ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከሮማኒያ መልስ ከጋዜጠኖች ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ በሰጡበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከሮማኒያ መልስ ከጋዜጠኖች ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ በሰጡበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “የአውሮፓ አህጉር ሕብረቱን ጠብቆ ይጓዝ ዘንድ ልንጸልይ ይገባል” አሉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ማነኛውንም ዓይነት ሐዋርያዊ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ሮም ሲመለሱ እንደ ተለመደው እና ዘወትር ማነኛውንም ሐዋርያዊ ጉብኝት አጠናቀው በሚመለሱበት ወቅት በአውሮፕላን ውስጥ ሆነው ጋዜጠኞች ስላከናወኑት ሐዋርያዊ ጉብኝት እና ተያያዥነት ያላቸውን ጥያቄዎች እንደ ሚያቀርቡላቸው እና ቅዱስነታቸው ምላሽ እንደ ሚሰጡ የሚታወቅ ሲሆን በዚህም መሰረት ቅዱስነታቸው ከባለፈው ግንቦት 23-25/2011 ዓ.ም በሮማኒያ እይደረጉ የነበረውን 30ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በግንቦት 25/2011 ዓ.ም ምሽት ላይ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ ሮም በሚመለሱበት ወቅት ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች መልስ መስጠታቸው የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው “የአውሮፓ አህጉር ሕብረቱን ጠብቆ ይጓዝ ዘንድ ልንጸልይ ይገባል” ማለታቸው ተገልጹዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ቅዱስነታቸው በወቅቱ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው በርካታ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን ችግሮች በሚከሰቱበት ወቅት ችግሮቹን ለመፍታት በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊደረግ ስለሚገባው ትብብር፣ በካቶሊክ እና በኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ስላለው ግንኙነት እና ወቅታዊውን የአውሮፓ ሁኔታ በተመለከተ ከጋዜጠኞ ለቀረበላቸው በርካታ ጥያቄ ቅዱስነታቸው መልስ መስጠታቸው ተገልጹዋል።

ወቅታዊ የአውርፓን ሁኔታ በተመለከተ

በአሁኑ ወቅት በአውሮፓ አህጉር ስለሚታየው ፖሌቲካዊ ውጥረት በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ቅዱስነታቸው በሰጡት ምላሽ እንደ ገለጹት “አውሮፓ ለወደፊት የሚገጥሙትን ተግዳሮቶች በማየት ችግሮቹን ካሁኑ ለመፍታት እንቅስቃሴ  ካልተጀመረ የአውሮፓ አህጉር የተዳከመ ይሆናል” በማለት ምላሽ የሰጡት ቅዱስነታቸው በአሁኑ ጊዜ የሚገኙ የአውሮፓ ፖለቲከኞች ቀደም ሲል የአውሮፓን አህጉር የመሰረቱ አባቶቻቸው የነበራቸውን ዓይነት በቅንነት የተሞላ ወኔ መልሰው ሊጎናጸፉ ይገባል” ብለዋል። የአውሮፓ አህጉር ራሱን መሆን ይኖርበታል፣ በአሁኑ ወቅት ያጣውን የራሱን መለያ ባህሪይ መልሶ መጎናጸፍ ይኖርበታል፣ የነበረውን ሕብረት በድጋሚ ማጠናከር ይኖርበታል፣ መከፋፈልን ለማስወገድ ይችላ ዘንድ በድንበር አከባቢ የሚታዩትን ሁኔታዎች መፍታት ይኖርበታል በማለት ምልሽ መስጠታቸው ተገልጹዋል።

በአውሮፓ ውስጥ የሚገኙ እያንዳንዱ አገር የራሱ የሆን ትክክለኛ ማንነት እንዳላቸው እሙን መሆኑን በአጽኖት የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህንን ትክክለኛ ማንነት ጠብቆ መጓዝ ተገቢ የሆነ ነገር መሆኑን ገልጸው ሁሉንም ባሕሎች እና ትክክለኛ ማንነት ከግንዛቤ ባስገባ መልኩ ሕበረት መፍጠር እንደ ሚቻል ገልጸዋል።

ችግሮች በሚከሰቱበት ሰዓት ሊደረግ የሚገባውን ዓለም አቅፍ የሆነ ትብብር በተመለከተ እና በተጨማሪም “አንዳንድ ቤተሰቦች ልጆቻቸው ከአገር ውጪ ሂደው እንዲሰሩ እንደሚልኩዋቸው እና ይህ ተግባር ተገቢ ነው ወይ? ተብሎ ከአንድ የሮማኒያ ጋዜጠኛ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምልሽ የሰጡት ቅዱስነታቸው “ቤተሰቦኣቻቸውን ትተው ወደ ሌላ አገር በመሄድ በተለያዩ አገራት ሥራ ላይ መሰማራት እና ቤተሰብ ማገዝ በራሱ የፍቅር ሥራ መገለጫ ባሕሪይ መሆኑን የገለጹት ቅዱስነታቸው በእዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ የሚለያዩ ቤተሰቦች ሁኔታ ሐሳዛኝ ቢሆንም ቅሉ የእዚህ ዓይነቱ ችግር በሮማኒያ ብቻ እየተከሰተ የሚገኝ ችግር ሳይሆን ዓለማቀፋዊ ይዘት ያለው ችግር እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸው ለዚህ ዓይነቱ ዓለማቀፋዊ ችግር ዓለማቀፋዊ ምላሽ ያሻዋል ብለዋልል።

በሮማኒያ የሚትገኘው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ያላቸውን ግንኙነት በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ቅዱስነታቸው የሮማኒያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ለሆኑት ለብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ዳኒኤል ምስጋና ይድረሳቸው እና በጣም መልካም የሚባል ግንኙነት እንዳለ ገልጸው እርሳቸው ከእዚህ ቀደም በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለው ሕብረት እንዲጠናከር የበኩላቸውን አስተዋጾ ማደረጋቸውን ገልጸው በተለያዩ የክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት ሰማዕታት ደም የተሳሰረ ሕበረት አለን በማለት ደጋግመው እንደ ሚናገሩ ቅዱስነታቸው አስታውሰው በዚህ ሥር መሰረታችን ላይ በመቆም በጋራ የክርስትና ሐይማኖት ግዴታችንን በመመስከር ድሆችን እና በሕመም የሚሰቃዩ ሰዎችን ማገዝ ይኖርብናል ብለዋል።

02 June 2019, 16:47