ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በፔሩ ከአማዞን ቀደምት ሕዝቦች ጋር በተጋናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በፔሩ ከአማዞን ቀደምት ሕዝቦች ጋር በተጋናኙበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፣- አክራሪ የሆነ ሉዋላዊነት እና መርህ አልባ ሕዝባዊ ወገኝተኝነት ወደ ጦርነት ይመራል!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በነሐሴ 02/2011 ዓ. ም Vatican Insider በመባል ከሚታወቀው ጋዜጣ፣ ጋዜጠኛ ከሆነው አቶ ዶሜኒኮ አጋሶ ጋር በነበራቸው ቆያት “የአውሮፓ አህጉር መፈራረስ የለበትም እያንዳንዱ አገር ሉዋላዊ ማንነቱን በጠበቀ መልኩ ራሱን ለሌሎች ክፍት ማድረግ ይኖርበታል” ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን “የራስን ሉዋላዊነት ብቻ ለማረጋገጥ የሚደርገው ሩጫ ግጭቶችን ሊፈጥር ይችላል፣ እናም በሕዝቦች መካከል ውይይት የሚካሄድበትን መንገድ ማመቻቸት ያስፈልጋል” ብለዋል። ስደተኞችን ተቀብሎ ማስተናገድ ይችል ዘንድ የፖሌቲካ ቁርጠኝነት እና ብልህነትን ይጠያቃል ያሉት ቅዱስነታቸው በቅርቡ የአማዞን ደን እና የአከባቢውን ማኅበርሰቦች ሁኔታ በተመለከተ የሚደረገው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ሲኖዶስ ከቤተክርስቲያኗ የተወለደ እና ወንጌላዊ ገጽታ ያለው ምላሽ በመስጠት በምድራችን ላይ ለተቃጣው አካባቢያዊ አደጋ ምላሽ እንደ ሚሰጥ ይጠበቃል ብለዋል።

የእዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

“መበታተን እና መፍረስ የሌለበት ቅርስ ስለሆነ የአውሮፓን አህጉር መታደግ ይገባል” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የአንድ አገር የግል ሉአላዊነት ለማረጋገጥ ብቻ የሚደርገውን ሩጫ እና የሕዝቡን ወኔ እንደ ገና በመቀስቀስ ማብቂያ የሌለው ጥያቄ የሚፈጥረውን መርህ አልባ ሕዝባዊ ወገኝተኝነት (Populism) ማስታገስ የሚቻለው “ከእያንዳንዱ አገር ማንነት ጀምሮ” ሰብዓዊ መብቶችን ባከበረ እና ክርስቲያናዊ እሴቶችን ከግምት ባስገባ መልኩ በመደማመጥ ላይ የተመሰረት ውይይት በማደረግ አለመግባባቶችን ለመቅረፍ እንደ ሚቻል ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስት ፍራንቸስኮስ በሐምሌ 02/2011 ዓ.ም Vatican Insider በመባል ከሚታወቀው ጋዜጣ አዘጋጅ ከሆነው አቶ ዶሜኒኮ አጋሶ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደ ገለጹት “በአሁኑ ወቅት የአውሮፓ አህጉር ከተደቀነበት የመፈራረስ አደጋ ለመታደግ ይችላ ዘንድ አሁን ካለው የአውሮፓ ሕብረት መዋቅር ጋር ተባብሮ መሥራት እንደ ሚገባ” ገልጸው ቅዱስነታቸው ከVatican Insider በመባል ከሚታወቀው ጋዜጣ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ከሆነው ከአቶ ዶሜንኮ አጋሶ ጋር በነበራቸው ቆይታ የአውሮፓን አህጉር ጉዳይ ጨምሮ፣ የስደተኞችን፣ የዓለም የአየር ንብረት ለውጥን እና እንዲሁም በቅርቡ የአማዞን ደንን በተመለከተ በሚደረገው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ሲኖዶስ በተመለከተ አንስተው መወያየታቸው ተገልጹዋል።

የአውሮፓ አህጉር መሥራች አባቶች ሕልም እውን መሆን ይኖርበታል

የአውሮፓ አህጉር “የአውሮፓ አህጉር መሥራች አባቶችን ሕልም” እውን እንደ ሚያደርግ ተስፋ አለኝ በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ያን ታሪካዊ እና ባህላዊ አንድነት እውን ያደረገ አስተሳሰብ ሲተገበር፣ እንዲሁም አህጉራዊ መልካምድር በመጠበቅ የቅድሞ የአውሮፓ አህጉር መስራች አባቶችን ሕልም እና ርዕይ እውን ማደረግ እንደ ሚችላ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል። ምንም እንኳን “የአስተዳደር ችግሮች እና የውስጥ አለመግባባቶች” የነበሩ ቢሆንም ፣ የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ወ/ሮ ሁርሱላ ቮን ደር ሌዬን “የአውሮፓ አህጉር መስራች አባቶች የነበራቸውን ርእይ እና ጥንካሬ መልሶ በማምጣት” የአውሮፓ አህጉር ቀድሞ ወደ ነበረበት ቁመናው እንዲመለስ የማደረግ ብቃት አላቸው ብዬ አምናለሁ” ያሉት ቅዱስነታቸው ምክንያቱም “ሴቶች የማስተባበር እና የመተባበር ችሎታ ያላቸው በመሆኑ የተነሳ ነው” ብለዋል።

