ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በጣሊያን ግዛት ሥር ማሪኬ በሚባል ክልል ውስጥ በምትገኘው ካሜሪኖ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በጣሊያን ግዛት ሥር ማሪኬ በሚባል ክልል ውስጥ በምትገኘው ካሜሪኖ  

ር.ሊ.ጳ “በመካከለኛው ምስራቅ አገራት ያለው ውጥረት ይረግብ ዘንድ ጸሎት ማድረግ ያስፈልጋል!”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በትላንትናው እለት ማለትም በሰኔ 09/2011 ዓ.ም በጣሊያን ግዛት ሥር ማሪኬ በሚባል ክልል ውስጥ በምትገኘው ካሜሪኖ በመባል በምትታወቀው እና የዛሬ ሦስት አመት ገደማ ባጋጠማት የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ 300 ያህል ሰዎችን ነፍሳቸውን ያጡባት ተራራማ ስፍራ ተገኝተው መስዋዕተ ቅዳሴ ካሳረጉ በኋላ ቅዱስነታቸው በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ክብር በመስጠት ከሚደገሙ ጸሎቶች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰውን “የእግዚኣብሔር መልአክ ማርያምን አበሰራት” የሚለውን ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከመድገማቸው በፊት ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት እንደ ገለጹት በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም ይረጋገጥ ዘንድ ጸሎት ማደረግ እንደ ሚገብ የገለጹ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በመካከለኛው ምስራቅ የተፈጠረው ውጥረት ረግቦ ሰላም በቀጠናው ይፈጠር ዘንድ ባለድርሻ አካላት ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።

በአሁኑ ወቅት በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ አገራት መካከል ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ከኢራን ጋር ያላቸው ሽኩቻ እየጨመረ መምጣቱ የሚታወቅ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባስተላለፉት መልእክት ውጥረቱ ዲፖሎማሲያዊ በሆነ መልኩ በሚደረጉ ውይይቶች ይፈታ ዘንድ ጥሪ ማቅረባቸው ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ውስብስብ የሆነው የመካከለኛው ምስርቅ አገራት ችግር ይፈታ ዘንድ ዓለማቀፉ ማሕበረሰብ የተቻለውን በማደረግ የውይይት መንፈስ ይዳብር ዘንድ ጥረት ማደረግ ተገቢ መሆኑን ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

በመጪው ረቡዕ ሰኔ 13/2011 ዓ.ም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በዓለማቀፍ ደረጃ የስደተኞች ቀን እንደ ሚያከብር በመልእክታቸው ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ጦርነትን፣ መሰረታዊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እና በሀይማኖታዊ ጉዳዮች የተነሳ አገር ንብረቶቻቸውን ጥለው የሚሸሹትን ሰዎች መንከባከብ እና አጋርነት ማሳየት እንደ ሚገባ የገለጹ ሲሆን ቤተክርስቲያን እና የሲቪክ ማሕበረሰቡ ሳይቀር ስደተኞችን ማገዝ እንደ ሚገባ ከገለጹ በኋላ እንደ ተለመደው ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተው እና እባካችሁን ለእኔ መጸለይ አትዘንጉ በማለት ከተማጸኑ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

16 June 2019, 12:41