ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ “ፍቅር ሁልጊዜም ቢሆን አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው” አሉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር እሁድ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የአገር ጎብኝዎች በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው የቅዱስ ወንጌለ አስተንትኖ እንደ ሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህ መሰረት በነሐሴ 19/2011 ዓ.ም ቅዱስነታቸው ያሰሙት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ በእለቱ ከሉቃስ ወንጌል 13፡22-30 ላይ ተወስዶ በተነበበውና “በጠባቧ በር ለመግባት ተጣጣሩ” በሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጥ ላይ መሰረቱን ያደረገ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን “ፍቅር ሁልጊዜም ቢሆን አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው” ማለታቸው ተገልጹዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራቸስኮስ በእለቱ ያደረጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ!

የዛሬው ቅዱስ ወንጌል (ሉቃ 13፡22-30) ኢየሱስ በሚያልፍባቸው ከተሞች እና መንደሮች እያስተማረ ሁላችnንም ለማዳን በመስቀል ላይ ወደ ሚሰቀልበት ወደ ኢየሩሳሌም እየሄደ እንደ ነበረ ይተርክልናል። በእዚህ ሁኔታ ላይ በነበረበት ወቅት አንድ ሰውም ቀርቦ፣ “ጌታ ሆይ፤ የሚድኑት ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸውን?” አለው። የሚድኑት ስንቶቹ ናቸው፣ የማይድኑትስ ስንቶቹ ናቸው. . .? የሚል ክርክር በወቅቱ የነበረ ሲሆን እናም ይህንን በተመለከተ በመጽሐፍ ላይ ተመርኩዘው የተለያዩ መነገዶችን ተጠቅመው የየራቸውን ትርጉም ይሰጡ ነበር። ኢየሱስ ግን የእነርሱን ሕግጋት በመሻር የሚድኑት “ጥቂቶች ናቸው” በማለት በሐሃዝ በማስቀመጥ ይልቁን የአሁኑን ጊዜ በአግባቡ እንድንጠቀም በመጋበዝ መልሱን በኃላፊነት ላይ ያደርገዋል። “በጠባቧ በር ለመግባት ተጣጣሩ፤ እላችኋለሁ፤ ብዙዎች ለመግባት ይፈልጋሉ ነገር ግን አይሆንላቸውም” (ሉቃ 13፡24) በማለት ይመልስላቸዋል። በእነዚህ ቃላት ፣ ኢየሱስ የቁጥሮች ጥያቄ አለመሆኑን በመግለጽ፣ መንግስተ ሰማይ ውስጥ “ውስን የሆነ ቁጥር” እንደሌለ ግልፅ አድርጓል! ነገር ግን ትክክለኛውን የመተላለፊያ መንገድ ማቋረጥ ግድ እንደ ሚል፣ ይህ ትክክለኛው የመተላለፊያ መንገድ ለሁሉም ክፍት የሆነ ነገር ግን በጣም ጠባብ የሆነ መተላለፊያ እንደ ሆነ በግልጽ ይነግራቸዋል። እንግዲህ ችግሩ ያለው እዚህ ላይ ነው። ኢየሱስ “አዎ ፣ አይዞን አትጨነቅ እርግጠኛ ሁን፣ ቀላል ነው፣ በጣም ምርጥ የሆነ አውራ ጎዳና አለ፣ በመጨረሻም አንድ ትልቅ በር አለ…” በማለት ሊያታልለን አይፈልግም። እንድህ ሊለን በፍጹም አይፈልግም፣ አንድ ጠባብ በር እንዳለ ነው የሚነግረን። ነገሮቹን እንዳለ ቁልጭ አድርጎ ነው የሚነግረን በሯ ጠባብ እንደ ሆነች ይገልጻል። ኢየሱስ ነገሮቹን እንዳለ ያስቀምጣቸዋል፣ በሯ ጠባብ እንደ ሆነች ያናገራል። አንድ ለመዳን የፈለገ ሰው እግዚአብሔርን እና ባልንጀራውን መውደድ አለበት ፣ እናም ይህ ምቾት የሚሰጥ ነገር አይደለም! እርሱም እንደ “ጠባብ በር” ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል፣ ምክንያቱም አስፈላጊ ነገር በመሆኑ! ፍቅር ሁል ጊዜ አስፈላጊ ነገር ነው፣ ቃል ኪዳን መግባትን ይጠይቃል ፣ በእውነቱ ከፍተኛ የሆነ “ጥረት” የሚጠይቅ በቅዱስ ወንጌል ላይ መሰረቱን ያደርገ ቁርጥ ውሳኔ እና ጽናት የሚጠይቅ ነው። ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ “መልካሙ የእምነት ተጋድሎ” (1ጢሞ 6፡12) በማለት ይገልጸዋል። እግዚአብሔርን እና ሌሎችን መውደድ የእለት ተዕለት ጥረት ይጠይቃል።

