ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሮማኒያ በሚገኘው ይሽ የእመቤታችን ቅድስት ድንግላ ማርያም ቤተመቅደስ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሮማኒያ በሚገኘው ይሽ የእመቤታችን ቅድስት ድንግላ ማርያም ቤተመቅደስ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ከእናቶቻችሁ እና ከአያቶቻችሁ የተማራችሁትን እምነት በፍጹም እንዳትረሱ” አሉ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከግንቦት 23-25/2011 ዓ.ም ድረስ 30ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በሮማኒያ እያደርጉ እንደ ሚገኙ መዘግባችን የሚታወስ ሲሆን ቅዱሰንታቸው በግንቦት 24/2011 ዓ.ም በሮማኒያ በነባራቸው ሁለተኛው ቀን ሐዋርያዊ ጉብኝት  በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር 05፡30 በእዚያው በሮማኒያ በሚገኘው ሹሜለዩ ሹክ በመባል በሚታወቀው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቤተመቅደስ ውስጥ ተገኝተው መስዋዕተ ቅዳሴ ማደረጋቸው የተገለጸ ሲሆን ከእዚያ በመቀጠል ደግሞ በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 12፡25 ላይ በእዚያው በሮማኒያ የሚገኙውን ያሽ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ቤተመቅደስ በመጎብኘት በግል ጸሎት ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን  በግል ካደረጉት የጸሎት ቆያት በኋላ ቅዱስነታቸው በእዚያ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም በተሰየመው ቤተመቅደስ ውስጥ ከተገኙት ወጣቶች እና ቤተሰቦች ጋር ቆታ በማደረግ ቅዱስነታቸው ንግግር ማደረጋቸው ተገልጹዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

“የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አመሻችሁ” በማለት ንግግራቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው እዚህ ከእናተ ወጣቶች እና የቤተሰብ አባልት ጋር በመገናኘቴ ከፍተኛ የሆነ ደስታ ይሰማኛል ያሉት ቅዱስነታቸው የእናተን እዚህ መገኘት እና የእናንተን ፊት መመልከቴ በራሱ እቤቴ እንዳለሁኝ ሆኖ ይሰማኛል ብለዋል።

ዛሬ (ግንቦት 24/2011 ዓ.ም) በሮማኒያ የሕጻናት ቀን እየተከበረ ስለሚገኝ ለሕጻናት በሙሉ ሰላምታዬን ለማቅረብ እወዳለሁ ያሉት ቅዱስነታቸው ከሁሉም በላይ ደግሞ ለሕጻናት ልንጸልይላቸው ይገባል፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንድትጠብቃቸው ልንማጸናት ይገባል ብለዋል።  ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ወቅት ሕጻናት የእርሱ ሐዋርያዊ ተልዕኮ ማዕከል እንዲሆኑ አድርጎ እንደ ነበረ የገለጹት ቅዱስነታቸው እኛም ለሕጻናት ያለንን ፍቅር እና እነርሱን ለመንከባከብ ያለንን ቁርጠኝነት ማረጋገጥ ይገባናል ብለዋል።

እዚህ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተመቅደስ አደባባይ ላይ የብዙ ቤተሰቦች ፊት ይታየኛል በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የእግዚኣብሔር ቤተሰብ የሆኑ የብዙ ሕጻንት፣ ወጣቶች፣ ባለትዳሮች፣ ቄሳውስት እና ደናግላን፣ የአረጋዊያን ፊት ይታየኛል ያሉት ቅዱስነታቸው በተለይም ደግሞ ድንበር በመሻገር ከራሻ፣ ከፖላንድ እና ከተለያዩ ቦታዎች የተውጣጡ በርካታ ሰዎች እዚህ ይገኛሉ ብለው ምንም እንኳን የተለያየ ዓይነት ቋንቋ የምንናገር ቢሆንም ቅሉ መንፈስ ቅዱስ ግን እንዲንግባባ ያደርገናል ብለዋል።

