ፈልግ

በሩሲያ የሴቨርሞርስክ ከተማ ውስጥ የባሕር ሰርጓጅ መርከብ በሩሲያ የሴቨርሞርስክ ከተማ ውስጥ የባሕር ሰርጓጅ መርከብ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በራሽያ ባሕር ሰርጓጅ መርከብ ላይ በደረሰው አደጋ ማዘናቸውን ገለጹ።

በቅርቡ በአንድ የራሻ ባሕር ሰርጓጅ መርከብ ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ በተጎዱ ሰዎች እጅግ ማዘናቸውን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ገለጹ። በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ሰዎች ነብስ ይማር፣ በአደጋው የቅርብ ወዳጆቻቸውን ላጡ ቤተሰቦች ደግሞ መጽናናትን መመኘታቸውን ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አቅቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በቅርቡ በራሻ በባሕር ወለል ውስጥ ሆና የምርምር ተግባር እያከናወነች በነበረች ባሕር ሰርጓጅ መርከብ ላይ በደርሰው የእሳት አደጋ በውስጡ የነበሩ 14 መርከበኞች ሕይወት ማለፉ የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በቅድስት መንበር የእህትመት እና የዜና ማሰራጫ ተቋም ምክትል ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ አሌክሳንድሮ ጂዞቲ በኩልት ይፋ ባደረጉት የሐዘን መግለጫ በአደጋ ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ያጡ ቤተሰቦች ለእነርሱ ያላቸውን አጋርነት መግለጻቸው ታውቁዋል።

ባለፈው ሰኞ ሰኔ 14/2011 ዓ.ም በባሕር ወለል ውስጥ እለታዊ በሆነ መልኩ የምርምር ሥራዋን በማከናወን ላይ በነበረች አንድ የራሻ የባሕር ሰርጓጅ መርከብ ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ የተነሳ በውስጡ የነበሩት ባሕርተኞች በጪስ ታፍነው ሕይወታቸው እንዳለፈ የተገለጸ ሲሆን የአገሪቷ ሚንስትር ጉዳዩን በተመለከተ ገና ዝርዝር የሆነ መግለጫ ያልሰጠበት ጉዳይ ሲሆን ነገር ግን ከአገሪቷ የዜና ተቋማት የሚወጣው ዜና እንደ ሚያመለክተው እሳቱ ሊነሳ የቻለው ባሕር ሰርጓጅ መርከቦች ልዩ ለሆነ አገልግሎት በሚጠቀሙባቸው በኒውክለር በተሰሩ ፈንጂዎች ምክንያት እንደ ሆነ በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።

የራሻ ፐሬዚዳንት የሆኑ ቪላድሚር ፑቲን ጉዳዩን በተመለከተ አንድ አጣሪ ቡድን በቅርቡ ማዋቀራቸው የተገለጸ ሲሆን የራሻ የመከላከያ ሚንስትር አደጋውን በተመለከተ በቅርቡ ባወጣው መግለጫ ከባሕር ስርጓጅ መርከብ ውስጥ በሕይወት የተረፉ መርከበኞች እንዳሉ መገለጻቸው ታወቁዋል።

04 July 2019, 13:33