ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ከማዕከሉ ነዋሪ ወጣቶች እና አስተባባሪዎች ጋር በተገናኙበት ወቅት፣ ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ከማዕከሉ ነዋሪ ወጣቶች እና አስተባባሪዎች ጋር በተገናኙበት ወቅት፣ 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፥ “ርህራሄን ለማድረግ ወደ ኋላ ማለት አያስፈልግም”።

ከፖርቱጋል የመጡ የአባ ዳቪድ ደ ኦሊቬራ ማሕበራዊ ማዕከል ወጣቶችን አግኝተው ንግግር ባደረጉበት ጊዜ እንዳሳሰቡት ወጣቶች ርህራሄን ለማድረግ ፍርሃት ሊይዛቸው እንደማይገባ አሳስበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በፖቱጋል አገር ከሃምሳ ዓመት በፊት ወላጆቻቸውን የማያውቁ ሕጻናትን ተቀብሎ ለማሳደግ በሚል ሃሳብ፣ ክቡር አባ ዳቪድ ደ ኦሊቬራ ማርቲንስ አንድ ማዕከል ማቋቋማቸው ሲታወስ የማዕከሉ ሕጻናት ወደ ሮም መጥተው ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር መገናኘታቸውን ኤማኑኤላ ካምፓኒሌ ዘገባ አመልክቷል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዛሬ መስከረም 17/2012 ዓ. ም. ከማዕከሉ ሕጻናት እና አስተባባሪ ሠራተኞች ጋር ሰላምታ በተለዋወጡበት ጊዜ ምስጋናቸውን አቅርበው ወደ ሮም መምጣት ላልቻሉት እና በማዕከሉ እርዳታ ለሚደረግላቸው ሕጻናት፣ ወጣቶች እና አረጋዊያን በሙሉ ሰላምታቸውን እንዲያደርሱላቸው ጠይቀዋል። ለማዕከሉ አስተዳዳሪ ለሆኑት ለክቡር አባ ማኑኤል ዮሐኪም እና ሌሎች የማዕከሉ አባላት ባደረጉት ንግግር፣ የፍቅር አምባሳደር በመሆን በቤተክርስቲያን በኩል ለሕጻናት ለሚበረክቱት የእርዳታ አገልግሎት ምስጋናቸውን አቅርበውላቸዋል።

የማዕከሉ ነዋሪ ለሆኑት ወጣቶች ባስተላለፉት የማበራታቻ ንግግራቸው፣ ርዕሠ ሊቃነ ፍራንችስኮስ እንደተናገሩት ወጣቶቹ የወደፊት መልካም ሕይወት ተስፋ የሚከፍቱበትን ቁልፍ የሰጡት ቅዱስነታቸው ከጎናቸው ሆኖ የሚመራቸው የተስፋ ቁልፍ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን አስረድተዋል።

የሕይወት ጉዞአቸው አብረው የወደፊት ሕይወታቸውን እንዲመለከቱ ያግዛል ያሉት ቅዱስነታቸው የሚመለከቱትም ራሳቸውን ብቻ ሳይሆን፣ ሐዋርያው ጳውሎስ እንደሚያስተምረው የዛሬውም ሆነ የነገው ተስፋዎች ራሳቸው መሆናቸውን ገልጸው በሕይወት ጉዞ መካከል ሁል ጊዜ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር መሆናቸውን እና የኢየሱስ ክርስቶስ መሆናቸውንም አስረድተዋል።  በማከልም የእስካሁን ሕይወታቸው ትክክለኛ ትርጉምን የሚያገኘው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በመሆናችሁ ነው ብለዋል። በዘወትር ጸሎታችሁ፣ ለወንድሞቻችሁ እና ለእህቶቻችሁ በምታደርጉ እንክብካቤ አማካይነት ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር መሆናቸውንም አስረድተዋል። በመሆኑም በመካከላችሁ አንዱ ለሌላው ርህራሄን ከማድረግ ወደ ኋላ ማለት እንደማያስፈልግ አሳስበዋል።

የምሕረት እና የርህራሄ መልዕክተኞች ናችሁ፣

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለአባ ዳቪድ ደ ኦሊቬራ ማዕከል ነዋሪዎች ያደረጉትን ንግግር ሲያጠቃልሉ ያለፈው ሕይወታቸው የወደፊት ለመወሰን እንደሚያግዛቸው አስረድተው፣ ወደ ፊት የሚመኙትን ነገር ለማግኘት ዛሬ በርትተው መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል። በዚህ ወቅትም ከመማከላቸው ማንም የብቸኝነት ስሜት እንዳይሰማው፣ የኢየሱስ ክርስቶስ አምሳል የሆነ ሰው ሁሉ ለሌላው የቅርብ አጋዡ ሊሆን እንደሚገባ ገልጸው፣ እርስ በርሳችሁ ምህረትን ፣ ርኅራሄን እና ፍቅርን የምታደርጉ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ይርዳችሁ በማለት ቡራኬአቸውን ሰጥተዋል።

ይህን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!

            

28 September 2019, 16:48