ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከዓለምአቀፍ ካቶሊክ የሕክምና ባለሙያዎች ማሕበር ተወካዮች ጋር በተገናኙበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከዓለምአቀፍ ካቶሊክ የሕክምና ባለሙያዎች ማሕበር ተወካዮች ጋር በተገናኙበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “የሕክምና ባለሙያዎች ለበሽተኛው ቅርብ መሆን ይገባቸዋል” አሉ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከዓለምአቀፍ ካቶሊክ የሕክምና ባለሙያዎች ማሕበር ተወካዮች ጋር በሰኔ 15/2011 ዓ.ም በቫቲካን ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባደረጉት ንግግር እንደ ገለጹት የሕክምና ባለሙያዎች አገልግሎታቸውን ለበሽተኛው ቅርብ በመሆን ሊወጡ እንደ ሚገባ የገለጹ ሲሆን ኢየሱስ በሐዋርያዊ አገልግሎቱ እንደ ፈጸመው የሕክምና ባለሙያዎችም በሽተኛውን በጥንቃቄ እና በትዕግስት በማዳመጥ ማጽናናት እንደ ሚገባቸው ቅዱስነታቸው መናገራቸውን ከደረሰን ዘገባ ለመረዳ ትችሉዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

“በርኅራኄ መንፈስ የተሞላ ቅርበት በማሳየት ኢየሱስ በችግር ላይ ለነበሩ ሰዎች ዘላለማዊ የሆነውን የእግዚኣብሔር ፍቅር ገልጾላቸው ” እንደ ነበረ ለዓለም አቀፍ ካቶሊክ የሕክምና ባለሙያዎች ማሕበር ተወካዮች የተናገሩት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ እዚህ ምድር ላይ በነበረበት ወቅት ለበሽተኞች በርኅራኄ መንፈስ የተሞላ እገዛ አድርጎ እንደ ነበረ ገልጸው በእዚህም የተነሳ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች ኢየሱስን ሀኪማችን ብለው ይጠሩት እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

ኢየሱስ በማሕበረሰቡ እንደ ኋጥያተኛ ተቆጥረው ለተገለሉ ለበሽተኞች እና ለአካል ጉዳተኞች ቅርብ እንደ ነበረ በንግግራቸው ያስታወሱት ቅዱስነታቸው በእዚህም የተነሳ ለበሽተኞች እገዛ ማደረግ የክርስቲያን እምነት መገለጫ እና በተጨማሪም የቤተክርስቲያን ዋነኛው ተልዕኮ ነው ብለዋል።

ለበሽተኞች ቅርብ መሆን ያስፈልጋል

ኢየሱስ ለታመሙ ሰዎች ያደርገው የነበረው እንክብካቤ መስጫ "መንገድ" በማንኛውም ጊዜ ውስጥ ለሚገኙ ሀኪሞች እና ነርሶች ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን በመግለጽ ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህ መንገድ ደግሞ ምንም እንኳን ማህበራዊ የሆኑ ደንቦች ቢኖሩም "ለግለሰቦች ቅርብ መሆንን" ያካትታል ብለዋል። ኢየሱስ ማነኛውንም ዓይነት ፈውስ ከመፈጸሙ በፊት “ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋልህ?” በማለት ከበሽተኛው ጋር በቅድሚያ ውይይት እንደ ሚያደርግ የጠቀሱት ቅዱስነታቸው “ይህም ለበሽተኛው እፎይታን፣ መጽናናትን እና ፈውስን ያስገኛል” ብለው አንዱ ለሌላው እውነተኛ ፍቅር ሲሰጥ የፍቅር ተቀባዩን አድማስ ያሰፋል፣ ምክንያቱም የሰው ልጆች በመንፈስ፣ በነፍስ እና በአካል የተዋቀረ ሕብረት ያላቸው በመሆናቸው የተነሳ ነው ብለዋል።

