ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሰኔ 14/2011 ዓ.ም ናፖሊን እንደ ሚጎበኙ ተገለጸ። ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሰኔ 14/2011 ዓ.ም ናፖሊን እንደ ሚጎበኙ ተገለጸ። 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሰኔ 14/2011 ዓ.ም ናፖሊን እንደ ሚጎበኙ ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በነገው እለት ማለትም በሰኔ 14/2011 ዓ.ም የናፖሊን ከተማ እንደ ሚጎበኙ የተገለጸ ሲሆን በእዚያው በናፖሊ በላቲን ቋንቋ Veritatis Gaudium (በእውነት የሚገኝ ደስታ) በሚል አርእስት እርሳቸው እ.አ.አ በጥር 29/2018 ዓ.ም ያፋ ባደረጉት ሐዋሪያዊ ሕግ-ጋት ላይ በሚካሄደው ኮንፈረንስ ላይ ቅዱስነታቸው እንደ ሚሳተፉም ተገልጹዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በናፖሊ በሚያደርጉት የአንድ ቀን ሐዋሪያዊ ጉብኝት ላይ ቅዱስነታቸው ቀደም ሲል በገለጽነው መሰረት በእዚያው በሚካሄደው ኮንፈረንስ ላይ ተገኝተው በላቲን ቋንቋ “Veritatis Gaudium (በእውነት የሚገኝ ደስታ) ነገረ መለኮት በአውሮፓ አውድ ሲታይ” በሚል አርእስት ላይ ተመርኩዘው ንግግር እንደ ሚያደርጉ ተገልጹዋል።

ይህ በናፖሊ የሚካሄደው እና ቅዱስነታቸው የሚሳተፉበት ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ በአሁኑ ወቅት በተለይም በአውሮፓ አህጉር በከፍተኛ ሁኔታ እየታየ የሚገኘው የስደተኞ ፍልሰት ላይ፣ በባህሎች መካከል ያለው ልዩነት ላይ እና በተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት መካከል የሚደረጉ ውይይቶችን በተመለከተ ማብራሪያ የሚሰጡ የተላያዩ ምሁራን ተግብዝወ ንግግር እንደ ሚያደርጉ የተገለጸ ሲሆን በእዚህ ውይይት ላይ ቅዱስነታቸው እንደ ሚሳተፉ ተገልጹዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እ.አ.አ በጥር 29/2018 ዓ.ም በላቲን ቋንቋ “Veritatis Gaudium (በእውነት የሚገኝ ደስታ) ይፋ ያደረጉት ሐዋርያዊ ሕግ-ጋት በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማሕበራዊ ተቋማት ውስጥ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን በተለይም ደግሞ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሥር በሚተዳደሩ ትምህርት ቤቶች እና መሰል ተቋማት ውስጥ ሥራ ላይ እየዋለ የሚገኝ ሕግ እንደ ሆነ ይታወቃል። ሕግ-ጋቱ የእግዚአብሔርን ታላቅነት እና እውነትን በተመለከተ ሰፊ የሆነ መልእክት የያዘ ሲሆን በተጨማሪም በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተቋማት ውስጥ በተለይም ደግሞ በትምህርት ቤቶች ውስጥ ለስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ሊደረግ ሰለሚገባው እንክብካቤ የሚያመለክቱ ሕጎች ተጠቅሰውበታል።

20 June 2019, 12:15