ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ማንም ሰው ሊገለል አይገባውም” አሉ

ሰደተኞች ብቻ ሳይሆኑ በአጠቃላይ ማንም ሰው ሊገለል አይገባውም።

የዛሬው ዓለማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ጭካኔ በተሞላው መልኩ የጥቂት ሰዎችን የበላይነት እያረገጋጠ እና በተቃራኒው ብዙሃኑን እያገለለ መጥቱዋል። በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ውድ የሆኑ የተፈጥሮ እና አእምሮአዊ አብቶቻቸው በጥቂት የተወሰኑ ልዩ መብት ባላቸው ሰዎች ጥቅም ላይ በመዋል ላይ ይገኛሉ።

ጦርነቶች በአንዳንድ የአለም ክልሎች ውስጥ ብቻ ይካሄዳሉ፣ ሆኖም የጦር መሣሪያዎች በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ውስጥ የሚመረት እና ወደ ሌሎች አገሮች የሚሸጡ ሲሆን በተሸጡ የጦር መሣሪያዎች የተነሳ በሚከሰቱ ግጭቶች ምክንያት የሚሰደዱ ስደተኞችን ተቀብለው ለማስተናገድ ግን ፈቃደኛ አይደሉም።

ሁልጊዜም ቢሆን ዋጋውን የሚከፍሉት ደግሞ በጣም ለጥቃት ተገላጭ የሆኑ አቀመ ደካማ የሚባሉት ድሆች ሲሆኑ፣ በማዕዳ ላያ ተቀምጠው እንዳይበሉ የተከለከሉ እና ከሐብታሞቹ ድግስ የሚጣለውን ፍራፋሪ ለመብላት የሚጓጉ ድሆች ናቸው።

ወደ ፊት የምትጓዝ ቤተክርስቲያን ወደ ፊት በመሄድ በድፈረት ሌሎችን ለማገዝ የምትችል ሲሆን የወደቁትን ሰዎች ትፈልጋለች፣ በመስቀለኛ መንገድ ላይ የቆሙ ሰዎችን እና በማኅበርሰቡ የተገለሉትን ሰዎች ለመሰብሰብ ትችላለች።

እውነተኛ ልማት የወደፊቱን ነገር ከግምት ባስገባ መልኩ ፍሬያማና ሁሉን አካታች በሆነ መልኩ የሚደረግ ልማት ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ

03 July 2019, 15:31