ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሮማኒያ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሮማኒያ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሮማኒያ ሰለተደረገልኝ መልካም አቀባበል አመሰግናለሁ አሉ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከግንቦት 23-25/2011 ዓ.ም ድረስ 30ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በሮማኒያ እያደርጉ እንደ ሚገኙ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ቅዱሰንታቸው በግንቦት 25/2011 ዓ.ም በሮማኒያ በነበራቸው  የሐዋሪያዊ ጉዞ ማብቂያ ላይ በሮማኒያ ዋና ከተማ በቡካሬስት መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በመስዋዕተ ቅዳሴው ላይ ለእምነታቸው ሲሉ መስዋዕትነትን የከፈሉ ሰባት የግሪክ-ካቶሊክ ጳጳሳትን የሰማዕትነት ማዕረግ እንደ ሰጧዋቸው የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው ባደረጉት ስብከት እንደ ገለጹት “በተለያየ ዓይነት ርዕዮተ ዓለም ምክንያት የሚቃጡትን በደሎች ፍቅር ያሸንፋል” ማለታቸው ተገልጹዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ቅዱስነታቸው መስዋዕተ ቅዳሴ ካጠንቀቁ በኋላ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ክብር በመስጠት ከሚደገሙ ጸሎቶች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰውና በተለይም ክርስቶስ ከሙታን ከተነሳበት የትንሳኤ በዓል ጀምሮ እስከ በዓለ ሃምሳ ድረስ የሚደገመውን “የሰማይ ንግስት ሆይ ደስ ይበልሽ”  የሚለውን ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኋላ እንደ ተለመደው ቅዱስነታቸው ለምዕመኑ ባስተላለፉት መልእክት በሮማኒያ ከግንቦት 23-25/2011 ዓ.ም 30ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ስለተደረገላቸው እንክብካቤ መላውን የአገሪቷን ሕዝብ ያመሰገኑ ሲሆን በዚህ ሐዋርያዊ ጉብኝቴ ወቅት በተለያዩ አጋጣሚዎች የገኘኋቸውን ግለሰቦች እና ተቋማት አመሰግናለሁ ብለዋል። ለአገሪቷ ርዕሰ ብሔር እና ባለስልጣናት  የተከበረ ሰላምታዬን እያቀረብኩኝ ስላደረጉልኝ ሞቅ ያለ እንክብካቤ ከልብ አመሰግናለሁ ብለዋል። በሮማኒያ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ የሆኑት ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ዳኒኤልን እና በአገሪቷ የሚገኘውን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ ቋሚ አባልትን ስላደረጉልኝ አቀባበል ከልብ አመስግናለሁ ያሉት ቅዱስነታቸው ጌታ የእነርሱን ጥንታዊ ቤተክርስቲያን እና ተልዕኮዋቸውን ይባርክላቸው ዘንድ ጸሎቴ ነው ብለዋል።

በሮማኒያ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳስ የሆኑትን ካርዲናል ሉሻን ቡርሳን ላደረጉልኝ አቀባበል ከልብ አመሰግናለሁ ያሉት ቅዱስነታቸው በተጨማሪም በአገሪቷ የሚገኙትን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካህናት፣ ደናግላ፣ ምዕመናን ሁሉ ላመሰግን እወዳለሁ ያሉት ቅዱስነታቸው በማርያም ስም በሚጠሩ የተለያዩ ቤተመቅደሶች ውስጥ ተገኝቼ ከሕዝቡ ጋር እንድጸልይ እድል በማግኜቴ እግዚኣብሔርን አመሰግናለሁ ብለዋል።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በመላው የሮማኒያ ሕዝብ ላይ እናታዊ ጥበቃዋን ታደርግ ዘንድ ምኞቴ እና ጸሎቴ ነው፣ የሮማኒያ ሕዝቦች ሁሉም በእመቤታችን ቅድስት ድንግላ ማርያም አማላጅነት የመተማመን ልምድ ስላላቸው አሁንም ቢሆን ይህንን የሮማኒያ ሕዝብ በማርያም ጥበቃ ስር ይሆኑ ጸንድ አመላጅነቷን እማጸናለሁ ያሉት ቅዱስነታቸው በተጨማሪም ዘላቂ የሆነ ሰላም በመገንባት በወንድማማችነት ፍቅር የተገነባ አገር ትመሰረቱ ዘንድ ጸሎቴ እና ምኞቴ ነው ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

02 June 2019, 16:52