ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በታይላንድ ባንኮክ ካቴድራል መስዋዕተ ቅዳሴ ባደረጉበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በታይላንድ ባንኮክ ካቴድራል መስዋዕተ ቅዳሴ ባደረጉበት ወቅት  

ወጣቶች ከኢየሱስ ጋር ያላቸውን ወዳጅነት አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል!

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከኅዳር 09-16/2012 ዓ.ም ድረስ በታይላንድ እና በጃፓን በቅደም ተከተል የሚያደርጉትን 32ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በኅዳር 09/2012 ዓ.ም አመሻሹ ላይ መጀመራቸውን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በእዚህም መሰረት ቅዱስነታቸው በኅዳር 12/2012 ዓ.ም በርካታ ወጣቶች በተገኙበት በታይላንድ በሚገኘው ካቴድራል መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት ወጣቶች ሕይወታቸውን በእምነት ላይ በመትከል ከኢየሱስ ጋር ያላቸውን ወዳጅነት ማጠናከር ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጨምረው እንደ ገለጹት በታይላንድ የሚገኙ ወጣቶች ከኢየሱስ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት በመመሥረት በእምነት ላይ ሥር መሰረታቸውን በመትከል፣ ማዕለቃቸውን በእመንት ላይ በማሳረፍ በሕይወት ጉዞዋቸው እንደ መብራት ሆኖ የሚመራቸውን ብርሃን እዳይጠፋ የሚያደርገውን መብራታቸው ለራሳቸው እና ለሌሎች በሚገባ ማብራቱን እንዲቀጥል የሚያደርገውን ዘይት ከኢየሱስ ምንጭ መቅዳት እንደ ሚኖርባቸው ጨምረው ገልጸዋል።

“የእዚች ምድር መጻይ ጊዜ የሚወሰነው በእናንተ በወጣቶች እንደ ሆነ ጌታ በሚገባ እንደ ሚያወቅ” በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእዚህም የተነሳ ተልእኳችሁን ከዛሬው እለት አንስታቸው መወጣት ይኖርባችኋል፣ ይህንንም ማደረግ እንደ ምትችሉ እተማመንባችኋለሁ ብለዋል።

በእለቱ በተነበበው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ መሰረቱን ባደርገው ስብከት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት እግዚአብሔር የመንግሥቱ ተካፋይ እንድሆን ሁላችንንም እንደ ሚጠራን ገልጸው ብዙውን ጊዜ በምንወዳቸው ሰዎች ላይ መከራ እና መሰናክሎች ሲከሰቱ ፣ ወይም በራሳችን ድክመቶች ውስጥ በግልጽ ከሚታዩ ሁኔታዎች በመነሳት በሚፈጠሩ አለመታመን እና ምሬቶች ሕልሞቻችንን እንደ ሚያጨልሙ እና በልባችን ውስጥ ቀዝቃዛ የሆነ መንፈስ እንደ ሚፈጥሩ በቅዱስ ወንጌል ውስጥ እንደ ተጠቀሱት 5ቱ ሞኝ ልጃገረዶች በሕይወታችን ደስተኞች እንዳንሆን የሚያደርጉን እና ዘግይተን እንድንመጣ የሚያደርጉንን ነገሮች ከሕይወታችን ውስጥ ማስወገድ እንደ ሚገባ ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት ወጣቶች በጨለማ እና በችግር ውስጥ በሚገቡበት ወቅት ሁሉ የሕይወት ጨለማ በደማቁ እንዲበራ የሚያደርጋቸውን እሳት ይዘው በሕይወት ጉዞ እንዲቀጥሉ፣ ለጌታ ጥሪ እንዴት መልስ እንደሚሰጡ እና ጌታን በሁሉም አቅጣጫ ይዘው ወደፊት እንዲጓዙ የሚያደርገውን ዘይት እንዴት እንደሚያገኙ ለወጣቶች ምክር ሰጥተዋል።

