ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከታይላንድ የቡድሃ እመነት መሪ ጋር በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከታይላንድ የቡድሃ እመነት መሪ ጋር በተገናኙበት ወቅት  

በካቶሊክ እና በቡድሃ እምነት መካከል ያለውን ወንድማማችነት በውይይት ማጠናከር ያስፈልጋል።

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከኅዳር 09-16/2012 ዓ.ም ድረስ በታይላንድ እና በጃፓን በቅደም ተከተል የሚያደርጉትን 32ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በኅዳር 09/2012 ዓ.ም አመሻሹ ላይ መጀመራቸውን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በእዚህም መሰረት ቅዱስነታቸው በዛሬው እለት ማለትም በኅዳር 11/2012 ዓ.ም በታይላንድ ብሔራዊ ቤተመንግሥት ውስጥ ተገኝተው የአገሪቷን ጠቅላይ ሚንስትርን ጨምሮ በስፍራው ለተገኙ የአገሪቷ ባለስልጣናት እና የተለያዩ አገራት ልዑካን ንግግር ማደረጋቸውን መግለጻችን የሚታወስ ሲሆን ከእዚያም በመቀጠል ቅዱስነታቸው በታይላንድ የቡድሃ እምነት ቤተመቅደስ ውስጥ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

“እንኳን ደህና መጣህ በማለት ስላደረጉት ንግግር አመስገናለሁ” በማለት ከእርሳቸው በፊት የእንኳን ደህና መጣህ መልእክት ላስተላለፉት በታይላንድ የቡድሃ እምነት መሪ ላቀረቡት ንግግር ማስጋና በማቀረብ ንግግራቸውን የጀመሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራቸስኮስ በእዚህ በታይላንድ በማደርገው የመጀርያ ጉብኝት ላይ እነዚህን ውድ የሆኑ ሰዎችን ባሕርይ የሚያመለክቱ እሴቶች እና አስተምህሮዎች ምልክት ወደሆነው ብሔራዊ የቡዳ ቤተመቅደስ ውስጥ በመገኜቴ ከፍ ያለ ደስታ ተሰምቶኛል ብለዋል። “የታይላንድ ሕዝቦች ለሕይወት እና ለቀድሞ አባቶቻቸው ያላቸውን ታላቅ ክብር፣ በሚገልጽ መልኩ በአስተንትኖ የተሞላ የሕይወት ዘይቤ የመከተል ባሕል እና ጠንክሮ የመሥራት ባሕሪይ ከቡዳ እምነት ምንጭ የተቀዳ ባሕል ጠጥተዋል” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእዚህም የተነሳ በአስተሳሰብ፣ ጥንክሮ በመሥራት፣ በትጋት እና በስነስርዓት ላይ የተመሠረተ አኗኗር የሚመሩ ዜጎች እንዲፈጠሩ ማሳችሉን ገልጸው “እነዚህ ለየት ያሉ ባህሪዎች  በአገሪቷ በፈገግታ የተሞላ ሕዝብ እንዲኖር አስችሉዋል ብለዋል።

“ግንኙነታችን እና እያደረግን የምንገኘው ስብሰባ በቀዳሚነት የተጀመረው በመከባበር እና የእርስ በርስ መግባባት ጉዞ አንዱ አካል መሆኑን በመግለጽ” እንደ ሆነ በንግግራቸው ወቅት የገለጹት ቅዱስነታቸው  “ይህ ሐዋርያዊ ጉብኝት በእኛ መካከል ያለው የመከባበር ስሜት እንዲጨምር ብቻ ሳይሆን በማህበረሰቦቻችንም መካከል ያለው ወዳጅነት እንዲጨምር የሚያደርግ” ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደ ሆነ ጨምረው ገልጸዋል። በታይላንድ የቡዳ እምነት አስራ ሰባተኛው ጠቅላይ መሪ የነበሩት ሶንዴ ፎራ ዋራት፣ ታዋቂ ከሆኑ የቡድሃ መነኩሴዎች ቡድን ጋር በመሆን በቫቲካን በመገኘት በወቅቱ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከነበሩት ከጳውሎስ ስድስተኛ ጋር የተገናኙበት 50 አመታት ያህል ማለፋቸውን” በንግግራቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው በሃያማኖት ተቋማት መካከል በሃይማኖታዊ ባህሎቻችን መካከል ለሚደረገው የውይይት ሂደት በጣም አስፈላጊ የሆነ ነጥብ ጥሎ ማለፉን ገልጸው በእዚህም የተነሳ የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ዮሐንስ ሁለተኛ ይህንን የቡዳሃ ቤተመቀድስ እና የቡዳሃ ሐይማኖት ጠቅላይ መሪ ከእዚህ ቀደም እንዲጎኙ መንገዱን መክፈቱን ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

