ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በካሜሩን ሰላማዊ የፖለቲካ መፍትሄ እንዲገኝ ጥሪ አቀረቡ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ጊዜ ለካሜሩን ሰላማዊ የፖለቲካ መፍትሄ እንዲመጣ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፡አያይዘውም በሃገሪቱ ስለሰላም የሚደረገውም ውይይት በጸሎት መታጀብ እንዳለበት መግለጻቸውን የቫቲካን ዜና አገልግሎት ባልደረባ ሊንዳ ቦርዶኒ የላከችልን ዘገባ አመልቷል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መቅድም ገረመው - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለካሜሩን ህዝብ በዚህ አስቸጋሪ ወቅትም ጭምር ቅርብ መሆናቸውን ገልጸው፣ ለምእመናን በሙሉ ለዚህ ብሄራዊ ውይይት እና ሰላም ዘላቂ መፍትሄ እንዲመጣ እንዲፀልዩ ጠይቀዋል። ቅዱስነታቸው ከመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት  በኋላ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ላይ ንግግር ሲያደርጉ ፣ ሰኞ መስከረም 19/2012 ዓ. ም. በካሜሩን ሃገር፡ሀገሪትዋ ለአመታት ካለችበት ቀውስ እንድትላቀቅና ሀገራዊ ሰላም እንዲሰፍን ብሔራዊ ውይይት እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ለተከበረው የካሜሮን ህዝብ  በዚህ አስቸጋሪ ወቅትም አብሮነታቸውን ከገለጹ በኋላ ለሁላችንም ጥቅም ስንል በዚች ሃገር ሰላም እንዲሰፍንና ዘላቂ መፍትሄ እንዲመጣ ሁሉም ሰው በጸሎት መትጋት እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል።

የካሜሮን ባለስልጣናት እንደገለጹት ስብሰባው ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ሲሆን በዋናነት በነዚህ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች መካከል እ-አ-አ ከ2016 ጀምሮ የተነሳውን ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግር ፍትሐዊ በሆነ መልኩ ለመቅረፍ ነው በማለት ተናግረዋል።

ብሄራዊ ውይይቱም እንዲካሄድ ጥሪ ያቀረቡት የሀገሩ ፕሬዚደንት ክቡር ፖል ብያ ሲሆኑ ለሁለት ሺህ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነውን በነዚህ ሁለት አካላት መሃከል የተነሳውን የሰላም ቀውስ ለመግታት እንደሆነም ተገልጿል።ባልፉት ቀናትም የብዙ ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ግጭቶችና ጸብ ባሉባቸው አካባቢዎች በሚነሳው እሳት ምክንያት መብራት የተቋረጠ ሲሆን ነዋሪውን ከአደጋ ለመከላከል የጸጥታ አስከባሪዎችም መሰማራታቸው ተገልጿል።

30 September 2019, 17:35