ፈልግ

የስነ ጥበብ ሥራ ውጤት ለሕዝብ እይታ መርቀው በከፈቱበት ወቅት፤ የስነ ጥበብ ሥራ ውጤት ለሕዝብ እይታ መርቀው በከፈቱበት ወቅት፤ 

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፥ “ከማሕበረሰቡ መካከል ማንም መገለል የለበትም”።

ር. ሊ. ጳ. ጳጳስት ፍራንችስኮስ ትናንት እሁድ ካቀረቡት የስብከተ ወንጌል አስተንትኖ በመቀጠል በደባባዩ ከተገኙት ስደተኞች፣ ጥገኝነት ጠያቂዎች እና መንፈሳዊ ነጋዲያን ጋር ሆነው የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት አድርሰዋል። ከመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ቀጥለው ባደረጉት አጭር ንግግር ወደ አካባቢያችንና ወደ ማኅበረሰባችን ለሚመጡ ሁሉ እንግዳ ተቀባይነታችንን ማሳየት አለብን በማለት ለምእመናኑ በሙሉ አሳስበው በስፍራው ለተገኙት በሙሉ ሰላምታቸውን አቅርበውላቸዋል።   ፡፡

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በትላንትናው እለት ለመስዋተ ቅዳሴና ለመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለነበሩት በርካታ የስደተኛው ማሕበረሰብ፣ ምእመናን ባደረጉት ንግግር፣ በዚህ ወቅት  ቤተክርስቲያናችን ትኩረት የምታደርገው ለተጎዱትና ለተለያዩ ማሕበራዊ ችግሮች ተጋላጭ ለሆኑት ወገኖች እገዛ ለማድረግ ነው ካሉ በኋላ በዓለም ዙሪያ ካሉ ሀገረ-ስብከቶች ሁሉ ጋር በመተባበር በዚሁ የዓለም የስደተኞች በዓል በሚከበርበት ቀን አስረግጠው ሲናገሩ፣ ማንም ሰው ከህብረተሰብ አይገለልም በማለት ተናግረዋል።

የስደተኞችን መከራ እና ስቃይ ማሳያ ይሆን ዘንድ አንድ የስነ ጥበብ ሥራ ውጤት ለሕዝብ እይታ መርቀው ከከፈቱ በኋላ መታሠቢያም እንዲሆን በቅዱስ ጴጥሮስ አንደባባይ እንዲደረግ አዝዘው ይህን ሁላችንም የእንግዳ ተቀባይነት ሐዋርያዊ ተልዕኮአችንን እንድንድወጣ ማስታወሻ ይሆነናል በማለት ተናግረዋል። 

30 September 2019, 17:27