ፈልግ

የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎትን ባቀረቡበት ወቅት፣ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎትን ባቀረቡበት ወቅት፣ 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በቅ. ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙት በሙሉ ሰላምታን አቅርበዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እሁድ ነሐሴ 12 ቀን 2011 ዓ.ም፣ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ላይ ለተሰበሰቡት ምዕመናን ካቀረቡት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ በመቀጠል በስፍራው ለተገኙት፣ ከኢጣሊያ እና ከሌሎች አገሮች ለመጡት መንፈሳዊ ነጋዲያን በሙሉ ሰላምታቸውን አቅርበውላቸዋል። ልዩ ልዩ የቤተክርስቲያን ማሕበራት አባላት የተገኙ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል ከካናዳ የመጡ የመለኮታዊ ፍቅር ማሕበር አባላት እንዲሁም ከፖርቱጋል እና ከፖላንድ የመጡ ምዕመናን የቅዱስነታቸውን የስብከተ ወንጌል አስተምሕሮ የተካፈሉ መሆናቸው ታውቋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመጨረሻም በአደባባዩ ለተገኙት በሙሉ መልካም ዕለተ ሰንበትን ተመኝተውላቸው፣ ምዕመናኑ በሙሉ በጸሎታቸው እንዲያስታውሷቸው አደራ ብለዋል።

19 August 2019, 17:53