ፈልግ

በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከተሰበሰቡት ምእመናን በከፊል፣ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከተሰበሰቡት ምእመናን በከፊል፣ 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ከስደተኞች ጋር የመስዋዕተ ቅዳሴን ጸሎት እንደሚያቀርቡ መሆኑን አስታወቁ።

ር. ሊ. ጳ. ጳጳስት ፍራንችስኮስ ትናንት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡት ምእመናን ያሰሙትን የስብከተ ወንጌል አስተንትኖ ከፈጸሙ በኋላ በስፍራው ለተገኙት በሙሉ ሰላምታቸውን አቅርበውላቸዋል። ከሰላምታቸው ቀጥለው ባሰሙት ንግግር መጪው እሁድ መስከረም 18/2012 ዓ. ም. ዓለም አቀፍ የስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች መታሰቢያ ቀን መሆኑን አስታውሰው፣ እለቱንም ከተለያዩ አገር ስደተኞች፣ ጥገኝነት ጠያቂዎች፣ እና ከመላው ምዕመናን ጋር ሆነው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በሚያሳርጉት የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት የሚያስታውሱ መሆኑን አስታውቀዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መቅድም ገረመው - ቫቲካን

እሑድ መስከረም 11/2012 ዓ. ም. ካቀረቡት የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት  በኋላ ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተሰበሰቡትን ምእመናን ለስደተኞች እንዲፀልዩ ጥሪ ካቀረቡ በኋላ እንዲሁም የዓለም የስደተኞች ቀን በሚቀጥለው ሳምንት  የሚከበር መሆኑን አሳስበዋል፡፡ በመጪው እሁድ መስከረም 18/2012 ዓ. ም.፣ 105ኛው የዓለም የስደተኞች  ቀን እንደሚከበር በትላንትናው እለት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙት ምእመናን አስገንዝበዋል። ዕለቱን ለማክበር ከጠዋቱ 3:30 በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ መስዋተ ቅዳሴ እንደሚያሳርጉ አስታውቀዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለስደተኞች እና ለተፈናቀሉት መብት መሟገት ከትላልቅ ትኩረት ከሚሰጡዋቸው ሐዋርያዊ ስራዎቻችው መካከል ዋነኛው ሲሆን ከእሁድ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በኋላ ለምእምናኑ፣ በአለም ዙሪያ የሚገኙ ስደተኞችን በጸሎት በማስታወስ ቅርበታችንን መግልጽ አለብን በማለት ጥሪ አቅርበዋል። የመስዋተ ቅዳሴውን ጸሎት ስነ ስርዓት በጋራ ሆነው ያዘጋጁት የኢጣሊያ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ እና በቅድስት መንበር የሰው ልጅ ሁለንተናዊ  እድገት አገልግሎት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት መሆናቸው ታውቋል።

ቅዱስነታቸው በንግግራቸው ላይ እንደገለጹት፡ የዕለቱ ጭብጥ “ስደተኞች ብቻ አይደሉም” የሚል ትርጉም እንዳለው በመግለጽ ስለ ስደተኞች ፣ ስለ ተፈናቃዮች ፣ ስለ ጥገኝነት ጠያቂዎች እና ስለ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባዎች እንዲሁም እኛ ሁላችንም እንደ አንድ ግለሰብ እና እንደ አንድ ቤተሰብ ሆነን ለእነዚህ ሰዎች ማሰብና መቆርቆር ይገባናል በማለት ጥሪ አቅርበዋል ፡፡

23 September 2019, 16:38