ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ቅዱሳን በዓለም ጨለማ ውስጥ ብርሃን ሆነው ያለፉ ሰዎች ናቸው” አሉ።

በሕይወት ዘመናቸው መልካሙን ግድል በመፈጸም በእግዚኣብሒር ኃይል እና በራሳቸው ከፍተኛ ጥረት የእዚህ ዓለምን ፈተና ድል ለመንሳት ከፍተኛ መንፈሳዊ ተጋድሎ አድርገው ላለፉ አምስት ሰዎች በጥቅምት 02/2011 ዓ. የቅድስና ማዕረግ እንደ ተሰጣቸው ለቫቲካን ዜና ከደርሰው ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል። ይህንን የቅድስና ማዕረግ የሰጡት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እንደ ነበሩ ከደርሰን ዘገባ ለማረዳት የተቻለ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙት ስብከት እግዚኣብሔርን መማጸን፣ ከእርሱ ጋር መራመድ እና እርሱን ማመስገን በሚሉት ጭብጦች ዙሪያ ላይ እንደ ነበረም ተያይዞ ከደርሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “ቅዱሳን በዓለም ጨለማ ውስጥ ብርሃን ሆነው ያለፉ ሰዎች ናቸው” ማለታቸው ተገልጹዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ቅዱስነታቸው በወቅቱ ጸሎት የነፍስ መድኅኒት ነው፣ እምነት ከእግዚኣብሔር ጋር አብሮ መጓዝ ማለት ነው፣ “ማመስገን” ማለት በጣም ቀላል በሆኑ ቃላት እግዚአብሔርን መባረክ ማለት ነው ማለታቸው ተገልጹዋል። ቅዱሳን በእምነት ሕይወት ጎዳና ላይ የሚገጥሙዋቸውን ፈተናዎች በመጋፈጥ እና ራሳቸውን ቀስ በቀስ ለመስዋዕትነት በማቅረብ፣ እውነተኛውን ኢየሱስ በሕይወታቸው በመሻት ይኖሩ እንደ ነበረ ጨምረው የገለጹት ቅዱስነታቸው እነዚህ በእለቱ የቅድስና ማዕረግ የተሰጣቸው አምስት ቅዱሳን በገጠራማ ስፋራዎች የምትገኘውን እና በእለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ እንደዚህ አይነት ሕይወት የምትኖር የቤተክርስትያንን ፊት የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል። በእለቱ የቅድስና ማዕረግ የተሰጣቸው እንግሊዛዊው ካርዲና ሄንሪ ኒው ማን፣  የቅዱስ ካርሜሎስ ልጆች ማሕበር መሳርች የነበሩ ሲስተር ጁሴሚና ቫኒ፣ የሕንድ አገር ተወላጅ የነበሩ ማርያም ትሬዛ ካርሜል ማኪዲያና፣ የብራዚል አገር ተወላጅ የነበሩ ሲስተር ዱልቼ ሎፔዝ እና የእስዊዚ አገር ተወላጅ የሆኑት ማርጌሪታ ባዬስ መሆናቸውም ተገልጹዋል።

13 October 2019, 17:12