ፈልግ

ር.ሊ.ጳ.ፍራንቸስኮስ በጃፓን ቶኪዮ መስዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ወቅት ር.ሊ.ጳ.ፍራንቸስኮስ በጃፓን ቶኪዮ መስዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ.ፍራንቸስኮስ “የክርስቲያን ማህበረሰብ በመስክ ላይ እንደ ሚገኝ አንድ ሆስፒታል ነው” አሉ!

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በጃፓን የሚያደርጉን ሐዋርያዊ ጉብኝት በመቀጠል በኅዳር 15/2019 ዓ.ም በቶኪዮ መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው ባስረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት ከኢየሱስ ሕይወት ጋር በሚስማማ መንገድ ላይ በመጓዝ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች በትክክል ማግኘት እንችላለን ብለዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያሰሙት ስብከት ኢየሱስ በተራራው ላይ ሆነ የሰበከውን ስብከት በተመለከተ በወቅቱ በተነበበው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ መሰረቱን ያደርገ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ይህ ኢየሱስ በተራራው ላይ ሆኖ የስበከው ስብከት እኛ የእግዚአብሔር ተወዳጅ ልጆች የመሆን ነፃነት ያገኘንበትን፣ ኢየሱስን እንድንከተለው የተጠራንበትን መንገድ ውበት የሚያመላክት ነው ብለዋል።

የእግዚአብሔር ልጆች የሚገጥማቸው መሰናክሎች

“ሆኖም የእግዚአብሔር ልጆች ለመሆን በነጻነት የምናደርገው ጉዞ በጭንቀት እና በፉክክር መንፈስ ሊዳከም እንደ ሚችል” በማመላከት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ምርታማ ለመሆን እና የነዋይ ፍቅርን በከፍተኛ ሁኔታ በመፈለግ ወደ ፊት መጓዝ ማንነታችንን ወይም ምን እንደሆንን ለመለካት ወይም ለመለየት ብቸኛው መመዘኛ ሊሆን እንደ ማይገባው የገለጹት ቅዱስነታቸው የእዚህ ዓይነቱ መመዘኛዎች በጣም አስፈላጊ ለሆኑ ጉዳዮች ግድየለሾች እንድንሆን እና በተቃራኒው ለሕይወታችን በጣም አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች አንዳንናፍቅ ቀስ በቀስ ከመስመር ሊያውጡን ስለሚችሉ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

በከፍተኛ ሁኔታ ባደገው በጃፓን ኢኮኖሚው ውስጥ ብዙ ሰዎች የህይወታቸውን ሕልውና እና የህይወታቸውን ትርጉም ሊገነዘቡ በማይችል መልኩ በማህበረሰቡ ውስጥ ብዙ ሰዎች ተገልለው እንደ ሚኖሩ የገለጹት ቅዱስነታቸው እርስ በርሳችን የምንረዳዳበት ሥፍራዎች እንዲሆን የታሰቡት የመኖሪያ ቤቶች፣ ትምህርት ቤት እና ማህበረሰቡ በአንድነት የሚሰበሰብብቻው ስፍራዎች ትርፍን ለማጋበስ በሚደረጉ ከፍተኛ ፉክክር የተነሳ እየተዘነጉ እንደ መጡ የገለጹት ቅዱስነታቸው  በዚህ ምክንያት ብዙዎች ሰላምና መረጋጋታቸውን እያጡ እንደ ሚገኙ ጨምረው ገልጸዋል።

ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች ማቀድ

ለዚህ መፍትሄው አሉ ቅዱስነታቸው ከተራራ ስብከቱ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ኢየሱስ የተጠቀማቸውን ቃላት ማስታወስ እንደ ሚገባ የገለጹት ሲሆን በእዚህም መሰረት “ስለ ኑሮህ አትጨነቅ… ስለ ነገም አትጨነቁ” የሚለውን የኢየሱስን ቃል ማስታወስ እንደ ሚገባ ገልጸው በሕይወት ሂደት ውስጥ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ነገሮች ቅድሚያ መስጠት እንደ ሚገባ ጨምረው ገልጸዋል። እነዚህ የኢየሱስ ቃላት በአከባቢያችን እየተከናወኑ የሚገኙትን ክስተቶች ችላ ብለን እንዳንቀመጥ፣ ወይም የዕለት ተዕለት ተግባሮቻችን እና ኃላፊነቶቻችንን ችላ እንድንላቸው የሚያበረታቱን ቃላት እንዳልሆኑ በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይልቁንም ተቀዳሚ የሆኑ ጉዳዮቻችን በቅድሚያ ማከናወንን የሚያመልክት ተግባር መሆኑን ገልጸው ይህም በቅድሚያ “የእግዚአብሔርን መንግሥት እና ጽድቁን ፈልጉ ፤ ከእዚያም ሌላው ነገር ሁሉ ይጨመርላችኋል” የሚለውን ቃል በተግባር በማዋል ሕይወታችንን ለእግዚአብሔር በቅድሚያ ማስገዛት ይኖርብናል ብለዋል።

