ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሮማኒያ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ከማቴዎ ቡሩኒ ጋር ሰላምታ በተለዋወጡበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሮማኒያ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ከማቴዎ ቡሩኒ ጋር ሰላምታ በተለዋወጡበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለቫቲካን መገናኛ ብዙኃን አዲስ ዳይሬክተር ሾሙ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዛሬ ሐምሌ 11/2011 ዓ.ም አቶ ማቴዎ ብሩኒ የቫቲካን መገናኛ ብዙኃን ዳይሬክተር አድርገው መሾማቸው የተገለጸ ሲሆን ከእዚህ ቀደም ለአንድ አመት ያህል ይህንን የቫቲካን የመገናኛ ብዙሃን ጽሕፈት ቤት በጊዜያዊ ምክትል ዳይሬክተር ደረጃ ሲያስተዳድሩ የቆዩት አቶ አሌክሳንድሮ ጂዞቲ የቫቲካን ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ዳይሬክተር አድርገው መሾማቸው ተገልጹዋል።

የእዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በእዚህ ሹመት መሰረት የእንግሊዚ አገር ተወለጅ የሆኑት አቶ ማቴዎ ብሩኒ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና የቅድስት መንበር የሕትመት እና የዜና መስጫ አግልግሎት ጽሕፈት ቤት ዳይሬክተር እና ቃል አቃባይ ሆነው እንደ ሚያገለግሉ ተያይዞ ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን አዲሱ ዳይሬክተር ከመጪው ሐምሌ 14/2011 ዓ.ም ጀመሮ ሥራቸውን በይፋ እንደ ሚጀምሩ ተገልጹዋል።

18 July 2019, 15:19