ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ጸሎትን አስመልክተው የጻፉት መጽሐፍ፣ ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ጸሎትን አስመልክተው የጻፉት መጽሐፍ፣  

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የክርስቲያኖች ጸሎት የቤተክርስቲያን ሕይወት መሆኑን አስታወቁ።

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በቅርቡ ለንባብ ባበቁት መጽሐፋቸው የክርስቲያኖች ጸሎት በክርስትና ሕይወት ውስጥ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ቅዱስነታቸው አስታውቀዋል። “ጸሎት” የሚል ርዕስ የተሰጠውን መጽሐፍ ያሳተመው ድርጅት “አቬኒር” የተባለ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጋዜጣ አዘጋጅ ክፍል መሆኑ ታውቋል። በጀርመን፣ ፍራንክፈርት ከተማ ሐሙስ ጥቅምት 13/2012 ዓ. ም. በተዘጋጀ ዓለም አቀፍ መጽሐፍት ትርኢት ላይ የቀረበው የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት መጽሐፍ፣ ቅዱስነታቸው በሚለው ጸሎት ላይ፣ በተለይም “አባታችን ሆይ !” በሚለው ሰሎት ላይ ያደረጉትን ተከከታታይ አስተንትኖ እና ንግግሮችን ያሰባሰበ መሆኑ ታውቋል።  መጽሐፉ በመግቢያው የሞስኮ ፓትርያርክ፣ የብጹዕ ወቅዱስ ኪሪል ሃሳብ ያካተተ መሆኑ ተገጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በመጽሐፋቸው ውስጥ ምስጢረ ጥምቀት የአዲስ ሕይወት መጀመሪያን እንደ ሆነ ያስረዱት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ በምስጢረ ጥምቀት የሚገኝ አዲስ ሕይወት ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ ነው ሲያስረዱ፣ ሥራን በመያዝ ሕይወትን መቀየር ቤተሰብን ማገዝ መጀመር ውይም የሚኖሩበትን አካባቢን ቀይሮ ወደ ሌላ አካባቢ መሄድ ሳይሆን፣ በእርግጥ በዚህ መልክ በኑሮ መካከል አነሰ በዛም ለውጦች ሊታዩ እንደሚችሉ ገልጸው ይህ ማለት ደግሞ ከዚህ በፊት የነበረ ሕይወት በተሻለ መንገድ ቀጣይነትን አገኘ እንጂ ምንም አዲስ ሕይወት እንዳልታየ አስረድተዋል። ጠቅላላ ውስጣዊም ሆነ ውጫዊ አስተሳሰብ እና ስሜት የሚለወጥበት፣ ከዚህ በፊት ያቀድናቸው እና ያሰብናቸው በሙሉ እንደ ምኞታችን ሆነው ሲገኙ ከቀድሞ ይልቅ ወደ ተሻለ ሕይወት መሸጋገርን፣ ይህም ደስታን እና እርካታን ማስገኘቱን ብቻ የሚያመለክት እንጂ አሁንም ቢሆን የሚፈለገውን ለውጥ የመጣ አለመሆኑን አስረድተዋል።  

ከዚህ በተለየ መልኩ በምስጢረ ጥምቀት የሚገኝ ወይም የሚጀመር አዲስ ሕይወት አዲስነቱ የሚገለጠው ከቀድሞ ሕይወት የተለየ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያው ጳውሎስ በመልዕክቶቹ እንደሚያስረዳን፣ በዮሐ. 13:34 “አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ ይኸውም እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው፤ እንግዲህ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ” የሚል ትዕዛዝ፣ በሌሎች ወንጌላትም እንዲሁም በዮሐ. ራእይ ላይ በምዕ. 5:9 ላይ የተገለጸውን ያስታወሱት ቅዱስነታቸው በምስጢረ ጥምቀት የሚገኘውን አዲስ ሕይወት ከሌላ ሕይወት ጋር ማወዳደር የማይቻል መሆኑን በመጽሐፋቸው ውስጥ አስረድተዋል። ሞትን እና ሕይወትን ማወዳደር፣ የሕጻንነትን እና ካደግን በኋላ የሚኖረንን ሕይወት ማወዳደር ይቻላል ወይ ያሉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ሲል የተሰቃየው፣ የሞተው እና ከሞትም የተነሳው ዓለማዊ ሕይወታችን የበለጠ የተመቻቸ እንዲሆን፣ ረጅም ዕድሜ እንዲኖረን፣ ችግር የተወገደበት የተደላደለ ሕይወትን መኖር እንድንችል ለማድረግ ሳይሆን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም የመጣው የተትረፈረፈ ሕይወት እንዲኖረን ለማድረግ ነው ብለዋል (ዮሐ.10፡10)።    

እግዚአብሔር አባታችን በምስጢረ ጥምቀት በኩል የሚሰጠን አዲስ ሕይወት የተትረፈረፈ እንደሆነ ያስረዱት ቅዱስነታቸው ቀድሞ ከምንኖርበት ሕይወት የተለየ እና አዲስ መሆኑ የሚታወቀው ከእግዚአብሔር ዘንድ በመሆኑ ነው ብለዋል። በእግዚአብሔር አብ፣ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ እና በመንፈስ ቅዱስ ፍቅር ተካፋዮች እንድንሆን በማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች እና ለመላው ፍጥረት የሚሰጠን የአዲስ ሕይወት ስጦታ ነው ብለው ከዘመናት ጀምሮ እኛ ክርስቲያኖች ይህ ወደር የማይገኝለት የኢየሱስ ክርስቶስ የአዲስ ሕይወት ስጦታ በግልጽ የሚታይበትን መንገድ ስንፈልግ ኖረናል ብለዋል። በቁጥርም በርካቶች ነን፣ አንድም ነን፣ የአንድ ቤተክርስቲያን ልጆችም ነን ብለዋል። በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር የተገነባው አንድነት፣ በመካከላችን ፍቅርን እና አንድነትን በማሳደግ ወደጅነታችን ያጠናክራል ብለዋል። “እውነተኛ አምላክ የሆንኸውን አንተንና የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት” (ዮሐ. 17:3)። እውነተኛ አዲስ ሕይወት የሚገኘው ከእግዚአብሔር ጋር ስንገናኝ እና እርሱን ስናውቅ መሆኑን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አስረድተዋል።

ይህን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
26 October 2019, 16:44