ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ሹሜለዩ ሹክ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቤተመቅደስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ሹሜለዩ ሹክ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቤተመቅደስ  

ር.ሊጳ ፍራንቸስኮስ “ራሳቸውን ለእርሱ አገልግሎት የሚያዘጋጁ ሰዎችን እግዚኣብሔር አያሳፍራቸውም”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በግንቦት 24/2011 ዓ.ም በሮማኒያ በማደረግ ላይ በሚገኙት ሁለተኛው ቀን ሐዋርያዊ ጉብኝት  በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር 05፡30 በእዚያው በሮማኒያ በሚገኘው ሹሜለዩ ሹክ በመባል በሚታወቀው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቤተመቅደስ ውስጥ ተገኝተው መስዋዕተ ቅዳሴ ማደረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው ባደረጉት ስብከት እንደ ገለጹት በዚህ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም በተሰየመው ጥናታዊ እና የቱባ ታሪክ እና የእመንት መፍለቂያ በሆነው ቤተመቅደስ ውስጥ ተገኝቼ መስዋዕተ ቅዳሴ ለማሳረግ በመብቃቴ ከፍተኛ ደስታ የተሰማኝ ሲሆን ለዚህ ያበቃኝ እግዚኣብሔር መሰግናለሁ ብለዋል።

ወደ እዚህ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም ወደ ተሰየመው ቤተመቅደስ የመጣነው እኛ ሁላችን የእርሷ ልጆች መሆናችንን በመገንዘብ እና በዚህም የተነሳ እኛ ሁላችን ወንድማማቾች እና እህተማማቾች መሆናችንን በኅብረት ለመግለጽ ነው ያሉት ቅዱስነታቸው ወደ እዚህ የመጣነው እውነት እና ሕይወት ወደ ሆነው ልጇ ወደ ኢየሱስ እንቀርብ ዘንድ እንድትረዳን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም እይታ በእኛ ላይ ይሆን ዘንድ በማመን ነው ብለዋል።

ወደ እዚህ ቤተመቅደስ የመጣነው በምክንያት ነው፣ እኛ ነጋዲያን ነን፣ በእየአመቱ የጴንጤቆስጤ በዓል ከመከበሩ በፊት ባለው የቅዳሜ እለት ምዕመኑ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያለውን ክብር እና ፍቅር ለመግለጸ ወደ እዚህ ቤተመቅደስ እንደ ሚመጣ በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእዚህ ቤተመቅደስ ውስጥ የሚገኘው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሐውልት ለሮማኒያ እና ለሀንጋሪ ሕዝቦች ባሕል እና እምነት ውስጥ ከፍተኛ ሥፍራ ያለው ቤተመቅደስ ነው ብለዋል።

ወደ እዚህ ቅዱስ የሆነ ሥፍራ ንግደት የምናደርገው ወደ እየቤታችን ስንመለስ በጸጋ ተሞልተን ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ኅብረት ፈጥረን የእርሷን የምስጋና መዝሙር እየዘመርን፣ ከልጇ ዘንድ እንድታማልደን እየተማጸንን፣ በሕይወታችን ውስጥ ተዐምር ይከሰት ዘንድ እርሷን እየተማጸንን፣ የሚለያዩንን ነገሮች አስወግደን እርስ በእርሳችን በወንድማማችነት ፍቅር እንድንዋደድ እንድትረዳን በመማጸን ጭምር መሆኑን ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

ወደ እዚህ ቅዱስ የሆነ ሥፍራ ንግደት የምናደርገው በጋራ እና በአንድነት መጓዝ እንችል ዘንድ እግዝአብሔር ይረዳን ዘንድ ጸጋውንም ይሰጠን ዘንድ፣ ያለፈውን ሕይወታችን በመቀየር አዲስ ሰዎች እንድንሆን እንዲያደርገን፣ የራሳችንን ምኞቶች፣ ተድላዎች ወደ ኋላ በመተው ጌታ ቃል የገባልልን የተስፋ ምድር ብቻ ማለም እንችል ዘንድ እርሷ በአማላጅነቷ እንድትረዳን ለመማጸን መሆኑን ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ገልጸዋል።

ወደ እዚህ ቅዱስ ወደ ሆነው ሥፍራ ንግደት ማደረግ ማለት ያለፈው ነግሮቻችን ላይ ብቻ ትኩረት አድርገን ለማሰላሰል ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በተጨማሪም መጭው ጊዜ የተቃና ይሆንል ዘንድ ለማሰላሰል እና ለመጸለይ መሆኑን የገለጹት ቅዱስነታቸው የሚመጣው እና አሁንም ቢሆን በመካከላችን የሚገኘው ጌታ በመካከላችን አንድነት፣ ወንድማማችነት መንፈስ፣ መልካም ነገሮችን እንድንመኝ፣ እውነትን እና ፍትህን እንድንፈልግ እርሷ በአማልጅነቷ ትረዳን ዘንድ ለመማጸን ነው ብለዋል።

በእዚህ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተመቅደስ ውስጥ የተገኘነው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እይታዋን በእኛ ላይ እንድታደርግ ለመማጸን እና እንዲሁም በእግዚኣብሔር የመመረጥ ምስጢር ምን መሆኑን መረዳት እንችል ዘንድ እንድትረዳን ልንማጸናት ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው መልአኩ ገብርኤል ላቀረበላት ጥያቄ “እነሆኝ እንዳልከኝ ይሁንልኝ” በማለት ምላሽ ሰጥታ እንደ ነበረ አስታውሰው የእዚህ ዓይነቱን በእግዚኣብሔር የመመረጥ ምስጢር በሚገባ መረዳት እንችል ዘንድ ፣ ኃያል የተባሉትን በማውረድ የተናቁትን ከፍ የሚያደርገው እግዚኣብሔር እኛም እርሱ እግዚኣብሔር ለሚያቀርብልን ጥያቄ “እነሆኝ” በማለት እንደ ማርያም  አዎንታዊ ምላሽ መስጠት እንችል ዘንድ እንድትረዳን በተጫማሪም በእርቅ ጉዳና ላይ መጓዝ እንችል ዘንድ እንድትረዳን አማላጅነቷን ለመማጸን ነው ብለዋል።

ራሳቸውን ለእርሱ አገልግሎት የሚያዘጋጁ ሰዎችን እግዚኣብሔር አያሳፍራቸውም በማለት ስብከታችውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እንግዲያውስ ሁላችንም በውስጣችን የሚናሰላስለው እርሾ የሆነውን ቅዱስ ወንጌል አጥብቀን በመያዝ በመዳናችን የምናገኘውን ደስታ በማጣጣም አብረን በጋራ ወደ ፊት እንድንጓዝ እንድትረዳን አማላጅነቷን ልንማጸን ይገባል ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

01 June 2019, 12:36