ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “የራስ ወዳድነት መንፈስ ባለበት ሥፍራ ሁሉ እውነተኛ ሕይወት የለም” አሉ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጥቅምት 30/2012 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የአገር ጎብኚዎች ያደረጉት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ በእለቱ ከሉቃስ ወንጌል 20፡27-38 ላይ ተወስዶ በተነበበውና ትንሣኤ ሙታንና ጋብቻን በተመለከተ ሰዱቃዊያን ለኢየሱስ ጥያቄ ማቅረባቸውን በሚያመለክተው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ መሰረቱን  ያደረገ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባደረጉት አስተንትኖ እንደ ገለጹት “የራስ ወዳድነት መንፈስ ባለበት ሥፍራ ሁሉ እውነተኛ ሕይወት የለም” ማለታቸው ተገልጹዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጥቅምት 30/2012 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያደረጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን ሰንበታችሁ!

የዛሬ ቅዱስ ወንጌል (ሉቃ 20 27-38 ይመልከቱ) የሙታን ትንሣኤን በተመለከተ ኢየሱስ የሰጠውን አስደናቂ ትምህርት ያቀርብልናል። በትንሣኤ የማያምኑ አንዳንድ ሰዱቃዊያን ኢየሱስን ሆን ብለው ለማጣቃት በማሰብ ተንኳሽ የሆነ ጥያቄ ያቀርቡለታል። አንዱ በሞት ሲለይ ሌሎቹ ሰባቱ ወንድማማቾች በየተራ ያገቧት ሴት በሙታን ትንሳኤ ወቅት የማን ሚስት ትሆናለች? በማለት ጥያቄ ያቀርቡለታል። ኢየሱስ ግን ወጥመዳቸው ውስጥ አልገባም፣ እናም በመጨረሻው ከሞት የሚነሱት “የሚመጣውን ዓለምና የሙታንን ትንሣኤ ማግኘት የሚገባቸው ግን አያገቡም፤ አይጋቡም፤ እንደ መላእክትም ስለሆኑ ከዚያ በኋላ አይሞቱም፤ የትንሣኤ ልጆች ስለ ሆኑም የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው” (ሉቃስ 20፡35-36) በማለት ኢየሱስ ይመልስላቸዋል። 

በዚህ መላሽ ኢየሱስ በመጀመሪያ ጥይቄ ላቀረቡለት ሰዎች እና ለእኛም ሳይቀር አሁን የምንኖርበት ይህ ምድራዊ ሕይወት የሰው ልጅ ሕይወት የሚለካበት ብቸኛው ምንገድ እንዳልሆነ፣ እኛ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን በግልጽ የሚያሳይ፣ ከእዚህ ከምዳራዊ ሕይወት የተለየ ሞት የሌለበት ሕይወት እንዳለ እንድንገነዘብ በማደረግ ከሞተ በኋላ ስላለው ሕይወት ቀላል እና ግልፅ ማብራሪይ በመስጠት የኢየሱስን ቃል ለመስማት የሚያስችለን ትልቅ ማበረታቻ እና ተስፋ ይሰጣል። ስለ አጽናፈ ዓለሙ ያለን እውቀት እጅግ የበዛ እንዲሆን የሚያደርገን እና በእዚህ ምድር ላይ ያለን ጥበብ በጣም አናስ እንደ ሆነም ያሳየናል።

ይህ ኢየሱስ የገለጸው የትንሣኤ ሕይወት ሙሉ በሙሉ የተመሰረተው የሕይወት አምላክ በሆነው እግዚአብሔር ላይ ባለን ታማኝነት ላይ ነው። በእውነቱ ፣ ከሰዱቃውያን ጥያቄ በስተጀርባ ጥልቅ የሆነ የተደበቀ ምስጢር አለ፣ የሰባት ባሎች ሚስት ስለነበረቺው ሴት ታሪክ ብቻ ሣይሆን፣ ሕይወቷ የማን እንደ ሆነ የሚያመለክት ጥያቄ አቅፎ ይዙዋል። ይህ ሁሉንም የሰው ልጆች፣ እኛንም ጨምሮ የሚነካ የጥርጣሬ ስሜት ሲሆን ከዚህ ምጻተኞች ከሆንበት ምድራዊ ሕይወት ጉዞ በኋላ፣ ሕይወታችን ምን ይሆናል? ለሞት ነው ወይስ እንዲያው በከንቱ ነው የሚቀረው የሚለውን ጣያቄ ያስነሳል።

ሕይወት እኛን የሚወደን እና ለእኛ ብዙ የሚያስብልን ከእግዚአብሔር የሚገኝ ስጦታ ነው ፣ ኢየሱስም “የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ’ በማለት መልስ ይሰጣል። “ለእርሱ ሕያዋን ስለሆኑ እርሱ የሕያዋን አምላክ እንጂ የሙታን አይ ደለም።” በማለት ይመልሳል።

ሕይወት የሚጸናው እና የሚመራው ህብረት፣ ትስስር እና የወንድማማችነት መንፈስ ባለበት ሕይወት ውስጥ ነው፣ በእውነተኛ ግንኙነቶች እና በታማኝነት ማሰሪያ ላይ ሲገነባ ሕይወት ከሞት የበለጠ ይሆናል።  በተቃራኒው አንድ ሰው የእራሱን ፍላጎቶች ብቻ በማራምመድ በራስ ወዳድ መንፈስ በሚራመድበት ሥፍር እና ራሱን እንደ አንድ ደሴት በመቁጠር ራሱን ከሌልቾ አግልሎ የሚኖር ከሆነ በእርሱ ውስጥ ሕይወት ሳይሆን ሞት ነው ያለው ማለት ይችላል። ራስ ወዳድነት ሞት ነው።  ለራሴ ብቻ የምኖር ከሆነ በልቤ ውስጥ ሞትን እዘራለሁ ማለት ነው።

በጸሎተ ሐይማኖት በመጨረሻው ክፍል ውስጥ የሚገኘውን “በሙታን ትንሳኤ እና በዘለዓለም ሕይወት አምናለሁ” የሚለውን ጸሎት በእየቀኑ በሕይወታችን ውስጥ በማሰብ መኖር እንችል ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትርዳን።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
10 November 2019, 11:17