ለሰዎች ሁለንተናዊ የሆነ እንክብካቤ ማደረግ

ኢየሱስ ያከናውነው የነበረው ፈውስ ሁለንተናዊ የሆነ ፈውስ እንደ ሆነ በመግለጽ ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እርሱ በታላቅ ርኅራኄ እና ቅርበት የፈወሳቸውን ሰዎች ተነስተው እንዲሄዱ፣ ተመልሰው ከማኅበርሰቡ ጋር እንዲቀላቀሉ ማደረጉን የገለጹት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ከፈወሳቸው ሰዎች ውስጥ ብዙዎቹ የእርሱ ተከታይ መሆናቸውን ጨምረው ገልጸዋል። 

ዓለምአቀፍ ካቶሊክ የሕክምና ባለሙያዎች ማሕበር አባላት “በተገቢው ሁኔታ እና ለእያንዳንዱ ሰው በጥንቃቄ መንፈስ እና የሰውን ሰብዓዊ መብት ባከበረ መልኩ በሽተኞች አካላዊ እና አእምሮአዊ ፈውስ ያገኙ ዘንድ የተቻላቸውን እንክብካቤ እንዲሰጡ ተጠርተዋል” በማለት የተናገሩት ቅዱስነታቸው በተጨማሪም በጥሞና በማዳመጥ፣ በማበረታታት እና በማጽናናት፣ ተስፋን በመስጠት ለበሽተኞች የበለጠ ሰብአዊ እንክብካቤ እንዲያደርጉ ቅዱስነታቸው ማሳሰባቸው ተገልጹዋል።

ለሕይወት አክብሮት መስጠት

ባለፉት 100 አመታት ውስጥ በሕክምናው ዘርፍ ከፍተኛ የሆነ ምርምር መካሄዱን እና በህክምናው ዘርፍ እጅግ ከፍተኛ የሆኑ መሻሻሎች እየታዩ መምጣታቸውን የገለጹት ቅዱስነታቸው "ይህ ማለት ደግሞ የሰዎች ስቃይን ማስታገስና ማቃለል ማለት እንደ ሆነ አክለው ተናግረዋል። ይህ ማለት ሰዎች ስለራሳቸው ጤና ይበልጥ እንዲጨነቁ ያስተምራል ብለዋል። በሕክምና ሂደት ውስጥ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ድረስ ከእግዚኣብሔር በስጦታ መልክ ለተሰጠን ለሕይወታችን ጥንቃቄ ማደረግ እንደ ሚገባ የገለጹት ቅዱስነታቸው “እኛ የሕይወታችን ጌታ አይደለንም” ሕይወታችን ለእኛ በአደራ የተሰጠች ናት፣ የሕክምና ባለሙያዎች ደግሞ ሕይወታችንን የመንከባከብ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል ብለዋል።

በመንፈስ መታደስ

በመጨረሻም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዓለምአቀፍ ካቶሊክ የሕክምና ባለሙያዎች ማሕበር አባላት እንደ ገለጹት በሽተኞችን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማደረግ ይቻል ዘንድ ሙያዊ ክህሎቶቻቸውን፣ የቡድን ሥራዎችን እና የሥነ-ምግባር አቋማቸውን ማስተባበር እና አቀናጀተው መቀጠል እንደ ሚገባቸው ያሳሰቡ ሲሆን በእዚህ ረገድ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን ለማደስ ይረዳቸው ዘንድ በእየለቱ መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ እና ቅዱሳን የቤተክርስቲያን ምስጢራትን መካፈል ይኖርባቸዋል ብለዋል። "በከፍተኛ ሁኔታ ጥንቃቄ የሚያሰፍልጋቸውን ውስብስብ የሆኑ የሕክምና ሁኔታዎችን በተገቢው እና በትክክለኛው መንገድ መጋፈጥ እንድትችሉ፣ ትክክለኛ የሆኑ ነገሮችን በትክክለኛው ጊዜ እና መንገድ ማከናውን ትችሉ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ የማስተዋል ስጦታ ይሰጣችኋል” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

 

24 June 2019, 17:57