ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የኢስቶኒያ ፕሬዚዳንት ከሆኑት ኬርስ ካሊጁላድ በቫቲካን ተገናኙ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የኢስቶኒያ ፕሬዚዳንት ከሆኑት ኬርስ ካሊጁላድ በቫቲካን ተገናኙ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የኢስቶኒያ ፕሬዚዳንት ከሆኑት ኬርስ ካሊጁላድ በቫቲካን ተገናኙ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስቸስኮስ የኢስቶኒያ ፌደራላዊ ሪፖብሊክ ፕሬዝዳንት ከሆኑት ኬርስ ካሊጁላድ በቫቲካን ተቀብለው ማነጋገራቸው ተገለጸ። በኅዳር 18/2012 ዓ.ም የኢስቶኒያ ፌደራላዊ ሪፖብሊክ ፕሬዝዳንት ከሆኑት ኬርስ ካሊጁላድ በቫቲካን ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በተገናኙበት ወቅት በሁለቱ አገራት ማለትም በቫቲካን እና በኢስቶኒያ መካከል ያለው መልካም ግንኙነት ተጠናክሮ የሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸው የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ ባደረጉት ንግግር አሁን በሁለቱ አገራት መካከል ያለው መልካም ግንኙነት ተጠናክሮ የሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸው ተገልጹዋል።  

የኢስቶኒያ ፌደራላዊ ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት ኬርስ ካሊጁላድ ከቅዱስነታቸው ጋር ተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራነቸስኮስ ኢስቶኒያን ይጎበኙ ዘንድ ጥሪ ማቅረባቸው የተገለጸ ሲሆን ትምህርት ፣ ማህበራዊ ፍትህ እና የተፈጥሮ ጥበቃን በተመለከተ በጋራ የመግባቢያ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ተገልጹዋል።

በመጨረሻም ስለሰላም፣ ደኅንነት፣ ለግጭቶች እልባት መስጠት በመሳሰሉ አከባቢያዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ የተወያዩ ሲሆን በተጨማሪም የዩክሬን ሁኔታ እንዲሁም የአውሮፓን የወደፊት ተግዳሮት ጨምሮ በርካታ የአካባቢያዊ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ላይ መወያየታቸው ተገልጹዋል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!

Photogallery

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የኢስቶኒያ ፕሬዚዳንት ከሆኑት ኬርስ ካሊጁላድ በቫቲካን ተገናኙ
29 November 2019, 14:14