ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ሕይወት ተልዕኮ እና ስጦታ ነው” አሉ

ዓለም አቀፋዊት በሆነቺው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በጥቅምት 09/2012 ዓ.ም በዓለም  አቀፍ ደረጃ የመንፈሳዊ ተልዕኮ ቀን” ተከብሮ ማለፉ ይታወቃል። ይህ ዓመታዊ “ዓለም አቀፍ የመንፈሳዊ ተልዕኮ ቀን” በርካታ ቀሳውስት፣ ደናግላን፣ ምዕመናን እና መንፈሳዊ ነጋዲያን በተገኙበት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መሪነት በተካሄደው መስዋዕተ ቅዳሴ ተከብሮ ማለፉን ከስፍራው ከደርሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙት ስብከት በእለቱ የተከበረውን ዓለም አቀፍ የሚስዮናዊያን ቀን ከግምት ባስገባ መልኩ ባደረጉት ስብከት “ ሕይወት ተልዕኮ እና ስጦታ ነው” ማለታቸው ተገልጹዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል እንድተከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

በዛሬ እለት ሥርዓተ አምልኮ ሥነ-ስርዓት ላይ በሁለተኛ ደረጃ የተነበበው ምንባብ ሐዋርያው ጳውሎስ ታማኝ የሥራ ተባባሪ ለሆነው ለጢሞቴዎስ “ቃሉን ስበክ፤ ጊዜው ቢመችም ባይመችም ዝግጁ ሁን፤ በታላቅ ትዕግሥትና በማስተማር አቅና፤ ገሥጽ፤ አበረታታም” (2ጢማ 4፡2) በማለት የተናገረውን ማሳሰቢያ ሰምተናል። ቃሉ ከልብ የመነጨ ነው- ጢሞቴዎስ ለሚሰጠው አስተምህሮ ኃላፊነት ሊሰማው ይገባል።

ዛሬ የሚከበረው የዓለም የተልዕኮ ቀን እያንዳንዱ ምስጢረ ጥምቀት የተቀበለ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ማወጅ እንደ ሚገባው የበለጠ የሚገነዘብበት፣ የእግዚኣብሔርን መንግሥት በታደሰ መንፈስ በተግባር መመስከር እንደ ሚገባው እንዲገነዘብ ጥሩ አጋጣሚ ይፈጥራል። ለመላው ቤተ-ክርስቲያኗ በታደሰ መልኩ የሚስዮናዊነት ተልእኮ ከፍተኛ ኃላፊነት መስጠት የሚያስችል መግለጫ ለመስጠት ከአንድ መቶ ዓመት በፊት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ 15ኛ “ማክሲሙም ኢሉድ” በሚል አርእስት ሐዋርያዊ መልእክት አስተላልፈው ነበር። ከማንኛውም የቅኝ ግዛት ወረራ እና ከአውሮፓ ሀገሮች የማስፋፊያ ፖሊሲዎች ነፃ መሆን እንዲቻል በዓለም ላይ ቤተክርስቲያን ያላት ተልዕኮ የማሻሻል አስፈላጊነት ተሰማቸው።

በዛሬው በተለወጠው አውድ ውስጥ የቤኔዲክስ 15ኛ መልእክት አሁንም ወቅታዊ ነው፣ እናም ራስን በማጣቀሻነት በመውሰድ ራስን ዝግ ማደረግ እና እያንዳንዱ ሐዋርያዊ እንቅስቃሴ የሚገጥመውን ተግዳሮት ለማለፍ ራሳችንን ለቅዱስ ወንጌል አስደሳች ልብ መክፈት እንችል ዘንድ ያበረታታናል።

በእዚህ አሁን ባለንበት ዘመናች፣ ሰዎችን ከነልዩነታቸው ተጨባጭ በሆነ መልኩ የሚደግፍ እና የሚያከብር ሁኔታ መንሮ በሚገባበት አሁን ባለው ግሎባላይዜሽን ይህንን ከማስፈጸም ይልቅ በምትኩ ከድሮ ጀምሮ ሲንከባለሉ በመጡ ኃያልነታቸውን ለማስከበር በማሰብ ከሚደረጉ ጦርነቶች እና ፕላኔቷን በሚያወድም እና በሚያበላሽ መልኩ በሚደረጉ የኃይል ግጭቶች ዓለማችን አሁንም እየተሰቃየች ትገኛለች፣ አማኞች በየቦታው በመንቀሳቀስ መልካም ዜና የሆነውን የኢየሱስ ምሕረት ኃጢአትን ድል እንደ ሚያደርግ፣ ተስፋ ፍርሃትን፣ ጥምረት ደግሞ ጠላትነትን እንደ ሚያሸንፍ ማወጅ ያስፈልጋል። ክርስቶስ ሰላማችን ነው፣ እናም በእርሱ ውስጥ እያንዳንዱ ክፍፍል ተሸንፏል፣ በእርሱ ብቻ ነው የሰዎች መዳን የሚገኘው።

ተልዕኮውን ሙሉ በሙሉ ለመኖር አንድ አስፈላጊ ሁኔታ አለ ፣ ጸሎት ፣ ልባዊ እና የማያቋርጥ ጸሎት ፣ በዛሬዉ ቅዱስ ወንጌል ውስጥ እንደታወጀው እና በኢየሱስ ትምህርት ውስጥ እንደ ተጠቀሰው “ሁል ጊዜ ፈጽሞ ሳይታክቱ መጸለይ” (ሉቃ 18፡1) አሰፍላጊ መሆኑን በምሳሌ ተናግሩዋል። የወንጌል ብርሃን እና ጸጋ ገና ለማያውቁ ሰዎች ለማወጅ እና ይህንን ከባድ የሆነ ተልዕኮ በፍቅር እና ምስጋና በተሞላው መልኩ ሚስዮናዊያን ያከናውኑ ዘንድ ወደ እግዚኣብሔር የሚደረግ ጸሎት የመጀመሪያው ድጋፍ ነው። እንዲሁም ዛሬ ለእራሳችን ጥያቄ የምናቀርብበት ጥሩ አጋጣሚ ነው፡ ለሚስዮናዊያን እጸልያለሁ ወይ? የእግዚአብሔርን ቃል በምስክርነት ለማዳረስ ርቀው ለሚሄዱ ሰዎች እጸልያለሁ ወይ? እስቲ ይህንን ጉዳይ በጥልቀት እናስበው።

የሰዎች ሁሉ እናት የሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በየእለቱ የቅዱስ ወንጌል ሚስዮናውያንን ትከተላቸ እንዲሁም ትጠብቃቸው።

20 October 2019, 12:34