የአውሮፓ አህጉር ሰብአዊና ክርስቲያናዊ እሴቶቹን መጠበቅ ይኖበታል

የአውሮፓን አህጉር እንደገና በአዲስ መልክ አጠናክሮ ለማስቀጠል እንዳይቻል ተግዳሮት እየሆነ የሚገኘው በበቂ ሁኔታ ገንቢ ውይይቶችን ካለማድረግ የመጣ ነው በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “በአውሮፓ ህብረት ውስጥ የመወያየት፣ ችግሮችን የመጋፈጥ፣ የመደራደር ባሕላችንን ማሳደግ ይኖርብናል” ያሉት ቅዱስነታቸው ከእያንዳንዱ አስተሳሰብ በስተጀርባ በቅድሚያ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው የአውሮፓ አህጉር መሆን ይኖርበታል በመቀጠል ደግሞ የእያንዳንዳችን አገር ሊሆን ይገባዋል ብለዋል። ይህንን አስተሳሰብ እውን ለማደረግ ደግሞ በቅድሚያ “የአውሮፓ አህጉር ሰብአዊና ክርስቲያናዊ እሴቶቹን አስጠብቆ መቀጠል ይኖርበታል” ያሉት ቅዱስነታቸው በቅድሚያ የሰው ልጆች ሰብዓዊ ክብር ሙሉ በሙሉ እውን ሊሆን የገባዋል፣ ከእዚህ ጋር በተያያዘ መልኩ ደግሞ ክርስትያናዊ እሴቶች ተጠብቀው ሊቀጥሉ ይገባል ምክንያቱም የአውሮፓ አህጉር ስር መሰረቱ የተገነባው የሰዎችን ሰብዓዊ መብት በማስጠበቅ እና ክርስትያንዊ በሆኑ እሴቶች ላይ መሆኑ ከታሪክ መዝገብ በሚገብ ለመረዳት ይቻላል ብለዋል።  “ክርስቲያን ስል የካቶሊክ የኦርቶዶክስ እና የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስትያናትን ጭምር እንደ ሆነ ልብ ሊባል ይገባል” ያሉት ቅዱስነታቸው የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ለአውሮፓ አህጉር ከፍተኛ የሆነ አዎንታዊ አስተዋጾ አበርክተዋል ያሉት ቅዱስነታቸው በአጠቃላይ ሁሉም ክርስቲያኖች ለአውሮፓ አህጉር ምስረታ መሰረታዊ የሆኑ እሴቶችን አበርክተዋል።

ማንነት ለድርድር የሚቀርብ ነገር አይደለም ፣ ግን ለውይይት ክፍት መሆን አለበት

“ማንነት ለድርድር የሚቀርብ ነገር አይደለም፣ ግን ለውይይት ክፍት መሆን ይኖርበታል” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ግልጽ ነው እያንዳንዳችን” አስፈላጊዎች ነን፣ ማንም እንደ ሁለተኛ ዜጋ ሊቆጠር አይገባውም በእዚህም የተነሳ በእውነቱ እያንዳንዱ ውይይት ከራስ ማንነት መጀመር ይኖርበታል” ብለዋል። ቅዱስነታቸው ይህንን ሐሳባቸውን በሚገባ ለማስረጽ በማሰብ የሚከተለውን ምሳሌ ተናግረዋል፦ “በሐይማኖት ተቋማት መካከል ሕብረት እንዲፈጠር ውይይት ማደረግ ከፈለኩኝ በቅድሚያ መነሳት የሚገባኝ ካቶሊካዊ ከሆነው ማንነቴ ነው፣ በተመሳሳይ መልኩ በሐይማኖት ተቋማት መካከል ሕብረት እንዲፈጠር መሥራት የሚፈልግ አንድ ፕሮቴስታንት ወይም አንድ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ በቅድሚያ ውይይቱን የሚጀምረው ከራሱ ማንነት ተነስቶ ሊሆን ይገባዋል” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የግል ማንነት ለድርድር የሚቀርብ ነገር ሳይሆን ነገር ግን ይህንን የግል ማንነት ከሌሎች ሰዎች ማንነት ጋር በማዋሃደ ለጋራ ጥቅም ማዋል ይቻላል ብለዋል። “የግል ማንነታችንን በተጋነነ መልኩ ለማስኬድ ስንሞክር በራሳችን ማንነት ውስጥ ብቻ ታጥረን እና ተዘግተን እንድንኖር የማድረግ አደጋ ውስጥ ይከተናል” ያሉት ቅዱስነታቸው “ማንነታችን ባህላችንን፣ ብሄራዊነታችንን፣ ታሪካችንን፣ ጥበባችንን ወዘተ አቅፎ የያዘ በመሆኑ የተነሳ አንጡራ የሆነ ሐብታችን ነው ያሉት ቅዱስነታቸው እያንዳንዱ ሀገር የራሱ የሆነ ማንነት ያለው ቢሆንም ቅሉ ማንነቱ ውይይት ከማድረግ ባሕል ጋር የተዋሃደ መሆን አለበት ብለዋል። ይህ ወሳኝ የሆነ ነገር ነው፣ ማነኛውም ውይይት የሚጀምረው ከራስ ማንነት በመነሳት ሲሆን ከራሳችን ማንነት ተነስተን የምናደርገው ውይይት ደግሞ ከሌላው ማንነት የላቀ ነገር ለመቀበል የሚያስችል እና ለውይይት በር የሚከፍት ነው” ብለዋል።

