ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ለእግዚኣብሔር ቅርብ የሆነ ሰው መከራን መሻገር ይችላል”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በትላንትናው እለት ማለትም በሰኔ 09/2011 ዓ.ም በጣሊያን ግዛት ሥር  ማሪኬ በሚባል ክልል ውስጥ በምትገኘው ካሜሪኖ በመባል በምትታወቀው እና የዛሬ ሦስት አመት ገደማ ባጋጠማት የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ 300 ያህል ሰዎችን ነፍሳቸውን ያጡባት ተራራማ ስፍራ ተገኝተው መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው  በወቅቱ ባሳረጉት መሰዋዕተ ቅዳሴ ላይ በርካታ ሕጻንት ለመጀርሚያ ጊዜ ምስጢረ ቅዱስ ቁርባን መቀበላቸው የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያደርጉት ስብከት በመዝሙረ ዳዊት ምዕረፍ 8 ላይ ትኩረቱን ያደርገ እንደ ነበረ ተያዞ ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “ለእግዚኣብሔር ቅርብ የሆነ ሰው መከራን መሻገር ይችላል” ማለታቸው ተገልጹዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን ስብከት ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል እንድትከታታሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

“በሐሳብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?” (መዝ 8፡5) የሚለውን ጸሎት ቀደም ሲሊ ጸልየናል። ስለእናንተ ሳስብ እነዚህ ቃላት ወደ አእምሮዬ ይመጣሉ። ባጋጠማችሁ የመከራ እና የስቃይ ሁኔታ፣ በተደረመሱባችሁ ቤቶች እና ህንጻዎች ምክንያት በፈረሰባችሁ የከተማችሁ ሁኔታ ስታስቡ፦ የሰው ልጅ ምንድነው? ብላችሁ ጥያቄ ታነሱ ይሆናል። የቆመ የሚመስለው ነገር ወዲያሁኑ ሲፈራርስ ምን ዓይነት ትርጉም ይሰጠናል? ተስፋ የደረግንበት ነገር ወደ አቧራነት ሲቀየር ምን ዓይነት ትርጉም ይሰጠናል? ታዲያ ስው ምንድነው? ስለእርሱ “በሐሳብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?” ለሚለው ጥያቄ መልስ መስጠት ያስፈልጋል። እኛ እንዲሁ ባለንበት ሁኔታ ከነድክመታችን ሳይቀር እግዚኣብሔር ሁሌም ስለእኛ ያስባል። ከውጪ እና ከውስጥ በተፈጠሩት ነገሮች ማክንያት ባጋጠመን እርግጠኛ ያለመሆን ስሜት ውስጥ እግዚኣብሔር አንድ ማረጋገጫ ይሰጠናል፣ እግዚኣብሔር ስለእኛ ያስባል። ያስባል ማለት ደግሞ ወደ እኛ ወደ ልባችን ውስጥ ይገባል፣ በልባችን ውስጥ ይሆናል ማለት ነው። እኛ በእዚህ ምድር ላይ ሆነን በምናከናውናቸው በጣም ብዙ በሆኑ ነገሮች ምክንያት እርሱን ብንረሳውም እግዚኣብሔር ግን እኛን በፍጹም አይረሳንም። በእርሱ ፊት ማንም ሰው የተናቀ አይደለም፣ እያንዳንዳችን በእርሱ እይታ ውስጥ ዘላለማቂ የሆነ ዋጋ አለን፣ እኛ ከሰማይ በታች የምንገኝ ትንንሽ የሆንን ፍጥረታት እና መሬት በሚንቀጠቀጥበት ወቅት የመቋቋም አቅም የሌለን ብንሆንም እንኳን በእግዚኣብሔር ፊት ከሁሉም በላይ ውድ የሆንን ፍጥረታት ነን።

ማስታወስ የሚለው ቃል በሕይወት ውስጥ በጣም ቁልፍ የሆነ ቃል ነው። በእያለቱ እግዚኣብሔርን እኛ እንዳንረሳው እና የእርሱ ተወዳጅ ልጆች መሆናችንን እንድናስታውስ፣ መተክያ የሌለን ልጆቹ መሆናችንን እንድንገነዘብ በሕይወት ሂደት ውስጥ የሚያጋጥሙንን ነገሮች ሁሉ ለብቻችን መጋፈጥ እንደማንችል እንድንገነዘብ ይረዳን ዘንድ በእየለቱ የእርሱን ጸጋ መማጸን ያስፈልጋል። ወደ ሐዘን እና መከራ ውስጥ ገብተን ከእዚያ ባሻገር በመሄድ መውጫ የሌለው ሐዘን ውስጥ እንዳንገባ ሁልጊዜም ቢሆን ምን ያሕል ዋጋ እንዳለን ልናስታውስ የገባል። መጥፎ የሆኑ ትውስታዎቻችን ሳንፈልጋቸው እንኳን ወደ እኛ ሊመጡ ይችሉ ይሆናል፣ ዋጋም ያስከፍሉናል፣ ክፉ ነገሮችን ብቻ እንድናስታውስ አደርገው ያልፋሉ። ከእንደዚህ ዓይነት መጥፎ ከሆኑ ትውስታዎች እንዴት ነው መላቀቅ የምንችለው? እግዚኣብሔር ከእስራኤላዊያን ልብ ውስጥ ግብጽን ከማውጣት ይልቅ እስራኤላዊያንን ከግብፅ ነፃ ማውጣት ይቀለው ነበረ የሚል አባባል አለ።