አብሮ መጓዝ ቀላል የሆነ ነገር አይደለም በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው አብሮ ለመጓዝ የሚያስቸልንን ጸጋ ከፈጣሪ መጠየቅ ይገባናል ብለዋል። የዕድሜ ባለጸጋ የሆኑት ኤልሳቤጥ እና ጆአን የተናገሩትን አንድ ትልቅ ነጥብ ለማንሳት እፈልጋለሁ በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እነዚህ የእድሜ ባለጸጎች ፍቅር በመሠዋት እና በቁርጠኝነት መንፈስ፣ እንዲሁም በስራ እና በጸሎት  አምካይነት ጥልቅ የሆነ ትርጉም ሊያገኝ ይችላል ማለታቸውን የገለጹት ቅዱስነታቸው ፍቅር ከሁለት ጥንዶች መካከል በመወለድ ፍሬ እንደ ሚያፈራ መናገራቸውን ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

ጥንዶች የወደፊት ጊዜን በጥልቀት በመመልከት ከአብራካቸው ለተገኙ ልጆች እና የልጅ ልጆች ሕጻናት መልካም የሆነ አጋጣሚ መክፈት ይኖርባቸዋል ያሉት ቅዱስነታቸው ይህንንም ማከናወን የሚገባችሁ እናንተ ወላጆች በሕይወት ሂደት ውስጥ የተማራችሁትን ትምህርት እና ልምድ ለልጆቻችሁ በማካፈል ሊሆን ይገባል ብለዋል። ያለፋችሁበትን የሕይወት ጉዞ እና ስር መሰረታችሁን በፍጹም መርሳት የለባችሁም በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ጥሞቲዎስ በጻፈው መልእክቱ ላይ “ከእናቶቻችሁ እና ከአያቶቻችሁ የተማራችሁትን እምነት በፍጹም እንዳትረሱ” ብሎ እንደ ነበረ አውስተው ከቤተሰቦቻችሁ የተማራችሁትን መልካም የሆኑ እሴቶችን ለልጆቻችሁ ማስተማር እንዳትርሱ ማለታቸው ተገልጹዋል።

አብራችሁ በአንድነት ወደ ፊት ለመጓዝ ያስችላችሁ ዘንድ ከቤተሰቦቻችሁ የተማራችሁትን ነገር በፍጹም መዘንጋት አይኖርባችሁም በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በክርስቲያኖች መካከል የሚያስኬድ መንገድ ከሌለ በክርስቲያኖች መካከል ፍቅር እና መግባባት አለመኖሩን እንደ ሚያሳይ የገለጹት ቅዱስነታቸው ሰዎች ለሰዎች በተለይም ደግሞ ክርስቲያናኖች እርስ በእርስ ያላቸው ፍቅር ሲቀዘቅዝ ያኔ የዓለም ማብቂያ ይሆናል ብለዋል።

ሕይወት ያለ እውነተኛ ፍቅር በጣም ከባድ ይሆናል፣ መዝቀጥ ይጀምራል፣ የልባችን ምት ይቀንሳል፣ አረጋውያን ከእንግዲህ ወዲያ ህልም አያልሙም፣ በጎሬበት መካከል ያለው መንገድ ከተዘጋ ወጣቶች የወደፊቱን መተንበይ አይችሉም ምክንያቱም ያለ ፍቅር እና ያለ እግዚኣብሔር ማንም ሰው በምድር ላይ መኖር አይችልም ብለዋል።

ሮማኒያ የእግዚኣብሔር እናት መናሐሪያ ናት፣ ይህ ስሜት በጥልቀት ተሰምቶኛል በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ማርያም ልጆቿ በሕይወታቸው ደስታን እንዲያገኙ የሚያስችላቸውን ተስፋቸው ይለመልም ዘንድ ልጆቿን ታበረታታለች ብለው እርሷ ልጆቹዋን በርኅራኄ እና በእውነት መንፈስ የምትንከባከብ እናታችን ናት ብለው ይህ የእናንተ ማኅበረሰብ በብልጽግና፣ በተስፋ የተሞላ ማኅበረሰብ ይሆን ዘንድ እንድትረዳችሁ በተጨማሪም ተጨባጭ በሆነ መልኩ በቤተክርስቲያን ውስጥ ተሳታፊ የምትሆኑ ወጣቶች እና ቤተሰቦች እንድትሆኑ ትረዳችሁ ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መማጸን ያስፈልጋል ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

01 June 2019, 08:56