ፈልግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጸሎታቸውን ለማቅረብ ወደ ባዚሊካው በደረሱበት ወቅት፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጸሎታቸውን ለማቅረብ ወደ ባዚሊካው በደረሱበት ወቅት፣ 

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለጉዟቸው መሳካት የእመቤታችን ማርያም ድጋፍ ተማጸኑ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወደ ሞዛምቢክ፣ ማዳጋስካር እና ሞሪሼስ የሚያደርጉት 31ኛው ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት የተሳካ ይሆን ዘንድ ጸሎታቸውን አቅርበዋል። ከነሐሴ 29/2011 ዓ. ም. ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 5/2011 ዓ. ም. ድረስ ለሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ጉዞ ከመጀመራቸው አስቀድመው በሮም ከተማ ውስጥ ወደ ሚገኘው ወደ ታላቁ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ባዚሊካ በመሄድ ጸሎታቸውን አድርሰዋል።

ቅዱስነታቸው ከዚህ በፊትም ቢሆን ይህን የመሰለ ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን ከመጀመራችን አስቀድመው በሮም ከተማ ውስጥ ከሚገኙት አራት ታላላቅ ባዚሊካዎች መካከል አንዱ ወደ ሆነው ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ባዚሊካ በመሄድ ጸሎት ማድረሳችው የተለመደ ነው።  

03 September 2019, 16:37