ፈልግ

የር. ሊ. ጳ. ፍራንቺስኮስ የበረራ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የር. ሊ. ጳ. ፍራንቺስኮስ የበረራ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ፣  

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ከአፍሪቃ ጉብኝታቸው ሲመለሱ ዜጣዊ መግለጫ ሰጡ።

ከሶስት የአፍሪቃ አገራት በሚመለሱበት የበረራ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ያገኟቸውን የህጻናቱ ደስታ በማስታወስ መንግስት የማህበረሰብ መሰረት የሆነውን ቤተሰብን የመንከባከብና የማስተዳደር ሃላፊነት እንዳለበት ተናግረዋል ፡፡ እሳቸው እንዳሉት አዲስ ነገር የመቀበል ፍራቻ በሽታ እንደሆነና ርዕዮተ ዓለማዊ ቅኝ ግዛት ባለበት በዚህ ዘመንም የባህላዊ ማንነታችን ጥበቃ እንዲደረግለትም ጥሪ አቅርበዋል፡፡”መንግስት ቤተሰብን የመንከባከብ ሀላፊነቱን በሚገባ መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል።

መቅድም ገረመው - ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ዋዜማ ላይ እ. ኤ. አ. በ1992   የፒዮስ 12ኛ ታሪካዊ የሬዲዮ መልእክት ባስተላለፉበት ጊዜ በሰላም ሁሉም ነገር ሙሉ እንደሆነና ፣ ነገር ግን በጦርነት ምንም እንደማይገኝ በዘመኑ ማስተጋባታቸውን አድንቀዋል”፡፡ምክንያቱም አሁን ባለንበት ዘመን በየቦታው የሰላም ማጣት መኖሩን ገልጠው ሰላምን አዲስ እንደተወለደ ህጻን መንከባከብ እንዳለብን ካስገነዘቡ በኋላ “በብዙ ርህራሄ” እና “ብዙ ይቅርታ” ታጅቦ ማደግ አለበት በማለትም መክረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ  የመገናኛ ብዙሀን ለሰላምና ለማህበረሰብ ግንባታ ያለው አስፈላጊነትን ለማሳየት የ 80 ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ላለው አንድ የስፔን የዜና ወኪል በቅድሚያ ለመጎብኘት የተለየ ቦታ ሰጥተዋል፡፡የህዝብ ግንኙነትና የመገናኛ ብዙሀን  ሚና ላይ ያላቸውን አመለካከትም ሲገልጡ ሰላምን የሚገነባና ማህበረሰብን የሚያንጽ፣ገንቢ፣ ለሰላም መሳርያነት እንጂ በጭራሽ የጦርነት ግብአት መሆን የለበትም በማለት አስገንዝበዋል።

የአካባቢ ጥበቃን በተመለከተም ሲናገሩ በትምህርታቸው ዓምድ እና ወደ አፍሪካ ባደረጉት የጉዞው አላማ - ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ “ሥነ-ምህዳራዊ ፣ ብዝሃ-ህይወት ፣ ባጠቃላይ ተፈጥሮን መንከባከብ አለብን ምክንያቱም ህይወታችን  ነውና” ሲሉ በማስታወስ ተናግረዋል፡፡የቫቲካንም ዋነኛ ሀላፊነት መሆኑንም አስረድተዋል።ሙስናን በተመለከተም በአውሮፓ ውስጥ ያለ በአፍሪካውያኖች የሚደርስ የጉልበት ብዝበዛም ሰብአዊ አለመሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

11 September 2019, 17:28