“እኔ ራሴ በቅርቡ ከዌት ፎል ቤተመቅደስ ከመጡ የቡዳ እምነት መነኩሴዎችን ጋር በቫቲካን በመገናኜቴ ክብር ተሰምቶኝ ነበር” በማለት ምግግራቸውን የቀጠሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “እነርሱም ከፓሊ ቋንቋ የተተረጎመ የጥንት የቡዳሃ እምነት በእጅ የተጻፈ መጽሐፍ ትርጉም በስጦታ መልክ አቅርበውልኝ ነበር፣ ይህ ስጦታ በቫቲካን ሙዚዬም ይገኛል ብለዋል። “እንደነዚህ ያሉት ትናንሽ እርምጃዎች በማህበረሰባችን ውስጥ ብቻ ሳይሆን በአለማችንም ውስጥም ሳይቀር ተገናኝቶ የመወያየት ባሕል ማዳበር እንደ ሚቻል ለመመስከር ይረዳሉ” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ልዩነቶቻችን እንዳሉ ቢሆንም አንዳችን ለሌላው አድናቆት እና መከባበር ሲኖረን፣ በግጭት የተነሳ በሥቃይ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች የሚያበረታታ እና የሚደግፍ ተስፋን በዓለም ውስጥ እንዲለመልም ማደረግ እንችላለን፣ እንደዚህ ያሉ አጋጣሚዎች የሐይማኖት ተቋማት ይበልጥ የተስፋ እና የወንድማማችነት መንፈስ ለዓለም መስጠት አስፈላጊ መሆኑን እንድንገነዘብ ያሳስቡናል” ብለዋል።

“በዚህ ረገድ እኔ ለዚህች አገር ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁኝ ምክንያቱም ከዛሬ አራት መቶ ሃምሳ አመት በፊት በታይላንድ የክርስትና እምነት በመጣበት ወቅት የካቶሊክ እምነት ተከታይ የነበሩ ሰዎች በቁጥር  አናሳ በነበሩበት ሁኔታ ውስጥ ቢኖሩም፣ ለብዙ ዓመታት ሐይማኖታቸውን በነጻነት ማራመድ ችለዋል፣ የቡዳሃ እምነት ተከታይ ከሆኑ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ጋር ተስማምተው ኖረዋል” ብለዋል።

“በዚህ የጋራ መተማመን እና የፍትህ አካሄድ ላይ የሕዝቦችን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ግልፅ እና አክብሮት የተሞላበት ውይይት ማደረጋቸውን እንዲቀጥሉ በግሌ ያለኝን ቁርጠኝነት እና እንዲሁም  የመላው የቤተክርስቲያኗ ድጋፍ እንደማይለያችሁ በድጋሚ ላረጋግጥላችሁ እፈልጋለሁ” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ወደ ጥልቅ መግባባት የሚወስዱትን አስተምህሮዎችን መለዋወጥ በመቻላችን ላመሰግናችሁ እወዳለሁ” ብለዋል። እንዲሁም በሁለቱም ባህሎች መካከል የጋራ አስተሳሰብ እንዲፈጠር እና አብሮ የመኖር ባሕል ለማደበር የሚደርገውን በምሁራን የተጋዘ አስተምህሮ የጋራ መግባባትን በመፍጠር በሕዝቦች መካከል ሰላም ይመጣ ዘንድ የሚያስችል ክንውን በመሆኑ የተነሳ ሊበረታታ የሚገባው ጉዳይ ነው ብለዋል።

በተመሳሳይ መልኩም “እኛ በየሃይማኖቶቻችን ተከታዮች መካከል ድሆችን እና በከፍተኛ ሁኔታ የተበዘበዘችውን የጋራ መኖሪያ ቤታችንን በተመለከተ አዲስ የበጎ አድራጎት ፕሮጄክቶችን መፍጠር እና ማሳደግ የሚችሉ አዳዲስ የበጎ አድራጎት ሥራዎች ልማት ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራትን አጠናክረን መቀጠል ይገባናል” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “በዚህ መንገድ ፣ እዚህም ሆነ በሌሎች የዓለም ክፍሎች የርህራሄ ፣ የደስታ እና የመተማመን ባህል እንዲመሰረት አስተዋጾ ማደረግ እንችላለን” ብለዋል። “ይህ ጉዞ በብዛት ፍሬ ማፍራቱን እንደሚቀጥል እርግጠኛ ነኝ፣
በድጋሚ ፣ ይህንን ስብሰባ እና ግንኙነት ላስተባበሩት የቡዳ እምነት ጠቅላይ መሪ ምስጋናዬን ለማቅረብ እፈልጋለሁ” ያሉት ቅዱስነታቸው “ለራስዎ ጤንነት እና ደህንነት እያንዳንዱ መለኮታዊ በረከት እንዲሰጥዎ እንዲሁም የቡድሃ እምነት ተከታዮችን በሰላምና በስምምነት ጎዳና ላይ እንዲራመዱ ለማደረግ እና ለመምራት የተጣለብዎን ከፍተኛ ኃላፊነት አጠናክረው ይቀጥሉ ዘንድ እፀልያለሁ” ካሉ በኋላ ምስጋና አቅርበው ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን ማጠናቀቃቸው ተገልጹዋል።

Photogallery

ርዕስ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በታይላድ ከቡድሃ እምነት መሪ በተገናኙበት ወቅት ወቅት
21 November 2019, 13:33