ስለሆነም ጌታ የዕለት ተዕለት ውሳኔዎቻችንን እንድንገመግምና የሕይወታችንን ስኬት ፍለጋ ብቻ በመኳትን እንዳናባክናት፣ እንዲሁም በዕየለቱ ለምናወጣው ውጪ ሳይሆን ቅድሚያ መሰጠት የሚገባን ነገር ግን፣ በቅድሚያ ሕይወታችንን በመፈተሽ ለእግዚአብሔር የተገባ ሕይወት እንዲኖረን በርትቶ መሥራት የገባል ብለዋል ።

“በዚህ ዓለም ውስጥ አንድ ሰው ትርፍ ለማግኘት ወይም ትርፍን ብቻ የሚመለከቱ ተግብራትን እና የደስታ ምንጭ ነው ብለን ራሳችንን ብቻ መውደድ” ማስወገድ እንደ ሚገባ በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የእዚህ ዓይነቱ ተግባር ደግሞ በእውነቱ በከፍተኛ ሐዘን ውስጥ እንደ ሚከተን እና ባሪያዎች እንደ ሚያደርገን፣ እውነተኛ እድገትን የሚያደናቅፉ እና ተስማሚ የሆነ ሰብአዊው ማህበረሰብ ለመገንባት የሚደርገውን ጥረት የሚያደናቅፉ ናቸው ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት ተገልለው የሚገኙ ሰዎችን፣ ብቸኛ የሆኑ የማሕበርሰብ ክፍሎችን ወደ እኛ ለማምጣት እና ከእኛ ጋር እንዲገናኙ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው በዚህ ረገድ “ለራሳችን ሕይወት እና ከተፈጥሮ ጋር ያለንን ግንኙነት በማጠናከር ለፍጥረታት እንክብካቤ በማደረግ ከሌሎች ሰዎች ጋር በጋራ በመሆን ፍትህን እና ታማኝነትን ማስፈን ይኖርብናል” ብለዋል።

ስለሆነም የክርስቲያኑ ማህበረሰብ ሁሉንም ህይወት እንዲጠብቅና በጥበብ እና በድፍረቱ በምስጋና እና በርህራሄ ፣ በልግስና እና በየዋሕነት ማዳመጥ በሚታወቅ አኗኗር ዘይቤውን ጠብቆ መኖር ይሞክር ዘንድ ጥሪ ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን የክርስቲያን ማህበረሰብ አቅመ ደካማ የአካል ጉዳተኛ ፣ የውጭ አገር ዜጋ ፣ ስሕተት የፈጸመ አንድ ሰው፣ የታመመ፣ በማረሚያ ቤት ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን የክርስትናው ማህበረሰብ በተቻለ መጠን መንከባከብ እንደ ሚገባው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

በእዚህ ረገድ ኢየሱስ በመልካም ምሳሌው እንደ ሚመራቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው እሱ የሥጋ ደዌውን ፣ ዓይነ ስውሩን ፣ ሽባውን ፣ ፈሪሳዊውን ፣ ኃጢአተኛውን ፣ በመስቀል ላይ ከእርሱ ጋር ተሰቅሎ የነበረውን ወንጀኛ የተባለውን ሰው ሳይቀር ይቅር እንዳለ ሁሉ እኛም ይህንን አብነት መከተል ይኖርብናል ብለዋል።

ክርስቲያን ማህበረሰብ በመስክ ላይ እንደ ሚገኝ አንድ ሆስፒታል ነው

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት ቅዱስ ወንጌል በሕይወታችን መመስከር ማለት አንድ በመስክ ላይ የሚገኝ ሆስፒታል እንደ መሆን ማለት ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የሰዎችን ቁስሎች ለመፈወስ እና ሁል ጊዜም የእርቅ እና የይቅርታ መንገድ እንድንከተል የሚያስገድድ ተግባር በመሆኑ የተነሳ ነው ብለዋል። እንደ ክርስቲያን በእያንዳንዱ ግለሰብ እና ሁኔታ ላይ አስተያየት መስተት የምንችለው በሚያስያው የፍርኅራሄ ተግባር ላይ መሰረቱን ባደርገ መልኩ ነው ብለው፣ በዚህ መንገድ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሁሉንም ህይወት የሚንከባከብ እና የምንጠብቅ ሰዎች በመሆን በማኅበርሰቡ ውስጥ እርሾ ሆነን መቀጠል እንችላለን ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 

Photogallery

ር.ሊ.ጳ.ፍራንቸስኮስ በጃፓን ቶኪዮ መስዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ወቅት
25 November 2019, 16:49