ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በአልባኒያ የመሬት መንቀጥቀጥ ለተጎዱ ወገኖች ሀዘናቸውን ገለጹ! ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በአልባኒያ የመሬት መንቀጥቀጥ ለተጎዱ ወገኖች ሀዘናቸውን ገለጹ! 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በአልባኒያ የመሬት መንቀጥቀጥ ለተጎዱ ወገኖች ሀዘናቸውን ገለጹ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅርቡ በአልባኒያ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ሀዘናቸውን ገለጹ። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስን በመወከል ይህንን የሐዘን መግለጫ መልእክት ያስተላለፉት በቫቲካን የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ፕትሮ ፓሮሊን እንደ ሆኑ ተያይዞ ከደርሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ፕትሮ ፓሮሊን በቴሌግራም መልእክት ባስተላለፉበት ወቅት ባለፈው ማክሰኞ ኅዳር 16/2012 ዓ.ም በአልባኒያ ተከስቶ በነበረው የመሬት መንቀጥቀት አደጋ ምክንያት በሕይወት እና በንብረት ላይ በደርሰው አደጋ ቅዱስነታቸው ማዘናቸውን ጨምረው ገልጸዋል። የአልባኒያ ፕሬዚዳንት ለሆኑት ኢሊሪ ሜታ በተደረገው የቴሌግራም መልእክት የቫቲካን ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ፕቶሮ ፓሮሊን በበኩላቸው እንደ ገለጹት ቅዱስነታቸው በአደጋው ለሞቱት ሰዎች ነፍስ እየፀለዩ መሆኑን ገልፀው “በአደጋው ለተጎዱ እና ለዘመድ አዝማዶቻቸው ሁሉ” በጸሎታቸው ከእነርሱ ጋር እንደ ሚሆኑ ያረጋገጡላቸው ሲሆን  እንዲሁም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በአደጋው ለተጎዱ ሰዎች እርዳታ በመስጠት ላይ ለሚገኙ “የአስቸኳይ ጊዜ ሰራተኞች ፀሎት እንዲደረግላቸው” መጠየቃቸውም ተዘግቡዋል።

ባልፈው ማክሰኞ ኅዳር 16/2012 ዓ.ም በአልባንያ ዋና ከተማ በቲራና በደርሰው ከፍተኛ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የ21 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈ እና በርካታ ሕንጻዎች እንዲደረመሱ ያደረገ ክስተት እንደ ነበረ የተዘገበ ሲሆን ብዙሃኑን ደግሞ በፍርስራሾች ውስጥ እንዲቀበሩ ያደረገ ክስተ እንደ ነበረ ከደርሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

29 November 2019, 14:21