ፈልግ

ባለትዳሮች በስብከተ ወንጌል መስፋፋት ሂደት ውስጥ ተካፋይ እንዲሆኑ እንጸልይላቸው !

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር ረቡዕ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ወይም በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ የስብሰባ አዳራሽ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የአገር ጎብኚዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። በእዚህም መሰረት ቅዱስነታቸው በኅዳር 03/2012 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ከእዚህ ቀደም የመጽሐፍ ቅዱስ አንዱ ክፍል በሆነው የሐዋርያት ሥራ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ተንተርሰው ሲያደርጉት የነበረው አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በእዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በኅዳር 03/2012 ዓ.ም ባደረጉት የክፍል ዐስራ ስድስት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ትኩረቱን ያደረገው  ሐዋርያው ጳውሎስ በቆሮንቶስ በነበረው ቆይታ ላይ መሰረቱን ያደረገ ሲሆን « ጵርስቅላና አቂላም ሐዋርያው ጳውሎስን ወደ ቤታቸው ወሰዱት » በሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ መሰረቱን ያደርገ እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “ባለትዳሮች በስብከተ ወንጌል መስፋፋት ሂደት ውስጥ ተካፋይ መሆን ይችሉ ዘንድ አብ መንፈሱን እንዲያዘንብባቸው እንጸልይላቸው » ማለታቸው ተገልጹዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በኅዳር 03/2012 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያደረጉትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ እንደ ሚተርከው ጳውሎስ ፣ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በአቴንስ ከቆየ በኋላ ከእዚያ ተልይቶ መሄዱ የሚታወቅ ሲሆን ዲዮኒስዮስ እና ደማሪስ የተባሉ ሰዎች የአማኞችን ሕብረት መቀላቀላቸው እና እነዚህን የመሳሰሉ ፍሬዎችን በማፍራት በዓለም ውስጥ ቅዱስ ወንጌል መስፋፋቱን እንዲቀጥል አደረገ። በወቅቱ በአከባቢው ሁለት አስፈላጊ ወደቦች መኖራቸው ምስጋና ይግባውና የንግድ እና ከተለያዩ ዓለማት የተውጣጡ ሕዝቦች የሚኖሩባት የሮማዊያን ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው በቆሮንቶስ የሚስዮናዊ ጉዞው እንዲጀር ማድረጉ አዲስ ደረጃ ላይ እንዲደርስ አድርጎታል።

በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 18 ላይ እንደምናነበው፣ ጳውሎስ ንጉሥ ቀላውዴዎስ አይሁዳውያን በሙሉ ከሮም እዲባረሩ  ካዘዘ በኋላ ይህንን ትዕዛዝ ተከትሎ ከተባረሩት ሰዎች መካከል አንዱ በሆነው በጵርስቅላና ሚስቱ በአቂላ ጋባዥነት ወደ ቤታቸው ይሄዳል። እነዚህ ባለትዳሮች የባዕድ አገር የሆኑ ሰዎችን ሁኔታ በሚገባ የሚያውቁ እና እነርሱንም ለማስተናገድ በሚችላ መልኩ ቦታ መስጠት የሚችል ችሎታ ያላቸው ሰዎች የነበሩ ሲሆን በተጨማሪም በእግዚአብሔር ላይ ሙሉ እምነት ያላቸው እና ለሌሎች ለጋስ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ። ይህ የእነሱ የእንግዳ ተቀባይነት ከፍተኛ ስሜት ክርስቲያናዊ በሆነ መልኩ የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ እንዲማሩ የረዳቸው ሲሆን  (ሮም 12:13 ፤ ዕብ 13:2 ይመልከቱ) በእዚህም መሰረት ሐዋርያው ጳውሎስን ለመቀበል የቤታቸውን በሮች ይከፍታሉ። ስለሆነም እነርሱ በቤታቸው የተቀበሉት ወንጌላዊውን ብቻ ሳይሆን ወንጌላዊው ያመጣውን አዋጅ ጭምር ይቀበላሉ፣ ይኸውም “የሚያምኑትን ሰዎች ሁሉ ማዳን የሚችል የእግዚአብሔር ኃይል የሆነው የክርስቶስ ወንጌል” (ሮሜ 1 16) ነው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ቤታቸው ልብን በሚያድስ “ሕያው” ቃል መዓዛ ተሞልቷል (ዕብ. 4 12)።

