ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የሕልውናችን ምንጭ የሆነውን የአማዞን ደን ከውድመት መከላከል ይገባል። ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የሕልውናችን ምንጭ የሆነውን የአማዞን ደን ከውድመት መከላከል ይገባል። 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የሕልውናችን ምንጭ የሆነውን የአማዞን ደን ከውድመት መከላከል ይገባል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በነሐሴ 19/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ እንደ ተለመደው በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ክብር በመስጠት ከሚደገሙ ጸሎቶች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰውን “የእግዚኣብሔር መልአክ ማርያምን አበሰራት” የሚለውን ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኋላ ለዓለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት በአሁኑ ወቅት ብራዚል በአማዞን ደን ላይ በተከሰተው የእሳት አደጋ ቅዱስነታቸው እጅግ እንዳሳሰባቸው የገለጹ ሲሆን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና በመጫወት ይህንን የደን ቃጠሎ ያስወግዱ ዘንድ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል። የአማዞን ደን ለመላው የአለማችን ሕዝቦች የሕልውና ምንጭ መሆኑን የገለጹት ቅዱስነታቸው ችግሩን በእዚህ አግባብ በመረዳት አስፈላጊውን ጥበቃ ማደረግ እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው ማጠቃለያ ላይ በእዚያው በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እርሳቸው ዘወትር እሁድ እለት በእለቱ ቅዱስ ወንጌላ ላይ ተንተርሰው የሚያደርጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ለማዳመጥ ለተሰበሰቡ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና ለአገር ጎብኝዎች ሰላምታቸውን አቅርበው እና እንደተለመደው “እባካችሁን ለእኔ መጸለይ እንዳትዘነጉ” ካሉ በኋላ ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተው የእለቱ ዝግጅት መጠናቀቁን ከደርሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

25 August 2019, 16:07