የታላላቃቸውን ምክር ማዳመጥ

“ስለዚህ በቀድሞ አባቶቻቸው እምነት፣ በወላጆቻችሁ፣ በአያቶቻቸው እና በአስተማሪዎቻቸው ላይ ጠንካራ የሆነ ሥር መሰረት መገንባት ይጠበቅባችኋል” ያሉት ቅዱስነታቸው በተለይም ደግሞ የታላላቆቻችሁን ምክር እና ተግሳጽ ማዳመጥ ይገባችኋል ብለዋል። በህይወት ውስጥ በሚያጋጥማችው መከራ እና ሞት ውስጥ አባቶቻችሁ እንዴት ደስተኛ መሆን እንደ ሚቻል ያስተምሩዋችሁ ዘንድ የሕይወት ምስጢራቸውን እንዲያጋሩዋችሁ ልትጠይቋቸው ይገባል ብለዋል።

ሥር መሰረታችሁን በእምነት ላይ አድርጉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት ጨምረው እንደ ገለጹት ስር መሰረታችንን ጠንካራ በሆነ መሰረት ላይ ካልገነባን በስተቀር ማደግ አንችልም ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን በእዚህም መሰረት በሕይወት ሂደት ውስጥ የሚያጋጥመንን መሰናክሎች እና ፈተናዎች መሻገር የምንችለው ሕይወታችንን በእመንት ላይ መትከል ስንችል ብቻ ነው ብለዋል። ጠንካራ የሆነ የእምነት ስሜት ከሌለ ፣ ወጣቶች ዓለም በሚያሰማው ድምጽ ሊወሰዱ ይችላሉ፣ በእዚህም የተነሳ በዓለም ውስጥ ይባክናሉ፣  ባዶ ፣ ድካማ ፣ ብቸኛ እና እራሳቸውን ችለው መንቀሳቀስ የማይችሉ ሆነው እንዲሰማቸው የሚያደርጉ ስሜቶች ይፈጠራሉ፣ በእያንዳንዳችሁ ልብ ውስጥ የጌታ ብርሃን ያበራ ዘንድ የሕይወት ምንጭ የሆነውን ኢየሱስን አጥብቃችሁ መያዝ ይኖርባችኋል ብለዋል።

ከኢየሱስ ጋር ወዳጅነት ፍጠሩ

ከኢየሱስ ጋር ወዳጅነት መፍጠር እንደ ሚገባ በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በታይላንድ የሚኖሩ ወጣት ካቶሊኮች አዲስ ትውልድ እንደ መሆናቸው መጠን ፣ አዲስ ተስፋዎቻቸውን፣ ህልሞቻቸውን እና ጥያቄዎቻቸውን፣ ጥርጣሬዎቻቸውን፣ እርግጠኛ መሆናቸውን ሳይቀር ለክርስቶስ ማቅረብ እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። “ከኢየሱስ ጋር የዳበረ ጓደኝነት በመፍጠር በሕይወታቸው እና በዙሪያቸው የሚያጋጥሟቸውን የህይወት ፈተና ለመወጣት እንደ ሚያስችል የገለጹ ሲሆን በተጨማሪም በዙሪያቸው ከሚገኙ ጓደኞቻቸው እና ጎረቤቶችቻቸው ፣ የትምህርት ቤት ባልደረቦቸው እና በሥራ ቦታ ከሚገኙ ሰዎች ጋር ያላቸውን ወዳጅነት እና ግንኙነት ጠብቀው እንዲጓዙ እንደ ሚረዳቸው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማብቂያ ላይ ይህ 32ኛ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው እንዲሳካ ያደረጉትን ባለድርሻ አካልት በሙሉ ያመስገኑ ሲሆን በእዚህ ዝግጅት ላይ የተሳተፉትን በሙሉ እግዚኣብሔር ይባካቸው ዘንድ የተማጸኑ ሲሆን ወጣቶች ተስፋቸውን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ በማድረግ ወደ ፊት መጓዛቸውን እንዲቀጥሉ ምክረ ሐሳብ ካቀረቡ በኋላ ስብከታቸውን ማጠናቀቃቸው ከስፍራው ለቫቲካን ዜና ከደርሰው ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

22 November 2019, 16:19