ፈልግ

የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቤነዲክቶስ 16ኛ፣ በሮም አቅራቢያ በሚገኝ በካስቴል ጋንዶልፎ የአትክልት ሥፍራ፤ የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቤነዲክቶስ 16ኛ፣ በሮም አቅራቢያ በሚገኝ በካስቴል ጋንዶልፎ የአትክልት ሥፍራ፤ 

የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቤነዲክቶስ 16ኛ፣ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት የበጋ ወራት መኖሪያን ጎበኙ።

የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳስት ቤነዲክቶስ 16ኛ፣ ሐሙስ ሐምሌ 18 ቀን 2011 ዓ. ም.  በሮም አቅራቢያ በሚገኝ ካስቴል ጋንዶልፎ የተባለ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት የበጋ ወቅት የዕረፍት ስፍራን ጎብኝተውል። በአትክልት ሥፍራው የመቁጠሪያ ጸሎትን ማድረሳቸውን ከቫቲካን የዜና አገልግሎት የደረሰን ዘገባ አስታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቤነዲክቶስ 16ኛ ከዚህ በፊት፣ በርዕሠ ሊቃነ ጵጵስና ሐዋርያዊ አገልግሎታቸው ወቅትም ለበርካታ ጊዜ ወደዚሁ ጸጥታ በሰፈነበት እና ቀዝቃዛ አየር ወደሚነፍስበት፣ ወደ ካስተል ጋንዶልፎ ሄደው የበጋ ወራት የዕረፍት ጊዜአቸውን ያሳልፉ እንደነበር የሚታወስ ነው።

የቅድስት መንበር ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍል ዳይሬክተር የሆኑት ክቡር አቶ ማቴዎ ብሩኒ እንዳስታወቁት፣ የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቤነዲክቶስ 16ኛ ለጸሎት ወደ አትክልት ስፍራ ከመሄዳቸው አስቀድመው ካስቴል ጋብዶልፎ በተባለ ሥፍራ በሚገኝ ሐዋርያዊ ቤተ መንግሥት ቆይታ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።         

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቤነዲክቶስ 16ኛ ሐሙስ ሐምሌ 18 2011 ዓ. ም. ወደ ካስቴል ጋንዶልፎ ካደረጉት ጉብኝት በመቀጠል ሮካ ዲ ፓፓ በተባለ ሥፍራ በሚገኘው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደርሰው ጸሎት ማድረሳቸውን የቅድስት መንበር ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍሉ አስታውቆ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ፣ ብጹዕ አቡነ ራፋኤሎ ማርቲኔሊ በፍራስካቲ ባዘጋጁላቸው የእራት ግብዣ ላይ መገኘት ታውቋል።

ብጹዕ አቡነ ራፋኤሎ ማርቲኔሊ ለቫቲካን ሬዲዮ እንዳስታወቁት፣ የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቤነዲክቶስ 16ኛ ወደ ሀገረ ስብከታቸው ያደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት አስደሳች እና ታሪካዊ ትዝታን የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል። ብጹዕ አቡነ ማርቲኔሊ አክለውም ርዕሠ ሊቃነ ጳጳስት ቤነዲክቶስ በዘወትር የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ በመታገዝ፣ ይህን የእግዚአብሔርን ስጦታ ከሌሎች ሰዎች ጋር በደስታ የሚጋሩ ናቸው ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቤነዲክቶስ 16ኛ ሐሙስ ሐምሌ 18 ቀን 2011 ዓ. ም. በካስቴል ጋንዶልፎ እና በአካባቢው ያደረጉትን አጭር ጉብኝት ፈጽመው በቫቲካን ውስጥ ወደሚገኘው፣ ማተር ኤክልሲያ ገዳማችው በሰላም መመለሳቸውን የቅድስት መንበር ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍል አስታውቋል።

ይህን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
27 July 2019, 16:44