ፈልግ

ር. ሊ. ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከጃፓን ንጉሥ ናሩሂቶ ጋር፣ ር. ሊ. ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከጃፓን ንጉሥ ናሩሂቶ ጋር፣ 

ር. ሊ. ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከጃፓን ንጉሠ ነገሥት ናሩሂቶ ጋር መገናኘታቸው ተገለጸ።

የሩቅ ምስራቅ እስያ አገሮች በሆኑት ታይላንድ እና ጃፓን 32ኛ ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት ያደርጉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጃፓን ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ወቅት ከአገሪቱ ንጉሠ ነገሥት ናሩሂቶ ጋር መገናኘታቸውን የቫቲካን ዜና አገልግሎት ባልደረባ ማርኮ ጉዌራ የላከልን ዘገባ አመልክቷል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ንጉሠ ነገሥቱን በጎበኟቸው ወቅት ስጦታ ማበርከታቸውም ታውቋል። ቅዱስነታቸው ለጃፓኑ ንጉሠ ነገሥት ናሩሂቶ ያበረከቱት ስጦታ ሮማዊ የሰነ ጥበብ ሰው ፊሊፖ አኒቪቲ እጅ የተሳለ እና በሮም ከተማ ውስጥ የሚገኘውን “የቲቶ የቅስት መግቢያ በር እይታ” የሚገልጽ የቅብ ስዕል መሆኑ ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ከንጉሠ ነገሥት ናሩሂቶ በኩል ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው መሆኑን የንጉሣዊ ቤተመንግሥት መገናኛ እና የአገሪቱ መገናኛ ማዕከላት በስፋት የዘገቡ መሆናቸው ታውቋል። ንጉሠ ነገሥት ናሩሂቶ ቅዱስነታቸው በጃፓን ላደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ምስጋናቸውን አቅርበው በተለይም በሁለቱ የጃፓን ከተሞች፣ በሂሮሺማ እና በናጋሳኪ ያደረጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት በማስታወስ እንደዚሁም በጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር 2011 ዓ. ም. ጃፓንን ክፉኛ በጎዳት የመሬት መንቀጥቀጥ እና የባሕር መናወጥ አደጋ ወደ ተጠቁት ዜጎች መካከል ሄደው ሐዋርያዊ ጉብኝት ማድረጋቸውን በማስታወስ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበውላቸዋል።  

ንጉሠ ነገሥት ናሩሂቶ ወደ ዙፋን የወጡት በያዝነው የጎርጎሮሳዊያኑ ዓመት ግንቦት 1/2019 ዓ. ም. መሆኑ ስነገር በንጉሣዊ ቤተሰብ መካከል የካቶሊክ እምነትን የሚከተሉ መኖራቸው ታውቋል። የንጉሥ ናሩሂቶ እናት፣ ንግሥት ሚኪኮ ከካቶሊካዊ ቤተሰብ መወለዳቸው እና በሚኖሩበት አካባቢ በሚገኝ ካቶሊካዊ ትምህርት ቤት ገብተው መማራቸው እና በቶኪዮ ከተማ በሚገኝ በልበ ኢየሱስ ካቶሊካዊ ዩኒቨርሲቲ ገብተው ከፍተኛ ትምህርታቸውን የተከታተሉ መሆናቸው ታውቋል።

ይህን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
26 November 2019, 18:31