ፈልግ

ለር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በሞሪሼስ የክብር አቀባበል ተደርጎላቸዋል፣ ለር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በሞሪሼስ የክብር አቀባበል ተደርጎላቸዋል፣ 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በሞሪሼስ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን መጀመራቸው ተነገረ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከነሐሴ 29 - ጳጉሜ 5 ቀን 2011 ዓ. ም. ድረስ በሦስት የአፍሪቃ አገሮች፣ በሞዛምቢክ፣ በማዳጋስካር እና በሞሪሼስ ውስጥ የሚያደርጉትን 31ኛ ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን በመቀጠል የሁለቱን አገሮች ሐዋርያዊ ጉብኝት ፈጽመው ዛሬ ጳጉሜ 4/2011 ዓ. ም. ወደ ሦስተኛዋ እና የሐዋርያዊ ጉብኝታቸው የመጨረሻዋ አገር ወደ ሆነችው ወደ ሞሪሼስ መጓዛቸውን የቫቲካን ዜን አገልግሎት ባልደረባ ኤማኑኤላ ካምፓኒሌ የላከችልን ዘገባ አስታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ከማዳጋስካር ዋና ከተማ አንታናናሪቮ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ዛሬ ጠዋት የተነሱት ቅዱስነታቸው ወደ ሞሪሼስ ደሴት፣ ወደ ዋና መዲና ፖርት ሉዊስ፣ በአገሩ የሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ በሁለት ሰዓት ተኩል ሲደርሱ በአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በክቡር ፕራቪንድ ጁኛውት እና በፖርት ሉዊስ ከተማ ሊቀ ጳጳስ በብጹዕ ካርዲናል ማውሪስ ፒያት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል የክብር አቀባበል አበባም ተበርክቶላቸውል። በስፍራው ከነበሩት ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ ከሐይማኖት ተቋማት እና ከሕዝባዊ ማሕበራት ተወካዮች ጋር ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሰላም ንግሥት የንግደት ሥፍራ ሲደርሱ የቁምናው መሪ ካህን ከበርካታ ካቶሊካዊ ምእመናን ጋር አቀባበል አድረገውላቸዋል። ቅዱስነታቸው በተቀመጠላቸው የሐዋርያዊ ጉብኝት መርሃ ግብር መሠረት ከረፋዱ ሦስት ሰዓት ከሩብ ላይ የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ስነ ስርዓት መፈጸማቸው ታውቋል። ቅዱስነታቸው በሞሪሼስ የሚያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን “የሰላም መንፈሳዊ ተጓዥ” በሚል መሪ ቃል መጀመራቸው ታውቋል።

በመስዋዕተ ቅዳሴው ስነ ስርዓት ወቅት እ. አ. አ. በ1970 ዓ. ም. ብጽዕናቸው የታወጀላቸው ሚሲዮናዊ፣ የብጹዕ ጃኮብ ዴዚሬ ቅዱስ አጽም በክብር ቦታ ተቀምጦ ለምዕመናን ይፋ መደረጉ ከሥፍራው የደረሰን ዘገባ አመልክቷል።          

09 September 2019, 19:23