ፈልግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከምዕመናን ጋር፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከምዕመናን ጋር፣ 

ቅዱስ ቪንሴንት ዴ ፖል ሆይ፥ ቸርነትን አስተምረን!

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመስከረም 14/2012 ዓ. ም. ባቀረቡት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮአቸው ማጠቃለያ ላይ ከኢጣሊያ እና ከሌሎች አገሮች ለመጡት ምዕመናን እና መንፈሳዊ ነጋዲያን እንዲሁም ሃገር ጎብኝዎች ሰላምታቸውን አቅርበዋል። ቀጥለውም መጭው ዓርብ መስከረም 16/2012 ዓ. ም. በካቶሊካዊ ቤተክርስቲያን ዓለም አቀፍ የቸርነት ሥራ ማሕበራት መሥራች የሆነው የቅዱስ ቪንሴንት ዴ ፖል ዓመታው በዓል የሚከበርበት ዕለት መሆኑን አስታውሰው፣ “እኛም ደስታ የሚገኝበትን የቸርነት አገልግሎታችንን በድሕነት ምክንያት የሚቸገሩት በእንግድነት ተቀብለናቸው እንድናግዝ እና ሕይወታችንንም ለዚህ አገልግሎት በስጦታ ማቅረብ እንድንችል ቅዱስ ቪንሴንት ይርዳን” በማለት ዕለቱን በጸሎት ደምድመዋል።    

25 September 2019, 17:50