ፈልግ

በሰሜናዊ ምስራቅ ሶሪያ የተቀሰቀሰው ጦርነት ይገታ ዘንድ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ጥሪ አደረጉ። በሰሜናዊ ምስራቅ ሶሪያ የተቀሰቀሰው ጦርነት ይገታ ዘንድ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ጥሪ አደረጉ።  

በሰሜናዊ ምስራቅ ሶሪያ የተቀሰቀሰው ጦርነት ይገታ ዘንድ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ጥሪ አደረጉ።

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከ2011 ዓ.ም በኋላ እስከ ዛሬ ድረስ ለባለፉት ስምንት አመታት ማለት ነው፣ በሶሪያ የእርስ በእርስ ጦርነት በመካሄድ ላይ እንደ ሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ነፍስ የቀጠፈና ከ8 ሚልዮን በላይ ሰዎችን ለአስከፊ ስደት የዳረገ፣ ከቤት ንብረታቸው እንዲፈናቀሉ እና ከተማዎቻቸውን እና እንዲሁም መንደሮቻቸውን ያፈራረሰ፣ በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ አስከፊ ከሚባሉ የእርስ በእርስ ጦርነቶች ውስጥ የሚመደበው ይህ በሶሪያ የሚካሄደው የእርስ በእርስ ጦርነት እስካሁን ድረስ ማብቂያ አለማግኘቱ ይታወቃል። ይህ የእርስ በእስር ጦርነት አንዳንድ ጊዜ ጋብ ያለ የሚሄድ ቢመስልም፣ በተለያዩ ጊዜያት እንደ አዲስ በመቀስቀስ የንጹሃን ማህበርሰብ ስቃይን እያባባሰ እንደ ሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን በተለይም ደግሞ ከቅርብ ጊዜያት በኋላ በሶሪያ በኩል የሚገኙ ኩርድ ሕዝቦችን በማገዝ ላይ የነበሩ የአሜሪካ ወታደሮች አከባቢውን መልቀቅ በመጀመራቸው የተነሳ፣ የቱርክ ጦር በከፈተው የጦር ዘመቻ በሶሪያ ሰሜናዊ ምስራቅ በሚከናወነው ወታደራዊ እርምጃ ምክንያት የአከባቢው ሕዝብ ቤት ንበረታቸውን ጥለው እዲሸሹ ያስገደደ ሲሆን - ከእነዚህም መካከል ፣ በርካታ ክርስቲያን ቤተሰቦች እንደ ሚገኙበት ከስፍራው ከሚወጡ ዘገባዎች ለመረዳት ተችሉዋል።

የእዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በእዚህ አሰቃቂ እና ረጅም ጊዜ የፈጀ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳታፊ የሆኑ የሶሪያ እና ከሶሪያ ውጪ የመጡ ለጦርነቱ መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋጾ እይዳረጉ የሚገኙ አካላት ለእዚህ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ አሰቃቂ በሚባል ደረጃ ከፍተኛ ውድመት ላስከተለው ጦርነት ፖሌቲካዊ መፍትሄ እንዲፈልጉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በተደጋጋሚ የመማጸኛ ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ሲሆን አሁን በሰሜናዊ ምስራቅ የሶሪያ ግዛት ውስጥ በአዲስ መልክ የተቀሰቀሰውን ግጭት በማውገዝ ባለፈው እሁድ ጥቅምት 02/2012 በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት “የተወደደው የሶርያ ሕዝብ አሁንም ቢሆን በስቃይ ውስጥ ይገኛል” በማለት የሁኔታውን አሳዛኝነት እና አስከፊነት መግለጻቸው ታውቁዋል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባስተላለፉት መልእክት የሚከተለውን ብለው ነበር . . .

“ሀሳቤ እንደገና ወደ መካከለኛው ምስራቅ ይሄዳል። በተለይም የተወደደው እና በሰሜናዊ ምስራቅ የሶሪያ ክፍል የሚገኙ ህዝቦች ዕጣ ፈንታ በወታደራዊ ጥቃቶች ምክንያት ቤት ንብረታቸውን ጥለው ለመሰደድ ለተገደዱ ሶራዊያን በሙሉ እጅግ አሰቃቂ ሥቃይ እና መከራ እየደረሰባቸው ይገኛል፣ ከእነዚህ ህዝቦች መካከልም ብዙ ክርስቲያን ቤተሰቦች ይገኙበታል። ለሚመለከታቸው በጦርነቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳታፊ ለሆኑ ተዋናዮችና ለአለም አቀፍ ማህበረሰብም ፤ ውጤታማ መፍትሔዎችን ለመፈለግ በውይይት መንገድ ላይ በቅንነት ፣ በሐቀኝነት እና በግልፅነት እንዲሳተፍ ጥሪ ለማቅረብ እወዳለሁ!

በአከባቢው የሚገኘው የቱርክ ጦር በከፈተው ጥቃት ከባለፈው ሳምንት አጋማሽ ጀምሮ በሰሜን ምስራቅ የሶሪያ አከባቢ በሚገኙ ቴል አቢያድና የራስ አል አይን በተሰኙ ከተሞች ይኖሩ የነበሩ ከ130,000 ሰዎች በላይ መኖሪያ ቤታቸውን ለቀው መሰደዳቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በቅርቡ ማስታወቁ ይታወሳል። ከእነዚህ ስደተኞ መካከል አብዛኞቹ ኣል ታማር እና ራቃ በሚባሉ አጎራባች አከባቢዎች በሚገኙ ቦታዎች ወይም በትምህርት ቤቶች ውስጥ መጠለላቸውን ተያይዞ ከደርሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
13 October 2019, 14:33