አቂላ እና ጵርስቅላ የባለሙያ ሥራ የነበረውን እና ጳውሎስ እራሱ ያከናውን በነበረው የድንኳን ግንባታ ሥራ ላይ ተካፋይ ይሆናሉ። ጳውሎስ በእውነቱ የጉልበት ሥራን ከፍተኛ የሆነ ጫና ፈጥሮበት የነበረ ሲሆን በእዚህም የተነሳ ለክርስትና እምነት ምስክርነት የሚሆን ለየት ያለ ጊዜ ይሰጥ ነበር (1 ቆሮ 4፡ 12 ይመልከቱ)፣ በጉልበት ሥራ የተሰማራበት ዋነኛው ምክንያት ደግሞ ለሌሎች ሸክም ሳይሆን እራሱን ጠብቆ ለማቆየት የሚያስችል ትክክለኛ መንገድ በመሆኑ የተነሳ ነበር (1 ተሰ. 2፡9 ፤ 2 ተሰ 3: 8 ይመልከቱ)። ቅዱስ ኦሪጂን እንደ ሚለው ሐዋርያው ጳውሎስ “በመሬት ላይ የሚሰፍር ድንኳን ከመገንባት አንስቶ ወደ የሰማይ ድንኳን መገንባት ይሸጋገራል […] ለእያንዳንዱ ሰው የመዳንን መንገድ ያስተምራል” ይለናል። ስለዚህ ድንኳን በሚሠራበት በእንግድነት በተቀበሉት በአቂላ እና ጵርስቅላ የእንግዳ ማረፊያ ቤት ውስጥ  ሐዋርያው በቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን መካከል የእግዚአብሔርን “ድንኳን” ማቀድ እና መትከል ይጀምራል (1 ቆሮ 3፡10 ይመልከቱ)።

በቆሮንቶስ የነበረው የአቂላ እና ጵርስቅላ ቤት ለሐዋርያው ብቻ ሳይሆን በክርስቶስ ላመኑት ወንድሞችና እህቶችም በሩን ይከፍታል።  በእርግጥ ፣ ሐዋርያው ጳውሎስ “በቤታቸው ከሚሰበሰብ ማህበረሰብ” (1 ቆሮ 16፡19) ጋር መነጋገር የሚችል ሲሆን ፣ ያ ስፍራ ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል የሚሰማበት እና የቅዱስ ቁርባን ስነ-ስረዓት የሚፈጸምበት ቤተ ክርስቲያን ሊባል ይችላል።

በቆሮንቶስ አንድ ዓመት ተኩል ያህል ከቆየ በኋላ ከአቂላንና ጵርስቅላ ጋር በመሆን ቆሮንጦስን ለቆ ወደ ኤፌሶን ሄደ። እዚያም ቢሆን ቤታቸው ትምህርተ ክርስቶስ የሚሰጥበት ሥፍራ ይሆናል (ሐዋ. 18:26 ይመልከቱ)። በመጨረሻም ፣ ሁለቱ ባለትዳሮች ወደ ሮም ይመለሳሉ፣ ሐዋርያው ለሮም ሰዎች በጻፈው መልእክቱ “በክርስቶስ ኢየሱስ አብረውኝ ለሚያገለግሉት ለጵርስቅላና ለአቂላ ሰላምታ አቅርቡልኝ። እነርሱም ለእኔ ሲሉ ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው ሰጡ፤ እኔ ብቻ ሳልሆን የአሕዛብ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ያመሰግኗቸዋል » (ሮም 16፡3-4) በማለት ስለ እነርሱ አስደናቂ በሆነ መልኩ ያለውን ክብር ገልጹዋል።

ሐዋርያው ጳውሎስ ከነበሩት ብዙ ተባባሪዎች መካከል አቂላ እና ጵርስቅላ ብቅ ብለው “ለመላው የክርስቲያን ማኅበረሰብ በኃላፊነት  አገልግሎት የተሰጡ የባለትዳሮች ሕይወት ”ምሳሌዎች” እንደነበሩ እና ለእመነት እና ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋት ሂደት ውስጥ ላለው ቁርጠኝነት ምስጋና ይግባውና ስብከተ ወንጌል እስከ እኛ ጊዜ ድረስ እንዲዳረስ ያደረጉ እንደ እነርሱ ያሉ ብዙ ሰዎች እንዳሉ ያስታውሱናል። በእርግጥ “በሰዎች አገር ውስጥ ሥር ለመስደድ፣ በጥልቀት ለማዳበር ፣ የእነዚያ ቤተሰቦች ፣ የእነዚህ ባለትዳሮች ፣ የእነዚህ ክርስቲያን ማህበረሰቦች ፣ ለእምነቱ እድገት እንደ መልካም መሬት ሆነው ያገለገለሉ ታማኝ ሰዎች አስፈላጊ ናቸው።

የትዳር ጓደኞች “እውነተኛ” ሕያው የሆነ ቅርፅ ያለው ሕይወት እንዲይዙ እና እንዲመርጡ፣ በሁሉም በክርስትና ወግ ማዕረግ በተጋቡ ባለትዳሮች ላይ መንፈሱን እንዲያፈስ፣ የአቂላ እና የጵርስቅላ ምሳሌ በመከተል ልባቸውንና የቤቶቻቸውን በሮች ለክርስቶስ እና ለወንድሞቻቸው እንዴት መክፈት እንደ ሚችሉ እና ቤቶቻቸውን ወደ አብያተ-ክርስቲያንነት እንዲቀይሩ እና በእምነት፣ በተስፋ እና በልግስና የኖሩት ሕይወት ጸጋ እንዲያስገኝላቸው እንዲረዳቸው አብ እንዲያግዛቸው እንለምነው።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!

Photogallery

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ
13 November 2019, 15:00