በአውሮፓ ውስጥ የሉዋላዊነት እና መርህ አልባ ሕዝባዊ ወገኝተኝነት  እየተንሰራፋ መምጣቱ ያስጨንቀኛል

“በአሁኑ ወቅት በአውሮፓ አህጉር ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ አገራት አህጉራዊ መዋቅሩን ከማጠናክር ይልቅ እያንዳንዱ አገር ሉዋላዊነቱን ብቻ ለማረጋገጥ የሚያደርገው ሩጫ እና ሕዝባዊ ወገኝተኝነት መንፈስ እየተንሰራፋ መምጣቱ ያስጨንቀኛል” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም በአህጉሩ ውስጥ የሚገኙ አገራት ሕብረት ከመፍጠር ይልቅ የመለያየት ፍላጎቶቻቸውን እያጎለበተ ሊመጣ እንደ ሚችል የገለጹት ቅዱስነታቸው እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ1934 ዓ.ም አከባቢ ከነበረው ከናዚ አስተሳሰብ ጋር የሚመሳሰል ሐስተሳሰብ እና ባሕሪይ እንደ ሆነ ገልጸው “ቅድሚያ ለእኔ፣ ለእኔ፣ ለእኔ” የሚል አስተሳሰብ እየተንሰራፋ በመምጣቱ ፍርሃትን የሚፈጥር አስተሳሰብ ነው ብለዋል። ሉዋላዊነት ያለምንም ጥርጥር መከበር ያለበት መሰረታዊ ነገር ነው በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ነገር ግን ሉዋላዊነት ሙሉ በሙሉ ጠንካር በሆነ መልኩ ጥበቃ ሊደረግለት የሚችለው ደግሞ ከሌሎች ከአውሮፓ ሕበረት አገራት ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች በመሆኑ የተነሳ ሕበረትን ማጠናከር ያስፈልጋል፣ ሕብረት ከመፍጠር ይልቅ ሉዋላዊነትን በተጋነነ መልኩ አጥብቆ መያዝ በራሱ ከታሪክ እንደ ምንረዳው ግጭቶችን ይፈጥራል ብለዋል።

ስደተኞችን በተመለከተ በቅድሚያ የሰው ልጅ በሕይወት የመኖር መብት ሊከበር ይገባዋል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በነሐሴ 02/2011 ዓ. ም Vatican Insider በመባል ከሚታወቀው ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆያት ከዳሰሱዋቸው ሐሳቦች ውስጥ ወቅታዊውን የስደተኞችን ጉዳይ የተመለከቱ ሐሳቦችን መዳሰሳቸው የተገለጸ ሲሆን ስደተኞችን በተመለከተ በቅድሚያ የሰው ልጅ በሕይወት የመኖር መብት ሊከበር ይገባዋል ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን ስደተኞችን መቀበል፣ ማገዝ፣ ማስተማር እና ከማሕበርሰቡ ጋር ማዋሃድ ይገባል ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን ከሁሉም በላይ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ደግሞ ማንም ሰው በሕይወት የመኖር መብት ሊከበርለት ይገባል ብለዋል። የስደተኞችን ፍልሰት በምናስብበት ወቅት ቅድሚያ በመስጠት ልናስተውለው የሚገባን ጉዳይ ቢኖር ስደተኞች ፈልሰው የመጡባቸውን አገራት ሁኔታ መመልከት ተገቢ መሆኑን ገልጸው ስደተኞች ጦርነትን እና ረሃብን በመሸሽ ከአገራቸው እንደ ሚሰደዱ ማሰብ ያስፈልጋል ብለዋል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
09 August 2019, 15:41