ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሳናታ ማርያ ማጆሬ ባዚሊካ ውስጥ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሳናታ ማርያ ማጆሬ ባዚሊካ ውስጥ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ 32ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ቫቲካን ተመለሱ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከኅዳር 09-16/2012 ዓ.ም ድረስ በታይላንድ እና በጃፓን በቅደም ተከተል የሚያደርጉትን 32ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በትልንትናው እለት ማለትም በኅዳር 16/2012 ዓ.ም አጠናቀው ወደ ቫቲካን መመለሳቸው ተገልጹዋል። ቅዱስነታቸው ማንኛውንም ሐዋሪያዊ ጉብኝት ከመጀመራቸው በፊት እና ማነኛውንም ሐዋርያዊ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ሮም ከተማ በሚመለሱበት ወቅት በሮም ከተማ እንብርት ላይ በሚገኘው በማሪያም ስም ከተሰየሙ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ በአውሮፓ አህጉር በትልቅነቱ እና በጥንታዊነቱ በሚታወቀው ሳንታ ማሪያ ማጆሬ በመባል በሚታወቀው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተገኝተው፣ በዚያው በሳናታ ማርያ ማጆሬ ባዚሊካ ውስጥ በሚገኘው ባላቲን ቋንቋ “Salus Populi Romani” በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም “የሮም ከተማ ሕዝቦች አዳኝ ወይም ጠባቂ” በመባል በሚታወቀው እና በአብዛኞቹ  የሮም ከተማ ነዋሪዎች ከፍተኛ ክብር የሚሰጠው፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ሕጻኑን ኢየሱስን በእጆቹዋ ላይ አቅፋ መያዙዋን የሚያሳየው ምስል ስር በመገኘት ይህ ከኅዳር 09-16/2012 ዓ.ም ድረስ በታይላንድ እና በጃፓን በቅደም ተከተል የሚያደርጉትን 32ኛው ሐዋርያዊ ጉብኝት በተሳካ መልኩ በሰላም እንዲጠናቀቅ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስላደርገችላቸው ጥበቃ በስፍራው ተገኝተው ምስጋና ማቅረባቸው ተገልጹዋል።

27 November 2019, 15:57