ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በዩክሬይን የምስራቂያን የስረዓተ አምልኮ ተከታይ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ታላቁ ሊቀ ጳጳስ በሆኑት በኬቪ ጋሊች ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በዩክሬይን የምስራቂያን የስረዓተ አምልኮ ተከታይ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ታላቁ ሊቀ ጳጳስ በሆኑት በኬቪ ጋሊች ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት  

የዩክሬን የግሪክ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ተወካዮች ከር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ጋር በቫቲካን ተገናኙ።

በዮክሬይን ውስጥ የሚገኙትን የምስራቃዊያን የስርዓተ አምልኮ ተካታይ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ያለባቸውን ውስብስብ የሆነ ሁኔታ ለመፍታት ያስችላቸው ዘንድ ለሁለት ቀናት ያህል ስብሰባ ለማደረግ በዛሬው እለት ማለትም በሰኔ 28/2011 ዓ.ም ወደ ቫትካን ማቅናታቸው የተገለጸ ሲሆን ዛሬ ሰኔ 28/2011 ዓ.ም ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መመካከራቸው ተገልጹዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በዮክሬይን ውስጥ የሚገኙትን የምስራቃዊያን የስርዓተ አምልኮ ተካታይ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በቫቲካን የተገኙት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባቀረቡላቸው ጥሪ መሰረት እንደ ሆነ የተገለጸ ሲሆን ይህ በዩክሬይን የምስራቂያን የስረዓተ አምልኮ ተከታይ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ታላቁ ሊቀ ጳጳስ በሆኑት በኬቪ ጋሊች የተመራ ጉብኝት ሲሆን ከእርሳቸው ጋር የአገሪቷ ቋሚ ሲኖዶስ አባላት አብረው መገኘታቸውም ተገልጹዋል።

በአሁኑ ወቅት በዩክሬይን የምትገኘው የምስራቃዊያኑን የስረዓተ አምልኮ በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ውስብስብ የሆነ ችግሮች እያጋጠሙዋቸው በመሆኑ የተነሳ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዮክሬይን ለምትገኘው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ያላቸውን አጋርነት ለመግለጽ በማሰብ የተደረገ ጥሪ እንደ ሆነ የተገለጸ ሲሆን በዮክሬይን እና ከዩክሬይን ውጭ ሐዋርያዊ ተግባራችውን በማከናወን ላይ ለሚገኙ የምስራቃዊያን ስረዓተ አምልኮ በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ሐዋያዊ ተግባራቸውን በሚያከናውኑበት ወቅት የሚያጋጥማቸውን ተግዳሮቶች በትዕግስት ይወጡ ዘንድ ለማሳሰብ እና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና መላው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ለዩክሬይን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ያላቸውን አጋርነት ለመግለጽ ታስቦ የተጠራ የሁለት ቀን ስብሰባ ነው።

በተለያዩ ምክንያቶች እና ጦረነቶች የተነሳ ከፍተኛ የሆነ ማኅበራዊ ቀውስ በሚታይባት በዩክሬይን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእርሳቸው ጥረት ሰብዓዊ የሆነ እርዳታ በማደረግ ላይ እንደ ሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን በአውሮፓ አህጉር የሚገኙትን መላውን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ባሳታፈ መልኩ፣ ሌሎች አብያተ ክርስቲያናትንም ጭምር ባሳተፈ መልኩ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ እርዳታ በማደረግ ላይ እንደ ሚገኙም ይታወቃል።

ለሰላም የሚደረግ ጸሎት

ዩክሬይን በጦርነት ውስጥ በነበረችበት ወቅት ከእዚህ ከገባችበት ውጥቅጡ ከወጣ ሁኔታ ውስጥ ነጻ በመውጣት ሰላሟን መልሳ ትጎናጽፍ ዘንድ ለማስቻል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ማቀርባቸው የሚታወስ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩም በዩክሬይን ሰላም ይረጋገጥ ዘንድ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን እና እንዲሁም በጎ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች በሙሉ ጸሎት ያደርጉ ዘንድ ቅዱስነታቸው መማጸናቸውም ይታወሳል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
05 July 2019, 13:41