ካለፈው ጊዜ አሉታዊ ትውስታ ልባችንን ለማላቀቅ እና ሽባ ከሚያደርጉን አሉታዊ ከሆኑ ትውስታዎቻችን እስር ቤት ነጻ ለመውጣት እንችል ዘንድ ከእዚህ ሸክም ነጻ ሊያደርገን የሚችል የአንድ አካል እርዳታ ያስፈልገናል። በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ ኢየሱስ “ አሁን ግን ሁሉንም ነገር ልትሸከሙት አትችሉም” (ዮሐ 16፡12) በማለት ይናገራል። በድክመታችን እርሱ ምን ሊያደርገን ይችላል? እኛ ለችግሮቻችን ፈጣን እና ውስብስብ የሆኑ መፍትሄዎችን ለመስጠት በምንጣደፍበት መልኩ እርሱ ሸክማችንን ወዲያሁኑ አያስወግድልንም፣ ነገር ግን ጌታ መንፈስ ቅዱሱን ይሰጠናል። መንፈስ ቅዱስ እጅግ በጣም ያስፈልገናል፣ ምክንያቱም አጽናኝ እና በሕያወታችን ሂደት ውስጥ በሚያጋጥሙን የሕይወት ጫናዎች ወቅት ብቻችንን አይተወንም። ባሪያ ከሚያደርጉን መጥፎ ማሕደረ ትውስታችን ነጻ የሚያረገን፣ ያለፈውን ጊዜ ትውስታ በመልካም በመቀየር ወደ ደህንነት የሚመራን እርሱ ብቻ ነው። በኢየሱስ ላይ የተፈጸሙ ነገሮች፣ ቁስል፣ የደረሰበት መጥፎ መከራ ሁሉ በእኛም ላይ ይደርሳል፣ ነገር ግን እነዚህ ሁሉ ነገሮች በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ወደ ምሕረት ጎዳና እንድንራመድ የሚያደርጉን አጋጣሚዎች ሲሆኑ የእግዚኣብሔር ድንቅ የሆነ ፍቅር መገለጫ በመሆን፣ ከውደቀት ወደ ትንሳኤ እንድናመራ የሚያደርገን ፍቅር ይሰጠናል። ይህንን የሚያደርገው መንፈስ ቅዱስ ሲሆን ይህንን የሚፈጽመው ደግሞ በመከራዎቻችን ውስጥ ጣልቃ እንዲገባ በምንፈቅድበት እና በምንጋብዘው ወቅት ነው። መጥፎ የሆኑትን ትውስታዎቻችንን በተስፋ የቀባዋል፣ ምክንያቱም መንፍስ ቅዱስ ተስፋችን እንዲለመልም የማድረግ ብቃት አለውና።

ተስፋ! ተስፋ ስንል ምን ማለታችን ነው? እንዲሁ አላፊ የሆነ ተስፋን ግን አያመለክትም። ምድራዊ የሆኑ ተስፋዎቻችን ሁልጊዜም ቢሆኑ አላፊ ናቸው፣ ምክንያቱም እነደነዚህ ያሉ ምድራዊ ተስፋዎቻችን የተዋቀሩት ምድራዊ በሆኑ ነገሮች ስለሆነ፣ አስቀድመው ወይም ከቆይታዎች በኋላ በነው ይጠፋሉ። መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠን ተስፋ ግን ዘላቂ የሆነ ተስፋ ነው። በፍጹም መቋጫ የለውም፣ ምክንያቱም መሰረቱን ያደርገው በእግዚኣብሔር ላይ ባለን እምነት በመሆኑ። መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠን ተስፋ እንዲሁ ብልጭልጭ የሆነ ተስፋ አይደለም። በመወደዳችን የተነሳ ውድ መሆናችንን በማስታወስ ጥልቅ ከሆነ ልባችን ውስጥ የሚወለድ ተስፋ ነው። ብቻችንን አለመሆናችንን እንድንረዳ የሚያደርግ ተስፋ ነው። በልባችን ውስጥ ሰላም እና ደስታ እንዲኖር የሚያደርግ ውጫዊ በሆኑ ነገሮች የተነሳ የሚፈጠሩት ጫናዎችን መቋቋም እንችል ዘንድ የሚያደርገን ተስፋ ነው። ማነኛውም ውጫዊ የሆነ ጫና ነቅሎ ሊወስደው የማይችል የተስፋ ዓይነት ነው። ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ እንደ ሚለው “የማያስፍር ተስፋ” (ሮሜ 5፡5) ነው። መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠን ተስፋ የሚያሳፍር ተስፋ አይደለም፣ እያንዳንዱን መከራ እና ስቃይ መሻገር የሚያስችለን ተስፋ ነው። መከራ እና ስቃይ ውስጥ መግባት ማለት ምን ማለት እንደሆነ እናንተ በሚገባ ታውቃላችሁ- በመከራ እና በስቃይ ውስጥ በምንገባበት ወቅቶች ሁሉ በሐዘናችን እና  በፍርሃታችን ዙሪያ "ጎጆ" መግንባት እንጀምራለን። በሌላ በኩል ግን መንፈስ ቅዱስ እኛ በዙሪያችን ከምንገነባው ጎጆዎች ነፃ ያወጣናል፣ እኛ በተስፋ ተሞልተን እንድንኖር ያደርገናል፣በተወለድንበት ወቅት የተሰጠንን ድንቅ ዕጣ ፈንታ ምን እንደሆነ እንድንገነዘብ ያደርገናል። መንፈስ ቅዱስ የሕይወት ትስፋችንን ይመግባል። በሕይወታችን ውስጥ ይገባ ዘንድ እንጋብዘው።  ከእኛ ጋር እንዲሆን እና ቅርባችን ይሆን ዘንድ እንጋብዘው። አጽናኝ የሆንክ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ና! ብርሃንን አብራልን፣ መጥፎ ገጠመኞቻችንን  እንድንረዳ አርዳን፣ የማያሳፍር ተስፋ እንድንጎናጸፍ እርዳን። መንፈስ ቅዱስ ሆይ ና!

