ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፋርንቸስኮስ “ሚዛናዊ የሆነ ፍትህ” ይረጋገጥ ዘንድ እንጸልይ አሉ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በየወሩ ለወሩ የሚሆን የጸሎት ሐሳብ በቪዲዮ መልእክት ይፋ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። በዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው ለሐምሌ ወር 2011 ዓ.ም ያቀረቡት የጸሎት ሐሳብ “ሚዛናዊ የሆነ ፍትህ” ይረጋገጥ ዘንድ እንጸልይ ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለማችን በሚገኙ የፍትህ መስጫ ተቋማት ውስጥ በሚስተዋሉት የተዛባ የፍትህ አሰጣጥ ሂደቶች የተነሳ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች እየተሰቃዩ እንደ ሚገኙ ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው ገልጸዋል።

የእዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ቅዱስነታቸው በእዚሁ ለሐምሌ ወር ይሆን ዘንድ ባቀረቡት የጸሎት ሐሳብ የሚከተለውን ብለዋል. . .

ዳኞች የሚሰጡዋቸው ውሳኔዎች ወይም የሚያደርጉዋቸው ውሳኔዎች በዜጎች መብትና ንብረት ላይ ተፅዕኖ አለው። ዳኞች በነጻ ውሳኔ የመስጠት መብታቸውን በመጫን እና ወገኝተኛ የሆነ ውሳኔዎችን እንዲሰጡ ጫና በመፍጠር በሚሰጡት ውሳኔ ላይ ተጽእኖ ለመፍጠር ከሚደረጉ ተግባራት ዳኞች መቆጠብ ይኖርባቸዋል። ዳኞች በእውነት ላይ ፈጽሞ በጭራሽ የማይደራደረውን የኢየሱስን ምሳሌ መከተል ይኖርባቸዋል። ፍትህን ለማስፈን የሚተጉ ሰዎች በንጹህ ልብ እና አቋም እንዲሠሩ እና በዓለም ላይ እየታየ ያለው ኢፍትሃዊነት ያበቃ ዘንድ እንጸልይ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእዚህ ለነሐሴ ወር የሚሆን የጸሎት ሐሳብ ባቀረቡበት ወቅት የፍትህ መስጫ ተቋማት ፍትህ ይሰፍን ዘንድ የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ፣ ሰብአዊ መብትን እንዲያከብሩ እና ሚዛናዊ የሆነ ፍርድ ይሰጡ ዘንድ በሐምሌ ወር ልንጸልይላቸው የገባል ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለሐምሌ ወር 2011 ዓ.ም የሚሆን የጸሎት ሐሳብ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት ጨምረው እንደ ገለጹት በመላው ዓለም ሚዛናዊ የሆነ የፍርድ አሰጣጥ ሂደት ይኖር ዘንድ መላው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ለሕግ አውጪ፣ ለሕግ ተርጓሚ እና ለሕግ አስፈጻሚ አካላት በሐምሌ ወር ጸሎት ይደረግ ዘንድ የተማጸኑ ሲሆን እነዚህ አካላት የሚያደርጉዋቸው ውሳኔዎች እና የሚሰጡዋቸው ፍርዶች ትክክለኛ ዓላማውን በጠበቀ መልኩ እና ጥምር የሆኑ መስፈርቶችን ከግምት ባስገባ መልኩ መከናወን እንደ ሚገባቸው ጨምረው ገልጸዋል። ቅዱስነታቸው የሐምሌ ወር የጸሎት ሐሳብ ማነኛውም የፍርድ አሰጣጥ ሂደት እና ፍትሃዊ ውሳኔ የሰው ልጆችን ማዕከል ባደረገ መልኩ ሊተገበር እንደ ሚገባ የሚገልጽ መልእክት ያዘለ ሲሆን ፍትህ ለሰዎች አገልግሎት መዋል ይኖርበታል፣ ሁልጊዜ የሰውን ሰብአዊ መብት ባከበረ መልኩ መከናወን ይገባዋል የሚል እንድምታ የያዘ መልእክት ነው።

በተጨማሪም ዳኞች እና ፍርድ ቤቶች “በእውነት ላይ በፍጹም የማይደራደረውን” የኢየሱስን አብነት በመከተል ለእውነት እና ስለእውነት ብቻ፣ የሰው ልጆችን ሰብዓዊ ክብር ከግምት ባስገባ መልኩ ገቢራዊ ሊሆን እንደ ሚገባው ጨምረው ገልጸዋል።

በሙሳና ትጽእኖ ሥራ ሆነው የምዲረጉ ማነኛቸውም የፍርድ አሰጣጥ ሂደቶች ለሕዝቦች እና በአጠቃላይ በአገራት የተቀናጀ እድገት ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እንደ ሚፈጥሩ የሚታወቅ ሲሆን ብዙን ጊዜ በዓለማችን ላይ የፍትህ መዛበት የሚከሰተው በሙስና ሰበብ በመሆኑ የተነሳ ሙስና በሁሉም ሁኔታዎች በተለይም በፍትህ አሰጣጥ ሂደት ውስጥ እንዳይገባ ጥንቃቄ ማደረግ ይገባል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!

 

 

04 July 2019, 11:35