ፈልግ

በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተሰበሰቡት ምዕመናን፣ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተሰበሰቡት ምዕመናን፣  

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ቨነዙዌላን ላጋጠማት ቀውስ የጋራ ውይይት እንደሚያስፈልግ አሳሰቡ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከቅዱስ ወንጌል አስተንትኖአቸውን በማስከተል በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡት በሙሉ ባሰሙት ንግግር ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ቀውስ ያጋጠመውን የቨነዙዌላ ሕዝብ በጸሎታቸው   እንደሚያስታውሷቸው ገልጸው፣ በዚያች አገር የሚገኙ የፖለቲካ መሪዎች ለሕዝባቸው የሚበጀውን ማሰብ የሚችሉበት ልብ እንዲፈጠር፣ የሕዝቡም ስቃይ የሚያበቃበት ጊዜ እንዲመጣ፣ በአካባቢውም ሰላም እንዲወርድ የእግዚአብሔርን እገዛ መለመን እንዳለብን አሳስበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ከዚህም በመቀጠል ቅዱስነታቸው በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡት ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የአገር ጎብኝዎች ሰላምታቸውን ያቀረቡ ሲሆን በኢጣሊያ ውስጥ ከተለያዩ ሀገረ ስብከቶች እንዲሁም ከሌሎች የአካባቢ አገሮች ለመጡት መንፈሳዊ ነጋዲያን እና ወጣቶች ሰላምታቸው ያቀረቡላቸው ሲሆን በተጨማሪም የበጋ ወቅት ኮርስ በመከታተል ላይ የሚገኙትን የዘርዓ ክህነት ትምህርት ቤት መምህራንን፣ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን ያከናውኑትን የናዝሬቱ ቅድስት ቤተሰብ ማሕበር ደናግል እና የቅዱስ ሜሮን ትምህርታቸውን ላጠናቀቁ ለቤርጋሞ ሀገረ ስበከት ወጣቶች ሰላምታቸውን አቅርበውላቸዋል።

ቅዱስነታቸው በማከልም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙት የፖላንድ ምዕመናን ሰላምታቸውን አቅርበው በአደባባዩ ለተገኙትን መላው ምዕመናን እና ጎብኝዎች፣ አመታዊውን የራዲዮ ማርያ መንፈሳዊ ጉዞን ለማድረግ ወደ ፖላንድ፣ ቼስቶኮቫ ለሄዱት ሰላምታቸውን ካቀረቡ በኋላ በአደባባዩ የተገኙት በሙሉ በጸሎታቸው እንዲያስታውሷቸው አደራ ካሉ በኋላ መልካም ሰንበትን እና መልካም ምሳን ተመኝተውላቸዋል።     

15 July 2019, 16:49