም አቀፍ የድሆች ቀን ተከብሮ በማለፉ ምስጋና ማቅረባቸው የተገለጸ ሲሆን ድሆችን እና አቅመ ደካሞችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያየ ዓይነት ተነሳሽነቶች በመካሄድ ላይ በመሆናቸው ቅዱስነታቸው መደሰታቸውን ጨምረው ገልጸው እነዚህ መልካም የሆኑ እና ድሆችን ተጠቃሚ የሚያርጉ ተነሳሽነቶች ተጠናክረው ይቀጥሉ ዘንድ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል። ከመጪው ኅዳር 9-16/2012 ዓ.ም ድረስ  32ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ  ወደ ታይላንድ እና ጃፓን በቅደም ተከተል እንደ ሚያቀኑ የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው የተሳካ ይሆን ዘንድ ምዕመናን ጸሎት እንዲያደርጉላቸው ጠይቀዋል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ በእዚያ ስፍራ ሦስተኛውን ዓለም አቀፍ የድሆች ቀን ለማክበር የተገኙትን ሰዎች ሁሉ አመስግነው እና ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተው እንደ ተለመደው “እባካችሁን ለእኔ መጸለይ እንዳትዘነጉ” ካሉ በኋላ ሰላምታ አቅርበው መለየታቸውን ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

17 November 2019, 15:40