ፈልግ

በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ላይ ከተሰበሰቡት ምዕመናን በከፊል፣ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ላይ ከተሰበሰቡት ምዕመናን በከፊል፣ 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በሰ. ኮሪያ የታየውን የመልካም ግንኙነት ባሕልን አወድሰዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ትናንት እሁድ ሰኔ 23 ቀን 2011 ዓ. ም. በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ላይ ለተሰበሰቡት ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የአገር ጎብኝዎች ካቀርቡት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ በማስከተል አጭር ንግግር አሰምተዋል። በዚህ ንግግራቸው ቅዱስነታቸው በሰሜን ኮሪያ የታየውን የመልካም ግንኙነት እና የመቀራረብ ባሕልን አወድሰዋል። ለዚህም ፈቃደኛ እና ቀዳሚ ተዋናይ ሆነው ለተገኙትን ልባዊ ምስጋናቸውን እና ሰላምታቸውን አቅርበው ይህም በሰሜን ኮሪያ ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለማችን ለማስፈን በሚደረገው የሰላም ጥረት ትልቅ አስተዋጽዖ እንዳለው ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን በመቀጠል በተያዘው የሰኔ ወር ለዓመታዊ የዕረፍት ጊዜ ዝግጅት በማድረግ ላይ ለሚገኙት በሙሉ፣ ለቤተሰቦቻቸውም ጭምር መልካም የዕረፍት ጊዜን ተመኝተውላቸዋል። በአውሮጳ እና በሌሎችም የዓለማችን ክፍሎች በተጀመረው የበጋ ወራት፣ በከፍተኛ ሙቀት የሚሰቃዩትን ሕሙማን፣ አዛውንትን እና ከባድ የጉልበት ሥራን በመሥራት ላይ የሚገኙትን በጸሎታቸው የሚያስታውሱ መሆናቸውን ገልጸው ለዚህ በመዳረግ ማንም ለምዝበዛ እንዳይጋለጥ አሳስበዋል። ቀጥለውም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተሰበሰቡትን በሙሉ፣ የሮማ እና አካባቢው ምዕመናንን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያንን፣ ከተለያዩ አካባቢዎች ለመጡት የቤተሰብ ክፍሎችን እና የቁምስና መንፈሳዊ ማህበራት ዓባላት በሙሉ ሰላምታቸውን አቅርበውላቸዋል። በተለይም ለቅድስት ኤልሳቤጥ ማሕበር ደናግል ሰላምታቸውን አቅርበው ከፖላንድ ለመጡት መንፈሳዊ ነጋዲያን አድናቆታቸውን ችረው ሰላምታቸውን አቅርበውላቸዋል። በመጨረሻም በሥፍራው ለተገኙት በሙሉ መልካም ዕለተ ሰንበትን ከተመኙላቸው በኋላ ሳይዘነጉ በጸሎታቸው እንዲያስታውሷቸው አደራ በማለት ንግግራቸውን አጠቃልለዋል።

01 July 2019, 17:03