ቅርበት የሚለው ቃል በዛሬው ስብከቴ ከእናተ ጋር ልጋራው የምፈልገው ሦስተኛው እና የመጨረሻው ቃል ነው። ዛሬ የቅድስት ስላሴን በዓል እያከብርን እንገኛለን። የቅድስት ስላሴ ምስጢር የተወሳሰበ የነገረ መለኮት አስተምህሮ ሳይሆን የእግዚኣብሔርን ቅርበት የሚያሳይ ምስጢር ነው። ቅድስት ስላሴ የሚያስረዳን እኛ እግዚኣብሔር ላይ በሰማይ ብቻውን ቁጭ ብሎ የሚገኝ አምላክ እንዳልሆነ ያሳየናል፣ እርሱ አንደኛ ልጁን ለእኛ የሰጠን አባታችን ሲሆን ልጁን ልኮ እንደኛ ሰው እንዲሆን ያደረገ፣ ለእኛ ያለውን ቅርበት ያሳየ፣ የሕይወት መሰናክሎችን በሚገባ መሻገር እንችል ዘንድ ለእኛ ቅርብ በመሆን አጽናኝ የሆነውን መንፈስ ቅዱስ ለእኛ የሰጠን አባት ነው። ከእግዚኣብሔር ጋር ከሆንን ደግሞ የሕይወት ሽክማችን በእኛ ትክሻ ላይ ብቻ አይጫንም፣ ችግሮቻችንን በሚገባ መሸከም እንችል ዘንድ ኃይሉን ይሰጠናል፣ ያበረታታናል ሸክማችንን ይጋራል። አዲስ ከመገንባት ይልቅ ያለውን መጠገን ብዙ ጉልበት ይጠይቃል፣ ከመጽናናት ይልቅ በጉዳዩ መስማማት ይቀለናል። ይህንን እንድንወጣ የሚረዳንን ኃይል የሚሰጠን ደግሞ እግዚኣብሔር ነው። ስለዚህ በእግዚኣብሔር የሚተማመን እና ለእርሱ ቅርብ የሆነ ሰው መከራን ይሻገራል፣ ወደ ፊት ይጓዛል፣ ጉዞውን በአዲስ መልክ ይጀምራል፣ ያሻሽላል፣ እንደገና በአዲስ መልክ ይገነባል። መከራ ሊያጋጥመው ቢችልም እንኳን መከራን የመሻገር ብቃት፣ ነገሮችን የማሻሻል ብቃት፣ በድጋሚ የመገንባት ብቃት ይኖረዋል።

 ስለእርሱ ታስብ ዘንድ ሰው ምንድነው? እግዚኣብሔር ስለእኛ ያስባል፣ በስቃይ የተሞላውን ማሕደረ ትውስታችንን እግዚኣብሔር ይለውጣል፣ እግዚኣብሔር በውስጣችን ሆኖ ከውድቀታችን ሊያነሳን ይፈልጋል፣ እግዚኣብሔር ደግሞ መልካም ነገሮችን እንድናከናውን ይረዳናል፣ በልባችን ውስጥ አጽናኝ መንፈስ እንዲኖር ያደረጋል። እያንዳንዳችን ትንሽዬ ብትሆንም እንኳን መልካም ነገሮችን ማደረግ እንችላለን። እያንዳንዳችን አንዱ ሌላውን ማጽናናት ይችላል። የራሴ የግል የሆነ መስቀል የተሸከምኩኝ ቢሆንም እንኳን ሌሎችን ማጽናናት እንችላለን።

16 June 2019, 12:37