ኢየሱስ ይህንን ሁኔታ በተሻለ መልክ ለመግለጽ ይቻለው ዘንድ አንድ ምሳሌ ይነግራቸዋል። አንድ የቤት ባለቤት ስለነበረ ጌታ ይናገራል። ቤቱ የዘላለምን ሕይወት ያመለክታል ፣ ያም ድነት ነው። እዚህ ጋር የበሩ ምሳሌ ተመልሶ በመምጣት “የቤቱ ባለቤት ተነሥቶ በሩን ከቈለፈ በኋላ በውጭ ቆማችሁ፣ ጌታ ሆይ፤ ክፈትልን እያላችሁ በሩን ማንኳኳት ትጀምራላችሁ። “እርሱ ግን፣ ‘ማን እንደሆናችሁና ከየት እንደመጣችሁ አላውቅም’ ብሎ ይመልስላችኋል። ከዚያ በኋላ እነዚህ ሰዎች የቤቱን ባለቤት “ ከአንተ ጋር አብረን በልተናል፤ ጠጥተናል፤ በአደባባያችንም አስተምረሃል” በማለት ለቤቱ ባለቤት እውቅና ለመስጠት ይሞክራሉ። “ያንን አስተምህሮ በምትሰጥበት ወቅት እኔ በእዚያ ስፍራ ነበረኩኝ . . .” ነገር ግን ጌታው እነሩስን እንደ ማያውቃቸው ደጋግሞ ይነግራቸዋል፣ “አናተ አመጸኞች” በማለት ይጠራቸዋል። ችግሩ ያለው እንግዲህ እዚህ ጋር ነው። ጌታ እኛን የሚያውቀን በመጠሪያ ማዕረጎቻችን ላይ ተመስርቶ አይደለም “ተመልከት ጌታ ሆይ እኔ የእዚያ ማኅበር አባል ነበረኩኝ፣ የእከሌ ጉደኛ ነበርኩኝ፣ እከሌ የሚባል ካርዲናል ጓደኛ ነበርኩኝ፣ እከሌ የሚባል ካህን ጓደኝ ነበርኩኝ” ማለት ለእርሱ ብዙም ትርጉም አይሰጥም።  በእርሱ ዘንድ ማዕረግ ምንም ዓይነት ቦታ የለውም። ጌታ የሚያውቀን በትህትና በተማላ ሕይወታችን፣ መልካም በሆነ ሕይወታችን፣ በእምነት የተሞላ እና ያ እምነት ወደ ተግባር የተለወጠበት ሕይወታችንን ነው የሚመለከተው።

ለእኛም ክርስቲያኖች፣ ይህ ማለት ከኢየሱስ ጋር እውነተኛ ቁርኝት እንድንመሠርት፣ እንድንጸልይ፣ ወደ ቤተክርስቲያን በመሄድ ቅዱሳን ምስጢራትን መሳተፍ እና በቃሉ ሕይወታችንን እንድንመግብ መጠራታችንን ማወቅ ማለት ነው። ይህ በእምነት እንድንጸና ያደርገናል፣ ተስፋችንን ያለመልማል፣  ለጋሾች እንድንሆን ያደርገናል። እናም በእዚህ ሁኔታ በእግዚአብሔር ጸጋ በመታገዝ ሕይወታችንን ለወንድሞቻችን አገልግሎት ማዋል እንችላለን ፣ እናም ሁላችንም ክፋትንና ኢፍትሃዊነትን እንዋጋለን።

ይህንን በተግባር ላይ ማወል እንችል ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትርዳን። እርሷ ጠባብ በር በነበረው በኢየሱስ ውስጥ አልፋለች። በሙሉ ልቡ በደስታ ተቀብላው እና በሕይወቷ ውስጥ በየቀኑ ትከተለው ነበር፣ ምንም እንኳን ነገሮች ሁሉ ግልጽ ባይሆኑላትም እንኳን ነፍሷን ስይፍ ቢወጋውም እርሱን በእየለቱ ተከተለው ነበር።  እኛ እርሷን “የሰማይ ደጅ” ብለን የምንጠራት በዚህ ምክንያት ነው፣ ማርያም  የሰማይ በር፣ የኢየሱስን ሕይወት በትክክል የሚያመልክት በር ናት፣ ወደ እግዚአብሔር ልብ የምንገባበት በር፣ በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር ግን ለሁላችንም ክፍት የሆነ ወደ እግዚኣብሔር መንግሥት የምትመራን በር ናት።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
25 August 2019, 16:03